ዓይን ያለው ጆሮ የተስፋ መንገድ ነው።

ዓይን ያለው ጆሮ የተስፋ መንገድ ነው።
„መንገዳችሁን እና ሥራችሁን ፈጽማችሁ ብታሳምሩ፣ በሰው እና በጎረቤት መካከል 
ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፣ መጻተኛውን እና ደሃ አደጉን መበለቲቱንም ባትገፉ፣ በዚህም 
ሥፍራ ንጹህ ደምን ባታፋሱ፤ ክፉም ሊሆንባችሁ፣ እንግዶችን አማልክትን ባትከተሉ፣ 
ከዘላለም አስከ ዘላለም ለአባቶቻችሁ በሰጠኋዋችሁ ምድር በዚህ ስፍራ 
አሳድራችኋአለሁ።“
ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፯ ከቁጥር ፭ እስከ ፯  
ከሥርጉተ©ሥላሴ
 27.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።


  • ·       መነሻ።

Mustafa the Builder: My Somali & Ethiopian Identities 
Are Intertwined – SBS Amharic

በተለይም ለበርካታ ዓመታት በአማራው ላይ ስር የሰደደ አሉታዊ 
ስብከቶች ስለነበሩ፤ የመጀመሪያ ልዑካን ቡድናችንን በቅርቡ ወደ 
አማራ ክልል እንዲሄድ እናደርጋለን በማለት የአንድነትና 
ብሔራዊ ማንነት ግንባታ ውጥናቸውን አጋርተውናል።

SBS እንዲህ ብሏል „ሩቅ አሳቢ፤ ቅርብ አዳሪ 
እንደማይሆኑ ተስፋችን ነው።“

እኔ ደግሞ የችግሩን መከራ ስለደፈሩ ይህን መድፈራቸው በራሱ 
የታሪክ ብራና ሊያሰኛቸው ከመቻሉ በላይ አቅም በማመንጨት 
ረገድም ፏፏቴያዊ ዘይቤ ይመስለኛል። ስለሆነም ተስፋዬ በመቁንን 
አይደለም እንደማለት …

  • ·       የቀደመው የሥርጉተ ሥላሴ ዕይታ እና ዕድምታ።

 ዎህ! በተመጠነ ሁኔታ ሰኞ ኦገስት 27/ 2018

የሰብዕዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ሙስጦፋ መሐመድ ኡማር የሰሞኑ 
የመወያያ እርእስ ጉዳይ ሆነዋል። ተመስገን ነው! እኔ ራሱን አስችዬ
 በሁለት ጹሑፍ ኮልሜ ነበር። ከሌሎችም ጹሑፎቼ ጋር በዬጊዜው 
እንደ ሪፈረንስ አድርጌ ሰርቼዋለሁኝ። የሱማሌ ችግር አፈታት ጥበብን
 በእጅጉ ስለተመሰጥኩበት። ያን ጊዜ አጀንዳ አልነበሩም። አሁን የዜግነት
 ፖለቲካ ላይ ውስጣቸውን ምን እንደሚል ከተገለጸ በኋዋላ ልዩ 
መነጋገሪያ ሆነዋል።

ያን ጊዜ ግን ሳተናው፤ ዘሃበሻ፤ ቢቤኤን ላይ የሱማሌ ሁለት አክቲቢስቶቹ 
ጎልተው ከመውጣት በስተቀር ብዙም ልብ ያላቸው ያሰተዋላቸው 
አልነበረም። የሰው ልጅ መጀመሪያ አይን ሊኖረው ይገባል። ዓይን መኖሩ 
መሰካቱ ብቻ ሳይሆን ቁልፉ ጉዳይ ዓይኑ በኢትዮጵያ ፍላጎት ውስጥ 
ማዬት መቻሉ ነው ወሳኙ ጉዳይ።

ከዬትም ይሁን ኢትዮጵያ ያሏት አንጡራ ሃብታት በቅጡ ዕውቅና ሊሰጣቸው
 ይገባል። ልናከብራቸው፤ አይዛችሁ ልንላቸው ይገባል። ነገ ክህደት ሊኖር 
ይችላል በተደጋጋሚ ስለተከሰተ፤ ነገር ግን „እንቅልፍ ተፈርቶ ሳይተኛ መታደር“ 
ግን የለበትም። ኢትዮጵያ ነኝ እስከ ተባለ ድረስ ሁሉን ማቀፍ፤ ሁሉን ማከበር፤
 ሁሉንም ዌልካም ማለት ያስፈልጋል።

ሥልጣኔ የሚባሉ ማናቸውም ጉዳዮች መነሻቸው ዓይን ነው። አስተውሎት ነው 
ዓለምን የሥልጣኔ መናህሪያ ያደረጋት። አስተውሎት አለምን ፕላኔታችን ለሰው 
ልጅ እንድትመች፤ ኑሮን እንዲያቀል፤ በኑሮ የሚፈለጉ ጉዳዮችን አስተውሎ 
በማዬት በመመረመር ዕድሜ እስከ መቀጠል ተደርሷል።

አሁን እዚህ ሲዊዝ ካለ ጨጓራ የምትኖር የ24 ዓመት ወጣት የሥራ ባልደረባ 
ነበረችኝ እኔ። ጨጓሯዋ ወጥቷል። በዓመት በተወሰነ ጊዜ ሆስፒታል ለሁለት 
ሦስት ቀን ቁጥጥር ይደረግላታል፤ ሠርታ አትደክም። ጠንካራ ናት። ዛሬ 
የዲጅታል ዘመን የተደረሰው ብልህ ዓይን ያላቸው ተማራማሪዎች የፈጠራ 
ውጤት ነው። ማዬት መቻል መዬት ለሚችሉ ብቻም የተሰጠም ጸጋ ነው።

