ግራጫማው የኪሳራ ዑደት።

እንኳን ደህና መጣችሁልኝ
ግራጫማው የኪሳራ ዑደት።
„ምልክቱ እንሆ እንዲህ ያለ ወራት ይመጣል፤
በዚህ ዓለም የሚኖሩትም ሰዎች ታላቅ ድንጋጤ ይይዛቸዋል፤
ምግባረ ትሩፋትም የሚሠራባትም አገር ትሠወራለች።“
መጽሐፈ እዝራ ሱታኤል ፫ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
30.03.2019
ከእመ ሲዊዘርላንድ።


·       የቀደመው።

ESAT Eletawi Part Two Mon 25 Mar 2019 1

·       የዛሬው።
ESAT Eletawi Fri 29 Mar 2019

አንድ ቀን ይህ ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊት በሄሮድ መለስ ዜናዊ ዓይን፤ ጆሮ፤ አፍ፤ የአፍንጫ ቀዳዳ፤ በጸጉር ሥር የእጅ ስልክ መብራት እዬተላከላቸው ቴራፒ ሲደርግላቸው እንደነበር በህልሜ እንዳዬሁ ጽፌ ነበር። መፍታት አቅቶኝ ፍቱት ብዬም ነበር።
25.03.2019
መቼም የጀግና ጋዜጠኛ አበበ ገላው ተግባር በሄሮድ መለስ ዜናዊ ህይወት ላይ መቅሰፍት ነበር። ይህ ኢሳት የወሰደው እርምጃ ደግሞ ለሄሮድስ መለስ ዜናዊ ነፍስ ይማር ተጽናና አለንልህ ዓይነት ነው …

ያ መቅሰፍት እንደ ገና ነፍስ ዘርቶ ያደመጥ ዘንድ ነው የሆነው ሁሉ። የቀደመውም የትናንትናውም። የእኔ ህልምም ላካንስ ይህን አስቀድሞ ያሳዬኝ ለዚህ ነበር ብዬ አስባለሁኝ። አቤ ጀግናው የነፃነት ቀን ቀርፆልየተስፋን ማዕልት አበጅቷል። ይህ ደግሞ በምንም ሁኔታ ተረስቶ ሌላ ደባ ሊፈጸምበት አይገባም ነበር። መገፋፋት አለ። ግን ከላአዛሯ ኢትዮጵያ ዕንባ ጋር መሰላት ይኖርበታል።

ነገር ግን የዛን የክፉ ቀን አርበኛ አሁን በማዬው ሁኔተ ኢሳት ላይ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ብቻውን መለመላውን እንደቆመ ነው ያስተዋልኩት። ታድሞበታል። ቀን ሲጠበቅ የኖረ ቦንብ እንሆ አሁን ፈንድቷል። በዚህ የጀግንነት መንፈስ ውስጥ ሶቆቃው ጵጥሮስን አስታወስኩት - አብዝቼ።

አወያዮዋ የመጀመሪያው ቦንብ ፍንዳታ ያቺ በልቤ የመሰጠርኳት ደልዳዋ ጋዜጠኛ እዮሩሳሌም ተክለዛድቅ ነበረች፤ ተወያዮች ደግሞ አቶ ኤርምያስ ለገሰ፤ አቶ ካሳሁን ይልማ፤ አቶ ሃብታሙ አያሌው /ጋዜጠኛ/ ነበሩ። በሁለተኛው ውይይት አወያዩ አቶ ምናላቸው ስማቸው ተወያዮች አቶ አበባ ገላው፤ አቶ ኤርምያስ ለገሰ፤ አቶ ሃብታሙ አያሌው /ጋዜጠኛ/ ናቸው። 

ተደራጅተው የገቡ ነው የሚመለስሉትበዓይን ሁሉ ይናበባሉ። በውሽክታም ይሳላቃሉ። መቼውስ አይጣል ነው ቀን ሲከፋ። ለዛ ለአማራ የህልውና ተጋድሎ ውርስ ቅርስ ከባለቤቱ ከጎንደር እና ጎጃም ህዝብ ለአሸኛኘት አብረው ሁሎችም ታዳሚዎች ነበሩ። 

