#ለምን? ቁራሽ እንጀራ ለጠዬቀ ካቴና??? ማህጸንን እንደ ዱባ ይቀረድዳል።
#ለምን ? ቁራሽ እንጀራ ለጠዬቀ ካቴና??? ማህጸንን እንደ ዱባ ይቀረድዳል። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" እስከ አሁን የተደከመበት፤ ሙሉ አቅም የፈሰሰበት፤ ብዙ ወገኖቻችን ያጣንበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ #እርካታን ይለፍ ሊሰጠው አልቻለም። ለምን? ከሊቅ እስከ ደቂቅ ኢትዮጵያዊው ዜጋ በአደብ፤ በጥሞና ከራስ ፍላጎት፤ ጥቅም እና ድሎት አለፍ አድርጎ ሊያስብበት የሚገባ በኽረ ጉዳይ ይመስለኛል። በፖለቲካ ምክንያት ትናንት #ስደት ላይ የነበሩት ፖለቲከኞች ዛሬ አገር ውስጥ ገብተው #መኖርን እያኖሩ ነው። ትናንት አገር ውስጥ ሆነው መኖርን ያኖሩ የነበሩ ፖለቲከኞች ዛሬ መኖርን #ለስደት ሰጥተዋል። ይህ ተመክሮ ለዛሬም፤ ለነገም የትውልድ #በረከት ወይንስ #እርግማን ይሆን ብሎ ማንሰላሰል ይጠይቃል። ወደ ራስ አቅርቦም አጀንዳዬ ማለት ይገባል። በዚህ ውስጥ የእያንዳንዱን ዜጋ መብት እና ግዴታ #ሳይጫኑ ወይንም #ሳይጨፈልቁ በቅንነት የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሂደት ቁመና መገምገምም ይገባል። እያንዳንዱ ዜጋ እውነቴ የሚለው የራሱ ሃቅ አለውና። ስለሆነም የችግሮችን #ሴል በማድመጥ እረገድ በወልም በጋራም ሊታሰብበት ይገባል። ምክንያቱም ነገ የስርዓት ለውጥ ቢመጣ እንኳን፤ ይህ ጠቃሚ ያልሆነው የተመክሮ ሰርክል ወይንም አዟሪት ይደገማልና። ከሆነ ቦታ ላይ መቆም አለበት። የመጨረሻው የሊቃውንቱ የዕውቀት ደረጃ #ዶክተርነት ነው። በውነቱ በብዙ ትጋት እና ልፋት የሚገኝ የዕውቀት አስኳል ነው ዶክተርነት። ዶክተርነት የሊቃውንት #ቁንጮነት ነው። ይህ አካል #የዳቦ ጥያቄ አለኝ ሲል፤ የደህንነት ዋስትና ይኑረኝ ሲል፤ መኖሬ በዜግነቴ ደረጃ በልፋቴም ልክ ይሁን ሲል፤ በሊቃ...