ብርቅ የሚባሉ ጋዜጠኞችም ዓይናቸው የሚያዬውን በጆሯቸው መስከሪነት 
በህገ ልቦና ችሎት የሚሰጡት ብይን ነው አስተዋይ ጋዜጠኛ የሚያሰኛቸው። 
እንደ ሰው ስሜታቸው እንደ ሰው ቢፈትናቸውም ግን ስሜታቸውንም ሳይረገጡ፤ ዕውነታውንም ሳይጫኑ አጣጥመው መሄድ መቻላቸው ነው ምርጥ የሚባሉት፤ 
እንጂ እንደ ሁሉ የሰው ልጅ ዝንባሌም አቋምም አላቸው።

ለእኛ ስሜት፤ ለእኛ ፍላጎት ቅርብ እስከ አልሆነ ድረስ አጀንዳ መሆን ያልቻሉ
 ጉዳዮች ባለቤት የሌላቸው የመሆናቸው ምክንያቶች ናቸው ዛሬ ልንገራቸው ከማንችላቸው የመከራ ዕዳ የደረሱት። አሁን አማራ  ከእንግዲህ ወዲያ 
አማራ ነኝ አትበል ቢባል በእጅ አይልም። ይህን ዶክተሪን የሚራምዱ ሰዎችን
 እራሱ አይደለም ሌላው አፍሪካዊነቴ የሚመሰጥኝ እኔን ሥርጉተ ሥላሴ አላዳምጣቸውም።

ምክንያቱም እኔም እራሴ አማራ ነኝ፤ ራሴን ጥዬ የት ልሂድላቸው? እንደ ገናም
 ጥያቄው የሰብዕዊነት ጉዳይ ነው።፡እንደ ገናም ይህን ጥያቄ የሚያነሱ ወገኖቼ 
አማራ ነኝ በማለታቸው 27 ዓመት የደረሰባቸው ሰቆቃ የእኔ ካላልኩት የእኔ ኢትዮጵያዊነት ልጥ ይሆናል ማለት ነው።

ትናንት በአማራነትህ መደራጀት የለብህም፤ ዛሬም አትደራጅ እያልክ  
የአማራ ተቆርቋሪ ነኝ ማለት አይቻልም። ሎጅኩ አያስኬድም። ወይንም
 አንተ ከዞግ ድርጅት ወጥተህ ለዞግ ድርጅትህ እዬሰራህ አማራ ነኝ 
አትበልም አያስኬድም። ወይንም ድርጅትህን የዞጉን ጥለህ ህብረ ብሄር 
ፓርቲ ነን ከሚሉት ጋር መቀላቀል ወይንም ደግሞ ህግ መተላለፉን ማቆም
 ነው። ለአንተ የሰጠኸውን መብት ለሌላውም ያን መብት ይሻዋል። 
ይፈልጋዋል።
  
የቅራኔ አያያዝ ጥበብ ማነስ ነው ብሄራዊ አቅምን የሚጎዳው። አቅምን
 የሚያኮስሰው። በዚህ አጋጣሚ ለለማ አብይ ካቢኔም አሁን ያለ 
ቢመስለውም በዚኸው ከረር ያለ ጉዞ ከቀጠለ የአማራ የድጋፍ መንፈስ
 ሙለውን ያጣዋል። ሌሎች እነ ግንቦት 7 እንዳጡት ሁሉ። ይህ ሃይል 
ቀላል አይደለም። ለኢትዮጵያዊነትም የጀርባ አጥንት ነው። ራሱ አብይን
 ለሥልጣን ያበቃውም ይህ ሃይል ነው። ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂምን ለዚህ
 ቁልፍ ቦታ ያሰጠው የአማራ ተጋድሎም የከፈለው መስዋዕትነት መሆኑ
 መዘንጋት የለበትም።  

ዛሬ እንክህ እንክህ መባሉን አይደለም መታዬት ያለበት፤ በዬቤታችን፤
 በኢሜላችን ስንት ማስጠንቀቂያ ወጀብ በግራ ቀኝ እያስተናገድን ነበር
 ፊት ለፊት ወጥተን የሞገትነው። ዕውቅናውን በሚመለከት በዜሮ ነው 
የተባዛው። ግን ህሊናችን ውስጥ የጸና፤ የፈለቀ የዕውነት ማህደር ስለ
 አለ በህሊናች ውስጥ በፍጹም ሁኔታ ድንግል ሰላም ይገኛል።

ባላፈው ጊዜ የፕ/ አሳያስ ቃል አቀባይ ርዕሰ አንደበት ልበለው በውብ
 አማርኛ በግልጽ እና በአደባባይ ወጥተው አማራን ይቅርታ ጠይቃዋል።
 ተከታታይ ተግባራት ቢጠበቅባቸውም እኔ እራሴ አመስግኜ ጽፌያለሁ።
 ሌላ አንድ ወንድሜም ይህንኑ ፈጽሞታል።

ኢትዮጵያ ትሁን ኤርትራ በጋራ ያላባቸው የችግር ምንጭ አንዱ ይህ ነው።
ህሊና ያለው ዓይን ከተገኘ፤ ዓይን ያለው ጆሮ ከኖረ የሁለቱም አገሮች 
የቋሳ መነሻ የሊሂቃኑ የዶክትሪን ትርጉም ዝበት ነው።

እኛ ቅንነት፤ ደግነት፤ ይቅር ባይነት፤ ኦወንታዊነት፤ ሰላም ፈላጊነት ትህትና፤
 ገርነት፤ መቻል፤ የማይናወጽ ብሄራዊ ስሜት ስላለብን ነው እንጂ 27 
ዓመት የሆኖው ሁሉ፤ ከዛም ቀድሞ 50 ዓመት ሙሉ የሆነው ቢታሰብ ቢሰላ ለእግዚአብሄር ሰላምታ የሚያበቃ አልነበረም።

የ ፕ/ኢሳያስ አፈውርቂ ርዕሰ አንደበት ለነገሩ መንፈሳቸውም ቅርቤ ነው።
 እኔ የረጋ ሰው ክፍሌ ነው። እንዲህ ነበር ያሉት።

„ትልቁ የአማራ ህዝዝብ ያልሆነውን ነበር በማለት አማራ ጨቋኝ አማራ
 የገዢ መደብ ነው አማራ ጠላታችን ነው በማለት ለፍልፈናል። 
ተከራክረናል። ይህ በሙሉ ስህተት ነበር። ነጻ ከወጣንም በሆዋላ 
ይህን ስሀት ማስተካካል ሲገባን አላደረግነውም። ይህም እንደገና 
ትልቅ ስህተት ሆኗል። ስለዚህ ይቅርታ እንጠይቃለን። 
ፍቅር ያሸንፋል! „ 