በዚህ በታቀደ ታልሞ በተፈጸመ ጉዳይ አቶ ተወልደ በዬነ /ጋዜጠኛ/ የለበትም። ጉዳዩ ነገሮች ስለተነሱ ብቻ ሳይሆን ታስቦበት እንደተከናወነ ነው እኔ እማስበው። የሴራ ቁንዳላ ዘፍ ሰፍ … 

ስለዚህ የኢሳት አስተዳደርም አምኖበት አድርጎታል ብዬ አስባለሁኝ። ከራሱ ጋር ንክኪ እንዳይኖርም ብርቱ ጥንቃቄ አድርጓል። የትናንቱም ውይይት በጠ/ሚሩ የሰሞናት መግለጫ ተኮር ይምስል እንጂ ጋዜጠኛ አበበ ገላውን መለመላ ለማሰቀረት ተብሎ ታስቦ የተከወነ ነው። የመቅድሙም ቢሆን በሌላ ጉዳይ አጀንዳ ቢሆንም ጭብጡ ጅራቱ ላይ የነበረ ነው …  የትናንትናው ግን ጭብጡ ቀንድ ሳቢያው ጅራት ሆኖ ሪስፕሮካል ተሰርቶለታል። ኪኖ!

·       ተልቤ ሳስበው።

የጋዜጠኛ አበበ ገላው ክብር በኢትዮጵያ መሬት ነፍስን ያጉላላ ይመስለኛል … አንዱ ክብር ልዕልና ሲያገኝ፤ ያ ክብር እና ልዕልና ሌላው መሰሉን ሲያገኝ ሁለቱም በኢትዮጵያ ፊት የከፍታ እና የዝቅታ መንፈስም የፈጠረ ይመስለኛል አይዋ ቅናት፤ እኔ ብቻ ጀግና ልባል ዓይነት። 

ለዚህ ነው የዛች መከረኛ ባድማ ጀግኖች አፈር ድሜ ግጠው ተበትነው የቀሩት …
ብቻ ነገርዬው የምርምር ኩነቱ ጡዘት እራሱ በኢሳት በአስተዳደሩ ውስጥ ይመስላል። ይህን ጉዳይ በአወያይነት በተወያይነትም ደግሞ ከተቦርን ውጭ መሆኑ ለእኔ ሌላም መልዕክት አለበት። ታቡቱን ቡሩኬን እረስቼው አይደለም። አብዝቼ ነው እሱንም እምወደው። መስጥሬ አከብረዋለሁኝ እንደማለት …  

የመጀመሪያውም የአሁኑንም ጋዜጠኛ አቶ ተወልደ በዬነ እሱ እንዳይሳተፍ፤ በዚህ ጉዳይ መንፈሱ እንደይኖር ጥበብ በጥንቃቄ  ተሰርቶበታል። ስለዚህ ሌላም የሚንተከተክ ነበር አለበት በተቋሙ ውስጥ። ለነገሩ ካልጎሼ አይጠራም … አገር ያሉትስ ምን እና ምን እዬሆኑ ይሁን … አብሶ የዲሲዎች? እነሱም ያውም በዚህ መሰል ቁልፍ ጉዳይ ባይተዋር እንዳልነበሩ አስባለሁኝ ያው ጥንስሱም ዝልሉም ዓይነተውም እፍታውም ቤተኛ ነው እንደማለት።

ስለዚህ ለህይወታቸው ይታሰብ እንደማለት ለአሁኑ መንግሥት ሰጥ ለጥ ካሉ ግን ይቀጥሉ … በቀደመው መልክ ወረፋ እንገባለን ከሆነ ግን አደጋ አለበት። ሁሉም ሲጓዝ ምልስት ይሆናል ብዬ ሁሉ ነበር። 

ምክንያቱም የደህንነት ዋስትና ላይ ዝበት ስለማይ … ህግ ማዕከል ካልሆነ አደጋ አለበት። አሁን ካላገዷቸው ሹልክ ቢሉ ጥሩ ነው … ቋያው አይሏል … 

 እኔማ ከጅምሩ የቆሞስ ስመኛውን ህልፈት ካዬሁ በኋዋላ ለማጽናኛ በዋዜማው ጎንደር ላይ የነበረ የተቀደሰ ተግባር ጋር ግምኛ ተወራርሶብኝ ግንቦቶች ለመሄድ ሲወስኑ ግንቦት 7 አበደ ነው ያልኩት፤ ኢሳትንም እንዲሁ …

·       ህምታ በእምታ ሲጠመቅ።

እንዲህ ዓይነቱ የማጋለጥ እና እውነት የመፈለግ፤ የማፈላለግ ጉዳይ በራሳቸው ድርጅት በግንቦት 7 በራሱ በኢሳትም ቢጀምሩት ዕውነት ክብር ተጎናጸፈች ማለት ይቻላል። ግን አንድ አቅጣጫ ከሆነ ግንጥል ጌጥ ነው … ለእኔ። 

አሁን አቶ ሃብታሙ አያሌው በጠ/ሚር አብይ አህመድን ያነሳው ዕውነት የእኔም ነው ግን በሁሉም ሲሆን ነው ሚዛናዊነት ሊኖር የሚችለው፤ እሱም እኮ የአዲሱ ካቢኔ የውስጥ ሚስጢር አዋቂነት ቆሞስ ስለነበር በምን ስሌት የሚለውም እንዲሁ ከአቶ ምናላቸው ስማቸው በደንበር አገላለጽ ሁኔታ ጋር ሲላትም አይ ነበር። „እኔ ይህን አላውቅም“ ብሎ ነውና የሚነሳው አቶ ምናላቸው ስማቸው። እንደ እኔ የግንባር ሥጋም ይመስለኛል።  

… ስለዚህ ቤተኝነቱ በቀኝም በግራም በራስም በግርጌም እንዳለ የሚያሳጡ ሁኔታዎች ስላሉ እውነትን ከራስ በመጀመር ቢሆን ያምራል እንደማለት ... አንዲት ቅንጣቢ መረጃ እኛ አናገኝም፤ ሌላው ደግሞ በኩንታል ሲሆን ወራጅ ተዚህም አለ ያሰኛል … እንደ ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ...  

·       ዝቀሽማ ትርፍ።

… ህወሃት በሁለት መልኩ ነው ያተረፈው ኢሳት በወሰደው እርምጃ። አቤን መለመላ ለማስቀረት ወይንም አደጋ ውስጥ ለመቀርቅር ወይንም ተቀባይነቱን ለማሳሳት ወይንም ሰው እንዲጠራጠረው ለማደርግ የኢሳት ሃያል የራሱን የጥንካሬ መንፈሱ ጥቃት እንዲፈጸምበት አድርጓል። ምን አልባት አቤ እንዲህ በጥድፍያ ወደ አገረ አሜሪካ የተመለሰበት ጉዳይም ይኸው ይመስላል። ለነገሩ እኔ ድንግልዬን ለምኜ ስለነበር ተመስገን ብያለሁኝ።  

በኤርትራና በኢትዮጵያ ያለው ግንኙነትም ከእንግዲህ ውሃ ቅዳ ውሃ መለስ ሲሆን ህወሃት ያተርፍበታል ማለት ነው። ዝቅ ብዬ አነሳዋለሁኝ ይህን ጉዳይ። ከቀደመው የመጀመሪያ ፍንጭ የአሁኑ ደግሞ ከፋ … የራስ ገማናን ሜዳ ላይ የፖለቲካ ብስለት አይደለም። የትኛውም የመንግሥት ሚዲያ እንዲህ ተዝርክርኮ አያውቅም። ኢሳት ተዝረከረከ። ብዙ ጉዳይ ነው በዚህ የሚናደው። እኔ እንዲያውም ቆርጠው ያወጡታል ሁሉ ብዬ አስቤ ነበር … ጭራሽ የእልህ ደመራ አደርገውት ቁጭ አሉ። እግዛኦ!