ይል ነበር። ቃለ ምህዳንም ነው። እኔም ይህን ጤነኛ መንፈስ መዋቅራዊ
 ማድረግን ይጠይቃል በሚል ጠንከር ያለ ጉልበታም ማሳሰቢያ ሰጥቻለሁኝ።

እውነትን መድፈር መልካምነት ነው። ተቋማዊ ማደረግ ደግሞ ጀግንነት ነው።

በሌላ በኩል የረባ ዕውቅና ያልተሰጠው ነበር የሱማሌ ችግር አፈታት። ግን ልክ
እንደ አልጀርሱ ስምምነት እጅግ ደፋር እና እጅግም ልብ ያለው፤ ጥበብ 
የሞላበት የችግር አፈታት እንደ ነበር አበክሬ ገልጨዋለሁኝ። ለዛውም ያን
ጊዜ የሐምሌ 25/26 ዝምታ በመከተመበት ሰሞን ነበር። በዛ ፈጣሪ 
በሚያውቀው ተክዶኖ በባጀው የመከራ ድባብ ውስጥ፤ የጭንቅ ሁኔታ
ላይ እያሉ ነበር ጠቅላይ /አብይ አህመድ እዛው አዲስ አባባ ለችግሩ
እልባት ለመስጠት ሲታትሩ የነበሩት።

የጅጅጋ አካባቢ ነዋሪዎች ሁሉ አዲስ አባባ ድርስ ማምጣት የተፈለገበት
ምክንያት የነበረው መከራ ሌላ ስለነበር ነው የቡና ፖለቲካ ጦስ። 
እርምጃ ዕጹብ ድንቅ ነበር። ከቁጥር ያበቃው ባይኖርም። ዶር አብይ 
አህመድ የሰላም እና የደህነነት ባለሙያነታቸውን ያስመሰከረ ደፋር ልሁቅ
ብጡል ርምጃ ነበር የወሰዱት። መማር ማለት በመሆን የተተረጎመበት 
የዜማ ጊዜም ነበር። በተማሩበት የሰላም እና የደህንነት ሙያ ውስጥ የተገኜ
ፍሬ ነገር ነው። 

ጉባኤው አዲስ አባባ ላይ ነበር የተካሄደው ያን ጉባኤ በጽሞና በመምራት
የሸፈተውን ልቦና፤ የሸፈተውን ቀልብ መስመር ለማስያዝ የዘመናችን አንዱ
ገድለ መጸሐፍ ነበር የተፈጸመው። ይህንም በተከታታይ እንደ ሪፈረንስ 
ተጠቅሜበታለሁኝ።

በዚህ ሂደት ውስጥ ጎልቶ የወጣው ባልተደለመደ ሁኔታ አንድ የሰባዕዊ መብት
ተሟጋች ኢህአዴግን መቀላለቀሉ ነበር። ይህ ነፍስ ያለው እርምጃ ያልታለመ፤ 
ያልታቀደ ነበር። ልክ እንዳ አሁኑ የርዕስ ብሄሯ ምርጫ። ዓይን ማለት እንዲህ
ነው። እንዲህ ዓይን የተሰጠውን ተልዕኮ ለችግር መፍቻ ሲያውል ይበል ያሰኛል።

በዚህ ጉባኤ ልዩ እርምጃው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹን አቶ ሙስጦፋ
መሐመድ ኡማርን ወደ /ፕሬዚዳንትነት ማምጣት ህልም የሚመስል
እርምጃ ነበር። ኪኖ! ልክ አንድ ቅዳሜ ጥዋት ኤርትራ መግባታቸውን
ሰበር ዜና /ሚር አብይ አህመድ ማለት ነው።

እርምጃው አገራዊ ብቻ ሳይሆን መካከለኛውን አፍሪካንም የሚመለከት 
ነበር። ጁቡቲን፤ ጎረቤት አገር ሱማሌን፤ ኬኒያን ይህም ብቻ ሳይሆን 
እርምጃው ክርስት እና እስልምናንም ያካተተ ነበር። ቁልፍ ነበር 
የምስራቁ የአገራችን ጉዳይ የችግር አፈታት ልባዊ ዘይቤ። በዛ ላይ
የኡጋዴ ነጻ አውጪ ጉልበታም ገረር ያለ አቋም ደግሞ አለ።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በቂ የሚዲያ ሽፋን ያለገኘም ክስተት ነበር። የምስራቁ
የአገራችን የግጭት ኢላማ የነበሩት 9 ያላነሱ አብያተ ቤተክርስትያኖች
እና ሰማዕታት የተሰዉበትን የግፍ ጉዞ የጎንደር ከተማ የቅድስት ኦርቶዶክስ
ተዋህዶ አማንያን የእስልምናን ሉላዊ ክብረ ባዕልን አከባበር እንደ 
ለመደባቸው የመቻቻል ተቋምነት በፋሲል ግንብ ከመከበሩ በፊት ቀደም
ብለው አጽድተው ነበር።

መቸም ታምረኛው ጎንደር ጉደኛ ነው፤ የቡራዩ እልቂት እና የመስቀል ባዕል
ዋዜማ የመከራ ደመናን በሚመለከት ደግሞ የጎንደር ከተማ የእስልምና
ዕምነት ተከታዮች ፒያሳን መስቀል አደበባይን አጽድተው ነበር።

ያው የነገረ ጎንደር ልቅና ጎልቶ፤ በልጽጎ እንዳይነገር ስለሚፈለግ በመንግሥት
ደረጃ ተዳፈነ እንጂ /ሚር አብይ አህመድ በአልጀርሱ ስምምነት፤ የሱማሌን
ችግር ለምፍታት የሄዱበትን ብልሃት እና አሁን ርዕሰ ብሄር ምርጫቸው ላይ 
ያሳዩትን ብልህነት የሚመጥን ህዝባዊ ትሩፋት ነበር ጎንደር ላይ በሁለቱ 
ሃይማኖች የተካሄደው ወደር የለሽ ቅኑ ልባም ተግባር።