በሌላ በኩል ብዙ ነፍስ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለ በሳት ላይ ጨዋታው ታቅዶ ቢከወንም ግን ስጋቱን ለመቀነስ ያ ይሆናል ብዬ ነበር ሃላፊነት ለሚሰማው፤ ለነጻነት ለሚታገል ተቋም በመዳፉ ላይ የሚሊዮኖች ነፍስ ስላለ …። 

ተቆርጦ ቢወጣ እና ደፍን እምቅ አድርጎ ቢያዝ…  አስተዳደር ስሜት ሳይሆን ጥበብ ነው። አስተዳደር በቀልን ማብቀል ሳይሆን በቀልን መቅበር ነው። አስተዳደር ዕንባን መቀነስ እንጂ ዕንባን ማራባት አይደለም። አስተዳደር ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለዛሬ ለነገ ለነገ ተወዲያ አውንታዊ ድልድይ መስራት ነው። አስተዳደር ህሊናን አሸንፎ ስክነት ተመግቦ የሰውን መንፈስ ከሚያውኩ ነገሮች መቆጠብ ነው። የአንድ ሰው ነፍስ ጭንቀት የእኔ ማለትን ይጠይቃል አስተዳደር …
  
 በሌላ በኩል በሚዲያ ሥነ - ምግባርም እንዲህ የስለላን ተግባር በሙያነት ጨምሮ ደርቦ መሥራትም ሌላው የኤቲኪስ ጉዳይ ነው። እርግጥ ነው የምርመራ ጋዜጠኛ ተግባርና ሃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ብቻ ብዙ ነገር ነው የላዩ ወደ ታች የታቹ ወደላይ የተመሰቃቀለው። ጥቃት አልወድም እኔ። ያመኛል …።  

ኢሳት በአዲስ አበባ፤ ኢሳት በባህርዳርና በጎንደር ኢሳት በሚሊዬነም አዳራሽ፤ ኢሳት  በእናቶች ዘንድ ልብ ውስጥ ያለው ቦታ እና ድርሻ፤ በወደፊት በሚዲያው ተስፋ ላይም ግርዶሽ የሠራ ተግባር ነው ብዬ አስባለሁኝ።

ንዶ መገንባት ከባድ ነገር ነውና። ለማፈረስ 5 ደቂቃ አልፈጀም፤ መልሶ ለመገንባት ግን ዓመታትን ይጠይቃል። ያውም እኛ የደረጃ ነገር ሳይሆን ንፋስን አምነን የተቀመጥን ዜጎች ነን። ወጀብ ነው የአቅም ስንቃችን የሚያሰባስብልን። 

ገናና ሥምን የሚመጥን ጥንቃቄ ያስለፈልግ ነበር። በዚኽው ውስጥ የታሪክ ጥቅርሻነትም አለ። አንድ ሚዲያ ምን ሲባል? እንደ አንድ የፖለቲካ ድርጅት የደህነነት ቢሮ፧ እም ነው ከቶ ስንት ጊዜ እናምጥ … ? ? !

አሁን ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ፊት ሲመጡ ኢሳት ሞግቷል፤ አብሶ ጋዜጠኛ ኤርምያስ እና ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ብራና ላይ ሁሉ ብዙ ሞግተዋል። ከዚህ ሁሉ በፊት ግን ሰውም አቅም ሳያፈስ ይህን አሁን አወጣነው የሚሉትን መረጃ ቢያስቀድሙት ይሻል ነበር። ከብዙ ድካም ብዙውን ሰው ይገላግል ነበር። ሰው በሚያውቀው ልክ ስለሆነ ሊደግፍም ሊቃወምም የሚችለው።

·       አሁንስ።

መግደያ መዳህኒት ቆጥቦ ይዞ ግን፤ ያን እዬመዘዙ መንፈስ ማወክ የጽድቅ መንገድ አይደለም። ጠቃሚም አይደለም … አሁን በአደባባይ ሰው እዬተረሸነ እኮ ነው … በራህብ እንዲያልቅ እዬተደረገ ነው … ለተጎጂዎች የሚረዳ እንኳን ፈቃድ ተነስቷል … ብዙ ነገር ነው ያለው … ከሰብዕዊነት አንጻር … ሌላው ሙሉ ለሙሉ መረቡ ሲዘረጋ ሁሉ በእጅ ስላላ ነገም እንዴት ለሚለው ፊት ለፊታችን ግራጫ ይሁን ምን አለ … አቅሙ ከኖረን … ስልት ጥበብ እንደ አባቶቻችን … ቢኖረን ይበጅ ነበር።

ቀድሞ ያ ተከውኖ ቢሆን ኖሮ እንዲህ መቋጠር ካልተቻለ፤ አሁን ደግሞ ባለው ነገር ላይ ማተኮር ይቻል ነበር። ቀን እዬጠበቁ ቁርሾን እንደ ማዳኛ መሳሪያ፤ እንደ ዕውቅና መስበሪያ፤ እንደ ተቀባይነት ማነኮቻ ማዬት በቀጥታ የድምጽ አልባዎቹን የኢትዮጵያ እናቶች መከራ ቢጨምረው እንጂ አይቀንስውም። በፍጹም። ጉዳዮቹ የአስፈላጊነታቸው ልኬታ ህሊና ሲፈርደው የቀደመ ይሁን የዘገዬ እውነት ጋር ለቆሙ ስዕል ይሰጣል መረጃ ያቀበላል … አሁን የአቶ ወንድም የአቤው እናት ሌላ ተጨማሪ ስጋት ውስጥ ነው የሚሆኑት … በግራ በቀኝ …  
  
በቅድምያ ፈጣሪዬን እማመሰግነው ግን አቤ ወደ አሜሪካ ስለተመለሰ ነው። ወደፊቱም ህይወቱ ከቀደመው በላይ ያሰጋኛል። በግራ በቀኝ ስቅዛት አለበት። ሁለት ያጣ ጎመን ነው የሆነው። እሱም ስለምን አደገኛ ነገሮችን እንደሚሞካከር አይገባኝም። ለዛውም ጠንቃቃ አይደለም። በፈጣሪ ጥበብ ነው ህይወቱ የሰነበተው። 

አሁን የሆነው ሁሉ የሄሮድስ መለስ ዜናዊን የሙት መንፈስ ቢያፋፋ እንጂ ለነፃነት ትግሉ የሚጠቅም ፈጽሞ አይደለም። ደም መላሽ ነው የሆነው ኢሳት ለሄሮድስ መለስ ዜናዊ የሙት መንፈስ አምላኪዎች። ያሳዝናል።

በዚህ ውይይት የሦስት መንፈስ አህታዊነት እና የአንድ መንፈስ ገላይነት በግልጽ አይቻለሁኝ። ይህ መከራዋ አላዛሯ ኢትዮጵያ ይጠቅማል ወይ? ሲባክን ለነበረውትውልድ መንፈስስ? በምንም መስፈርት አይጠቀምም - አፍሰን መልቀም፤ ለቀመን መሰብሰብ፤ መልሰን ማፍሰስ - የኪሳራ ኡደት ።

አቤ ትናንት ያደረጋቸው ማንም ያልደፈራቸው መሰረታዊ የጀግንነት ተግባር የፈጸመ ሰው ነው። የእሱ የጀግንነት ዓይነት ከትርጉም በላይ ነው። አፍሪካንም ቅድስት ኦርቶዶክስን ያከተተ ገድል ነበርና። ያን ታምራቲዊ ጉዳይ በሰውኛ የመተርጎም አቅም ያለው የለም። ኢሳትም የተነሳበትን ቢያውቅ መልካም ነው። ማነው ገኖ እንዲወጣ ያደረገው? ማን? በማን ድምጽ እና ሰማዕትነት? ህሊና? ? ? !!!