የጋሞ አባቶቻችን ከፈጸሙት የሚመጥን ነበር። ግን አገሩም፤ ነዋሪውም 
ህዝቡም፤ ጎንደር ዕጣውም በጥርስ መያዝ ስለሆነ የውሽማ ሞት ሆኖ አልፏል።
ጥበበኛው ጎንደር ይህን ለውጥ በማምጣት እረገድም አንጎል የሆነውን 
የትውልዱን ገድል የፈጸመ የአባቶቹን ሌጋሲ በወርቅ ቀለም የጻፋ ነው። 

በዚህ አጋጣሚ የሰብዕዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ሙስጦፋ መሀመድ አማራ ክልል የመጀመሪያ ምርጨው አድርገዋል። ጎንደርን ቢሄዱ ደግሞ በከተሞች ታሪክ 
ኢትዮጵያ ቀደምት ከተሞች አሏት ቢባሉ ጎንደር እና ሀረርጌ ስለመሆኑ ማዬት
ይችላሉ እና ከቻሉ ቢያደርጉት መልካም ነው።

ወደ ቀደመው ስመለስ የሳቸውን ሹመትም አሳምሬ ጽፌው ነበር። ዎህ
በተወሰነ ደረጃ ብዬ። አንጻራዊ ሰላም አገኘሁ በማለት እና አክቲበስት 
ጀማል ዲሪኸሊፍ ወደ አገር መግባት እና /ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፋ
መሀመድ ያላቸው ሰብዕና ኢትዮጵያን የማድን ስለመሆኑ ገልጬ ነበር። 
ሌላም በተከታታይ ጽፌ ነበር ለጊዜው ግን ይህን ማንበብ ይቻላል   ….

በጋዜጠኝነት ሙያ ስሜት ከራስ ከፍላጎት ራቅ አድርጎ መስራትን 
ከሚያስተምሩት አንዱ አቶ ካሳሁን ሰቦቃ ነው። ያው የጥብበ ሰው አንቱ
ስለማይባል ነው አንተ የምለው እንጂ እንደ ብልህነቱ እንደ የማስተዋሉ 
መጠን አንቱታ አንሶበት አይደለም። ስለጎንደር መዳህም እንዲሁ ከልቡ
 ገብቶ አቶ ንጉሡ ጥላሁንን ጠይቋል። አመስገነዋለሁኝ፤ አስታዋሽ 
አያሳጣንም እላለሁ። ለነገሩ የ አገር ሃብትነቱ እጬጌ ነው።

ወደ ቀደመው ምለስት ሲሆን ሰሞኑን የእኔ የውስጥ ተስፋ ያገኜ ቃለ 
ምልልስ አድርጓል በራዲዮ ጣቢያው። መነሻዬም ይኸው ነው። የችግር
 ላይ፤ የችግር ግፋፎ እንጂ መንስኤው ላይ አይሰራበትም እና።፡


ዳርዳር የሚዞረው፤ የግጭቱ የመከራ ሌሊት ጉዳይ አንድ ጉዳይ ነው። ያን 
እስከ አሁን እኔ ነኝ ያለ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊሂቅ አልደፈረውም ነበር።
ዛሬ እኒህ የሰብዕዊ መብት ተሟጋች ደፍረውታል። ሴቶች በፖለቲካ አለም
ተገልን የኖርንበትን የጨለማ ዘመን /ሚር አብይ አህመድ እንደ ደረመሱት
ሁሉ ማለት ነው። አቶ ሙስጦፋ መሀመድም ኡማርም የሴራውን ግንብ እንዳለ ነው ያፈረሱት።

ትልቅ የኢትዮጵያ ተስፋም ሆነው ዘለግ ብለው ወጥተዋል። ቀንዲልነቱ እንደ
ጋሼ ብላቴ ጸጋዬ /መድህን በድፍረት ሊያሰጣቸው ይገባል ባይ ነኝ። እኔ 
ተጠራጥሬ አልጀመርም። እንዳለ በሙሉ ልቤ ነው እምቀበለው። አዎንታዊ
 ሰብዕና ነው ያለኝ። እርግጥ ነው አምኜ መንፈሴን ከሸልመኩት ማግስት ግን 
ክክትሌን ጥብቅ ነው ትችቴም ምህረት የለውም። 

ልብ ሲዳጥ ዝምታ አይታሰብም። ሰው በቃሉ ልክ መሆን አለበት። ያ ሲታጠፍ ቸልታ 
አያስፈልግም። ጉዳዩ የሰው ነውና። አሁን የራያ እና የ ወልቃይት የጠገዴ ጉዳይ 
አብይ ሆይ በሚለው ጹሑፌ ቢያንስ በወፍ በረር ጥበቃ እንዲደረግ አመልክቼ
አሰተዋሽ አልተገኘም። የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ዱላ ነው የገጠማቸው ባህርዳር
ላይ ቤተ መቅደስ ተጥሶ። እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ጃኖ በለበሱበት መንደር። 
  • ·       ስጥ ዳሰሳ።

እንደ ሰብዕዊ መብት ተሟጋቹ እሳቤ መፍትሄ በዘለቄታ ማምጣት የሚቻለው
የዘውግ ፖለቲከኞችን በመጨፍለቅ ሳይሆን፤ የዘውግ ፖለቲከኞችን ሁሉንም 
ተቀብሎ በከፋ ትርክት በውስጥ የተገለለውን አንዱን ማህበረሰብ አማራን 
በመጫን ብቻ መፍትሄ ሊመጣ እንደማይችል ጥልቅ የሆነ መልዕክት 
አስተላልፈዋል።
የዞጉን በውስጣቸው መሽጋው ይዘው ደግሞ ምላስ ላይ የዜግነት ፖለቲካ 
ለሚሉትም በሚሉት ልክ መሆን እንዳለባቸውም ዘመኑን አሳምረው 
ተርጉመውታል። ከራሳቸው ጋር መታረቅ እንዳለባቸው በደሞ አሳስበዋቸዋል። 
አስውበው አይተው አመሳጥረውታል። የዘመን የትርጉም መጸሐፍ ናቸው
ለእኔ ቅኔነትም እንዲህ ነው። ቅኔውም ተዘርፏል።

ትልቁ የኢትዮጵያ ችግርአማራ ጨቁኖሃል ገዝተኋዋል ነውበዚህ ስብከት 
ደግሞ አማራ ዜጋ አልነበረም። አማራ ዜጋ ሆኖ ያልኖረበት ዘመን አልበቃ 
ብሎ አሁንም ኦሮሞ ኦሮሞ ነኝ ሲል፤ ጉራጌው ጉራጌ ነኝ ሲል፤ ትግሬው 
ትግሬ ነኝ ሲል ሌላውም ነኝ አለውን ቢል ዕዳ የለበትም። በዬጓዳውም ህብረ 
ብሄር ነኝ የሚለው የራሱን ዞግ ሰብስቦ ዕውቅና ልዕልና ቦታ ሲያሰጥ ዕዳ ጠያቂ
የለበትም።

ዕዳ የኢትዮጵያ ሆኖ የሚመጣው አማራ አማራ ነኝ ሲል ነው። አማራ ብቻ 
ተነጥሎ እና ተልይቶ ኢትዮጵያዊ ነኝ በል ይባላል። በውስጣቸው የፕ/ መስፍን
 አማራ የለም ዶክተሪን የከተማባቸው በዚህ እሳቤ ይካተታሉ። 

በሌላ በኩል የአማራን ሥነ -ልቦና አጥፍተናዋል ብለው ስለሚያስቡ ሊሂቃን፤ የፖለቲካ ድርጅቶችም አሉ።

በዚህ ዘርፍ ቁልጭ ያለ ጉልህ ድክመት ያለበት ይህን ደፍሮ ማስታረቅ ያለበት 
የአብይ ይሁን የለማ ካቢኔ ጭምር ነው። ብአዴን የአማራ ድርጅት ነው ገዱም 
አማራ ነው። ሥርጉተ ሥላሴ ሽንጧኝ ገትራ አመት ሙሉ የተጋቸው አማራ ናት። 
ግን እኔ እና ሌላዋ እኩል ያዩኛል ለሚለው እእ ነው። ፈጽሞ። እኔም አላስበውም።
የሆነ ሆኖ አገር እንመራለን ሲባል ለድጋፍ ለመጠለይ ሳይሆን ራስን በትክክል 
በተጨባጭ ማስታረቅ ይገባል። አማራ የተበደለበትን አመክንዮ ከልብ ሆኖ 
መመርመር፤ ተበድለሃል፤ ጉደተንሃል፤ ሥነ - ልቦናህን አቁስለናዋል አሁንም 
የሚገባህን እውቅና እንሰጥሃለን ተብሎ መጀመር አለበት።

አልተጎዳም፤ ዘሩ አልጠፋም፤ ጥላቻ አልነበረብንም ጨዋታ ግን የትም አያስኬድም። 
እኔም ሞገደኛውን ሥርጉተ ሥልሴን እራሱ ማሳመን አይቻልም። እውነትን 
አሳማኙ እውነት ብቻ እንጂ ሸፍጥ ወይንም አግድሞሽ መንገድ አይደለም። 

አብሶ እንዲህ ዓይነት የችግሩን ሥረ - መሠረት ከውስጥ ሆኖ የሚያይ ሚስጢር 
የሆነ ሰብዕና ሲመጣ እሱን ሞግቶ አካል ለማደረግ ይቸግራል እራሱ እነ ለማ አብይ። ምክንያቱም ለዚህ ሰብዕና ማዕከሉ ሰው ስለሆነ።

የኢትዮጵያ ሊሂቃን የችግሩ ምንጭ ይህ ነው። ህብረ ብሄር ፓርቲዎች ሲደራጁ
የአማራ ናቸው ባዮችም ናቸው። ህብረ ብሄርም ሲደራጅ አማራ ቁልፉን ቦታ 
እራሱ ላለመያዝ /ላልመስያዝ/ ወይንም ከ አማራ የጸዳ ነው ለማሰኘት 
ተሸማቆ ነው የተኖረው።

አማራዎቹ እራሱ በፓርቲ ውስጥ አብረው ሲሰሩ እንዲህ እንባላለን ስለሚሉ
 ታች ወርደው ራሳቸውን ይሸጉጣሉ።ሲወዱ እስከ ንፍጥ ልጋጉ ነው“ ሲጠሉም እንዲሁ። አማራን አስፓልት አድርገህ ጎማዬ ይሸከርክርብህ ብዙም አያስኬድም። 
በወጉ ያልተያዘው፤ በወጉም ለመያዝ ፈቃድ ያልተሰጠው ነገረ አማራ ካፈነገጠ 
መጨረሻው አያምርም።

የዞጉ ድርጅት እራሱ  አማራ ሲደራጅ ሃይላቸውን ይጭኑበታል፤ መንግሥትን ጨምሮ ይሰፍሩበታል ለዛውም በዱላ። አሁን የአብይ ካቢኔ 6 ወር ምን ሠራ በአማራ መሬት ቢባል ይህን ነው ሲሳራ የባጀው።  አፋር ቤንሻንጉል ሱማሌ ላይ ተጨማሪ ባጀት ነበር። ኦሮምያ ላይ ፕሮጀክት ነው፤ በተጨማሪም ከቻይና መንግሥት ጋር ከዱከም እሰከ 
ቢሸፍቱ የሚደርስ የ80 ፋፍሪካ ግንባት ነበር ፊርማው።

አማራ ላይ ደግሞ ጽድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነኝ ሆኖ ኢትዮጵያዊነትን መጫን ነው። ይህን እንታዘባለን። ቁልፉ ጉዳይ አማራ ገዝተሃል ይበቃሃል ነው። ከአማራ የተወለደ የሌላ ዘር ከሆነ ይሻለናል ዓይነት ነው ጉዞው።