የሆነ ሆኖ ጊዜ አይተን የምናከበረው ጊዜ አይተን የምናገለው ሊሆን አይገባም ሰምዕትነትን>> ሰው ሲወደህ ሁለመናውን ሲሰጥህ ውስጡን ይፈቅድልሃል።  ስትለዬው ደግሞ የሰጠህን ጠብቀህ መያዝ ይገባል ይህ ከምንም በላይ ከአንድ መምህር የሚጠበቅ ነው። ይህን ማተብ የመጠበቅ የአደራ ውል ነው ሰውን ከእንሰሳ የሚለዬው። ይህን በሚመለከት ስሜቴን የጻፍኩበትን ሊንክ ይህ ነው። ስሰማው በጣም ነበር የደነገጥኩት። በአንድ ቀን እልም የሚል ነበር የመሰለኝ። አሁን ተረጋግቻለሁኝ።

·       ትናንት ሲታሰብ።

ሌላው ከህወሃት ጋር አብሮ የሠራው ሁሉም ነው። በዛ ውስጥ የነበሩ ጥፋቶች ደረጃው ቢለያይ እንጂ ሁሉም ያን ሥርዓት እንዲቀጥል ማገር ሆኖ ዕድሜ ማራዘሙ፤ አቅም ማባክኑ ግምት ውስጥ መግባት ይኖርበታል። ካድሬ ስልጥናም እኮ ሌላ ምን አለው ህወሃት ለ100 ዓመት የግዛት ህልሙ ቤት ማዋቀር እኮ ነው። አሁን ያለውስ መከራ ያ በጽኑ አለት ላይ የተገነባው ጉዳይ አይደለምን?

ህወሃት እንዲያገግም 40 በላይ ሊሂቃን ከአዲስ አበባ ሲባረሩ ተክቶ ቀዳደውን ደፍኖ መሥራት ህወሃት ጎኑን እስኪጠግን መተንፈሻ ቧንቧ መስጠት አይደለምን ወይ? ሌሎቹ ደግሞ ገበሬ ሆነዋል። ነገር ግን ነፃነት ተራ ደርሶ ሲቀማ ደግሞ ብዙ የሰው ህይወት የተገበረበት ከቀስተ ደመና እስከ አርበኞች ግንቦት 7 ድረስ ብዙ ብዙ ነገር ሆኗል። 

አሁን ደግሞ ለአዲስ ሰማዕትነት ህዝብ ተሰናዳ እዬተባለ ነው። ሂደት እንዲህ ነው ሊታይ ሊለካ ሊመዘን የሚችለው ... ነገ ወዮልህ? 

የጽናት ዋልታ ፈላስፋው / ምንዳርአለው ዘውዴ - ሰማዕትም!

·       ዝርግነት እና አደጋው።

ሌላው እንዲህ መሰል ጥልቅ ረቂቅ ሉላዊ ጉዳይ በደቦ የሚሠራ አይደለም የአቤ ስህተት ከዚህ ላይ ነው። የሎቢ ሥራ ተናጠላዊ ጥንካሬን ብቻን ይጠይቃል። ከድኖ መያዝ። ብቻ የጀመሩትን ብቻ ሆኖ መከወን። አሁን የጋሼ ሙሉጌታ ሉሌ ሞት እንዲህ በዝምታ ተውጦ የቀረው በልባሞች ስለተከወነ ነው።

አብሶ እንዲህ አይነት መጠራቅቅ የሚያስጋባ ጉዳይ ላይ ዝርግነት ጠቃሚ አይደለም
ሰው ራሱን ብቻ ማመን እንዳለበት ይህ አመክንዮ አሰተምሯል የናደውን ንዶ፤ 
የተረተረውን ተርትሮ፤ የፈለጠውን አፍልሶ። የጋሼ ሙሉጌታ ሉሌ ህልፈት እንደተከደነ የቀረበት ምክንያት እኮ የጥንቃቄው ሂደት በደቦ ስላልተሰራ ነው። የነፍስ ጉዳይ ላዘውም ይህን መሰል ጥልቅ ጉዳይ እንዲህ የገበያ ሸቀጥ ማድረግ ቀድሞውን የተገባ አልነበረም። ድንበር ያላቸው ነገሮች አሉ።