ይህን በቀጣይነት ማስኬድ የሚቻል አይሆንም። ለሶሞናት ሊሆን ይችላል። ለዘለቄታ ግን ግርባነት ማብቃቱንም ሊሂቃኑ ጠንቅቀው ማወቅ ይኖርባቸዋል። የቻለ ህዝብ በቃኝ ካለ ደግሞ መመለሻ የለውም። ሞቱን እንደሆን አማራ 50 ዓመት ሙቷል። እስራቱንም እንደሆን አሁንም እዬዬን ነው። በቃኝ ሲል የሚቀረው እግር ብረቱ ብቻ ነው። እሱን አውልቆ ራሱን ማሰከበር ደግሞ በመዳፉ ያለ ዕውነት ነው።

አማራ በድሎናል ጨቁኖናል ነው ጉዳዩ። የሚገረመው 27 ዓመት ቅጥቅጥ ፍልጥ 
አድርጎ የገዛው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ተቀምጦ የኦሮሞ ሊሂቃን የት ላይ 
እንደሚያማትቡ መመልከት ነው። ነጮች በተሰበሰቡት ስንት ዶክመንተሪ 
ፊልም ተሰርቶበት እነሱ ባዩበት አማራ እዬጨቆን ነው ይላሉ። ሌሎችም እንዲሁ።

አሁን እዬገዛን ያለው ትግሬ እና አማራ ነው ሲሉ ነው የባጁት። አንድ አይነት ነው መዝሙራቸው።  የሚገርመው አሁንም ሊለቁት አለመቻላቸው ነው። በቃ ጨቋኝ 
ገዢ ከሆነ ለምን ይፈለጋል? ለምን አይተውቱም?

ከዚህ ዕውነት ተፈርቶበት ከተኖረው ዘመን ጋር 50 ዓመት ውስጥ እኒህ የሰባዕዊ
መብት ተሟጋች  ጎኽ ቀዳጅ ናቸው ለእኔ። ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህንድስናም
አዲስ የመፍትሄ አምንጭ ባለ ራዕይም ናቸው። ትልቅ አቅም ናቸው። ወጣ ገባው፤ ሰባርባራው፤ ኮረንኮቹ መንገድ ሁሉ ደልዳይም መሃንዲስም ናቸው። አዲስ ተስፋም ናቸው። ለምን? የችግሩን መንስኤን ደፈሩት።

ችግሩን እራሱን ዕውቅና ሰጡት። እንግሊዞች እንደሚሉት ችግርን ማወቅ 50% 
መፍትሄ እንደማግኘት ነው ይላሉ። ኢትዮጵያ መዳን እንድትችል ሁሉም 
የልቦናውን ጣዖት ያውልቀው። ሁሉም በልቦናው የገናባውን የአማራ የጣውነትነት
ሃውልት ያፍርሰው።

ገዛም ቢባል እኮ አገር ነው ጨርቅ አይደለም ያቆዬው እሱ የተጨፈጨፈባትን
አገርን ኢትዮጵያን ነው ያቆዬው። ይህ እንኳንስ ሊያስወቅሰው ሊያሰመሰግነው 
ይገባ ነበር። ዛሬ በአደገች በበለጸገች እርእሰ መዲና መጤም ነው አማራ፤ 
ባይታዋርም ነው? ህም!

የአንድ አገር መሰረት ህዝብ ነው። ህዝብን ደግሞእውቀት መመራት ካልተቻለ
ግዑዝ  ወይንም ዱዳ ነው።  የዕውቀት መሰረቱ ደግሞ ፊደል ነው። የፊደል አውራ 
ነው ይህ ማህበረሰብ። ፍለስፍናው ምርምሩ ጥናቱ ሌላ ቀን እመለስበታለሁኝ።

የሆነ ሆኖ የመጀመሪያው የፖለቲካ ሊሂቅ ችግርን ያልሸሹ፤ ችግሩን የደፈሩ 
ብቻኛው የእኛ ልንላቸው የሚገባ ሰው ናቸው አቶ ሙስጦፋ መሀመድ 
ኡማር። የኢትዮጵያ የመፍትሄ ቁልፍም ናቸው። „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“
 መሰረቱ ከዚህ አመክንዮ ጋር መገናኘት ነው ብልሃቱ። እንግዲህ ኢትዮጵያዊነት
 ሱስ ነው ነፍሱ ካለች ለነገሩ ኦቢኤን አይሆኑ ሆኗል እኮ።

እኔ ልዑል እግዚአብሄርን አማመስግነው የጻፍኩት ጹሑፉን ነሃሴ 27 ቀን 2018
ነበር ስለ ሰብዕዊ መብት ተሟጋቹ። ዛሬ ስጸፈው የኔን ሃሳብ ያሰበለ ጭብጥ 
በተገኘበት የሚዲያም ርዕሰ አጀንዳ በመሆን በአዎንታዊነት ህብር በሆኑበት 
ወቅት ነው። ተመስገን! ለነገ ራሱ ነገ ያስብ። 

ደስ የሚለኝ የጸሁፌ መደበኛ ተከታታዮች ከእኔ ጋር መቆዬታቸው ያላከሰራቸው 
መሆኑም ጭምር እርካት ሰጥቶተኛል። ስለሆነም እኒህ ሊሂቅ ለእኔ ከለውጥ ሐዋርያት ውስጥ ይመዳበሉ። አቶ ሙስጦፋ፤  ክብርት ሳህለ ወርቅ፤ ክብርት / ሙፍርያት፤
አቶ ሚሊዮን፤ አቶ ደመቀ፤ ዶር ገዱ፤ ዶር አብይ፤ ዶር ለማ ስንት ሆኑ ማለት ነው 
አሁን ቁጥራቸው ስምንት ሆኗል።

አንድ ይቀራሉ /ጎሹ ወልዴ የጠ/ሚር አብይ አህመድ አማካሪ ከሆኖ ያን ቀን
ሙሉ ቀን እና ሌሊት ሻማ አበራለሁኝ። እኔ እንደ ዳዊት በወጣትነቴ /አሳፋ
ሞሲሳ የሆለታ ገነት ዋና አሰተዳደሪ እያስጠኑ ነበር ያሳደጉኝ ስለ እሳቸው። 
እና መሪ የአገር ሲባል አሳቸው ነበር በህሊናዬ የሚመጡት።

ኮነሬል ጎሹ ወልዴ ለማናቸውም ችግር ማርከሻ ናቸው ብዬ አስባለሁኝ። ቅንነታቸው
ፍጹም ድንግል ነው። የፓርቲ አባል መሆን ብፈልግ እሳቸው ቢተውትም እሳቸው ከመሰረቱት መድህን ጋር ነበር እምሆነው። ከውስጤ ነው የምወዳቸው። 
ጽላቴ ናቸው ለእኔ ኮነሬል ጎሹ ወልዴ። ሙሉ ዘመናቸውን እንደ ተነገረኝ፤ 
እንዳጠናዋቸው ነው ያገኘኋዋቸው።

በነገራችን ላይ መላ ቤተሰቦ ደግሞ ይወዳቸዋል። አሜሪካ ያሉትም። ጠንከር ያለ ኢትዮጵያዊ ልጅ ከቤት ሲወጣ /ጎሹ ወልዴ ነው የሚባለው። ታናሽ ወንድሜ 
ወደ አገር አሜሪካ ሲሄድ አቀባበሉ / ጎሹ ወልዴ መጣ ተብሎ ነው። እስከዚህ
ድረስ በውስጣችን የሰረጹ ናቸው። ንጠረ ነገራቸው የአገር ማማ እጬጌ 
ያደርጋቸዋል። ይሰሙኝ ከሆነ /ሚር አብይ አህመድ /ጎሹ ወልዴን ውስጠወት
ያድርጉ እና ሰላማዊ እንቅልፍ ልተኛ እባከዎትን ይለመኙኝ ያዳምጡኝም!

ኮ/ጎሹ ወልዴ ለ አብይ ካቢኔ አማከሪ ቢሆኑ? ሐሙስ 11 ኦክቶበር 2018

አብራችሁኝ ላላችሁ የእኔ ውድ አዱኛዎቼ ቅኖች አዲስ አይሆንም ልክ የዛሬ 
ሁለት ወር በዚህ ቀን ስለሳቸው ቅን የሆነውን እይታዬን እና ተስፋዬን ግልጬ ነበር። 
አሁን አዳዲስ ታዳሚዎች ደግሞ ስላሉኝ ነው ሊንኩን የለጠፍኩት ደግማችሁ 
አይታችሁ ምን ያህል ውስጥነት መቅድምነት እንዳለውም መገንዘብ ይቻላል።

ዋናው ቁም ነገር እውነትን ፍለጋ ከሆነ ማስተዋል ላለው ሰብዕና እውነት አቅም
 እያገኘች መሄዷን ማመሳከር ይቻላል። ሌላው ማንኛውንም እርምጃ በቅንነት 
ማዬት፤ በአዎንታዊንት ማዬትን ማስቀደምም ሌላው ፍሬ ነገር ነው። ወጀብ 
አምጥቶ ከሚጨምራቸው ጋር መለዬት ማለት እንዲህ ነው።

እውነት ማዬት ሲፈቅዱት ብቻ ነው ደንጋጣ የማይኮነው። ብዙ ሰው በቀደመው
 የአብይ የ100 ቀናት ትንግርት ደንጋጣ ሆነ። በዛ ውስጥም ሆኖ እንዳለ ነው „ተደምሬያለሁ“ ያለው። የሚገረመው አመሉ እዬተነሳበት አዳዲስ ነገር ባዬ
 ቁጥር መቀበል ሲያቅተው ሰባራ ሰንጣራ ገል ይዞ ከች ይላል። እሱ
የማያደርገውን እሳቸው ሲደፍሩት መጥለቅልቅ ነው በትችት። 

ትችቱ አቅም ያነሰዋል ነው ጉዳዩ አንዲት ሴት ርዕሰ ብሄር ማድረግ ትልቅ 
እርምጃ ነው፤ ይህ ሲገኝ ሌላ ሻታ ይዞራል። ካላቸው ተመክሮ አንጻር 
ያንሳቸዋል ይላሉ። ይገርማል እኮ። ስንት ሊሂቅ ሲገለል እኮ እናውቃለን።

የሚገርመው ያን በተቃርኖ ወጀብ የባጀበትን ጃኬቱን አወላልቁ ደግሞ የፊት
 ረድፈኛ ነኝ ብሎ ቃለ ምልልስ ሲደረግለት ታዩታላችሁ። ከዛ በፊት ሰፊ ጊዜ
 ነበር እውነት የመፈለግ። አማራጭ በእጅ ያለህን መመርምርም ያስፈልጋል። 
የሃሳብ አቅም እንኳን የለም። ሞግተህ የምትረታበት።

ዌብ ሞገድ ላይ ድል የለም። መሬት የያዘ የሚያሰመካ የመንፈስ ሃብት 
ሊኖርህይገባል ተንጠራርቱ  ለመኮፈስ። ያ ነበር ችግሩ። ለዚህም ነበር ልጅ
 ያያዘውን ይዞ ነው የሚየላቅሰው እያልኩኝ ስጽፍ የባጀሁት። እሱ ብቻ 
ሳይሆን ትንግርት የሆኖ የማይካዱ የብቃት አቅምም አለ፤ የአማራር 
ጥበብም አለ። በክህሎት በቅቶ፤ ልቆ ዘለግ ብሎ የመውጣትም ልዩ 
አቅም አለ። የአዲሳዊነት ትሩፋትም አለ። ወደ ትውፊት ማዘንበልም አለ። 


በልዩ አቅም ላይ ልዩ ትኩረት አለ። እነዚህን ከህሊና ሆኖ መመርምር እና
 አቅን ማዋጣት ይገባ ነበር የዛሬ ዓመት እኔ ስጮሕ በነበረበት ወቅት።

ያን ዕድል አጥተነው ቢሆን ኖሮ አሁን ያለንም እናጣው ነበር። የሆነ ሆኖ የእኔ
 ጌጦች ታዳሚዎቼ አብረን በመቆየታችን እንዳልከሰራችሁ ልብ ልክ ነው። 
አብረን እንዝለቅ።

ሙለውን የቃለ ምልልሱን መንፈስ ታች ታገኙታላችሁ። ቀላል የሚመስሉ ግን
 እጅግ ጥልቅ የሆኑ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ደክምንለት ከሚሉት የመሬት ተግባራት
 በላይ እንዲህ ባሉ የግለሰብ ሰብዕናዎችም መገኘታቸውን አዬን።

 ስለዚህ የግል ታጋዮችም የሃሳብ ዲታ መሆናቸው አመሳክሮልናል ይህ ዕድምታ። 
ስለሆነም አቶ ሙስጦፋ መሀመድን በጸሎት እንግዛቸው። ብርቅዬ የሆኑ 
እግዚአብሄር የሰጠን አንድ ተጨማሪ ሥጦታ እና ሸልማታችን ናቸው።

የኢትዮጵያም አዲስ ተስፋ ናቸው፤ ምዕራፍ ናቸው ብዬ አስባለሁኝ የሰብዕዊ 
መብት ተሟጋቹ አቶ ሙስጦፋ መሀመድ ኡማር። ስለሆነም የለውጥ ማህበርተኛ ሐዋርያነታቸውንም ተቀብያለሁኝ እኔ - እናንተስ ውዶቼ? የቻላችሁ ሸር እድርጉልኝ። ክብር ለሚገባው ክብር መስጠት የተገባ ስለሆነ።

#EBC ከሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ጋር በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የተደረገ ውይይት


  • ·       ዱኛዎቼ የቃለ ምልልሱ ጭብጥ ነው ይህ። እኔ አልሰራሁትም ከራሱ ዕይታ ጋር 

ራሲዮ ፕሮግራሙ ኤስ ቢ ኤስ የሰራው ነው። ከድካም ስላደነኝ አመሰግነዋለሁኝ። 
ልባም ራዲዮም ነው።፡  
„በሶማሌ ክልል ሰላምን ማስፈን፣ የሰብዓዊ መብቶችን ጥሰትን መግታት፣ ለሕዝብ ታማኝ 
አገልጋይ መሆን  ከዘርፈ ብዙ ተልዕኮቻቸው መካከል ጥቂቶቹ መሆናቸውን ያመላክታሉ።
ባለፉት በርካታ ዓመታት በሶማሌ ክልል ተከስተው ስለነበሩ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን 
ነቅሰው ሲናገሩም፤ ግድያ፣ ሰቆቃ፣ መንደሮችን ማቃጠል፣ በርካታ ሰዎችን ለስደት መዳረግ፣ 
ለወራት መጸዳጃ ቤት ውስጥ ሰዎችን ማሰር፣ በጅብና በነብር እስረኞችን ማሸበርን በዋነኘነት 
ያነሳሉ። ይህ ግፍ የተፈጸመበት የጂግጂጋ እሥር ቤት ወደ ሙዚየም ይቀየራል በማለትም 
ይገልጣሉ።
ሐምሌ 28 በጂግጂጋ የተካሄደው የአመጽ ጥቃት የተወጠነው በክልሉ ብቻ የተወሰነ ብጥብጥን ለማስነሳት ሳይሆን፤ በደገኛና ቆለኛው፣ በሙስሊሙና ክርስቲያኑ መካከል ግጭቶችን ፈጥሮ 
አገሪቷን ብጥብጥ ውስጥ ለማስገባት እንደነበረ ይጠቁማሉ።
ይህን ያስፈጸመውም መዋቅርና በጀት የነበረው  “ሔጎየሚባል በህቡዕ ይንቀሳቀስ የነበረ 
የወጣቶች ድርጅት እንደነበር ጠቅሰው፤ በአሁኑ ወቅት ግና አብዛኛዎቹ መዋቅሮቹ 
እንደፈራርሱና ቀሪዎቹንም በማፈራረስ ላይ እንዳሉ ያስታውቃሉ።
የማንነት ፖለቲካና የዜግነት ፖለቲካን አስመልክቶ ያላቸው አተያይ አደጋዎችን ጠቋሚና 
መፍትሔን አመላካች ነው።
ማንነት ላይ ያተኮረ ፖለቲካ ዞሮ-ዞሮ ወደ ግጭት ነው የሚያመራው። ከማንነት 
ፖለቲካ ወደ ፖለቲካዊ እሳቤ ቶሎ ብንሸጋገር፤ በዜግነት ላይ ያተኮረ የመብት ጥያቄዎች
የሚመለሱባት አገር ብንመሰርት ደስ ይለኛል ባይ ናቸው።“  /// ይህን እኔ መመረጣቸው 
አስደስቶኝ የዛሬ ሁለት ወር ነሃሴ 27 ስጽፍ ከቁጥር ያስገባው አልነበረም። ///
„ይህንኑ አንድነት ከክልላቸው ለመጀመር  የሶማሌን ባሕልና ታሪክ የሚዘክሩ ነገሮችን 
መሥራት እንዳለባቸው፤ የሶማሌን አንድነት ማጉላቱ የጎሳ ትንቅንቅን ለመክላትና ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖች ጋር የባሕል፣ የታሪክና ልምድ ልውውጦችን በማድረግ መቃቃሮችን
በመቻቻል ባሕል ለመተካት ያስባሉ። በተለይም ለበርካታ ዓመታት በአማራው ላይ ስር 
የሰደደ አሉታዊ ስብከቶች ስለነበሩ፤ የመጀመሪያ ልዑካን ቡድናችንን በቅርቡ ወደ አማራ 
ክልል እንዲሄድ እናደርጋለንበማለት የአንድነትና ብሔራዊ ማንነት ግንባታ ውጥናቸውን አጋርተውናል።“
  • ምንጭ

Mustafa the Builder: My Somali & Ethiopian Identities Are Intertwined
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
ዕውነትን ጊዜ አይላትም! ዕውነትን ጊዜም አይላትም!

ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።