·       ሌላ የድል አውታር ዝርጋታ በሌላኛው አቅጣጫ።

ብቻ ሁለት ነገሮችን ከሰሞኑ ማዬት ይቻላል። ከፕ/ብርሃኑ ነጋ ከ0BN ክፍል ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ክፍል አንድን በጥሞና አዳመጥኩት። በውነቱ እሳቸው አይመስሉም። የውስጥ መረጋጋታቸው ሸፍቷል። ክፉኛ የተንቦጀቦጀ አዬር አስተዋልኩኝ። 

እስር ቤት ሆነው የሚያደርጉት ነው የሚመሰለው። በምልሰት የአቶ አንዳርጋቸውን ቃለ ምልልስ አዳመጥኩት። ልዩነቱ የአሁኑ ሥልጡን ለማድረግ የተሄደበት መንገድ ነው። ውስጤን በፍጹም ሁኔታ አዘነ። የአንበሳ ግርማ የለም አሁን ላይ።

Ethiopia || በጉጉት ሲጥበቅ የነበረው ቪዲዮ ወጣ || / ብርሃኑ ነጋ ነጥብ ጣሉ ?

|| ለማንኛውም ክፍል አንድን ይከታተሉ


ምኑ በጉጉት እንደተባለለት አላውቅም። ከዚህ ቀደም ይህን አዘጋጅ ዋልታ ላይ ነበር እማዬው የወደቀባቸውን ሚዲያ ለመጠገን ዝውርውር ፈጽመዋል። ታማኙ ሆኗል። ምርጡም ሆኗል።

ብቻ ብቻ ጋዜጠኛው ያሰበውን ባሰበው ልክ ውሽክ እያለ በፍፁም በተረጋጋ እና  በአሸናፊነት ስሜት እየነካካ ክሩን አሰተርትሯል። እሳቸው ደግሞ ሌላ ሰው ሆነዋል። እራሱ የእጅ እንቅስቃሴያቸው እና ጠቅላላ መላ አካላታቸው፤ ተክለ ሰውነታቸው በራሱ የሚናገረው ነገር አለ። ሆን ተብሎ ታቅዶ ከዛ እንዲቀርቡ እንደተደረገ ነው እኔ ያስብኩት። ከዞግ ሚዲያ? ዋልታ ሲለምናቸው አሻም ማለታቸውን አዳምጠናል።

እንደ እኔ ሰብዕናቸው ላይ የተቃጣ አንዳች ነገርም አለበት። ግን ለምን? ስለምን ብዬ ስጠይቅ ያሉበት ሁኔታ አጣብቂኝ እንዳለበት ተረድቻለሁኝ። በሌላ በኩል ራሱ የመስከረሙን ግጭት በሳቸው ደጋፊዎች እና በኦነግ ደጋፊዎችን በኦሮሞ ወጣቶች እና በአማራ ወጣቶች አድርገው አቅርበውታል። አዲስ አባባ ብሄር አልቦሽ ናት ...
ይህም የመጨነቅ ይመስለኛል። 

በሌላ በኩል የደቡብ ሲሉም ጎላ ብሎ ሆኖ በማያውቅ ሁኔታ በጭንቁ ጊዜ በኤርትራ በርሃ ባልታዬ ሁኔታ የደገፋቸው የትኛው ማህበረሰብ እንደሆነ ልባቸው ያውቀዋል አዲስ አባባ ላይ። ግን ክርስቶስ ለሥጋው አደላ ሆኖባቸዋል። አጋልጠው አሳልፈው መስጠት አልፈለጉም ተዚህ ላይ ልባም ሆኑ ለጠረን። የጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ ተልዕኮ ይኸው ነበር። ዛርማን መግራት። አሁን ይልቅ ወደ ድርጅትነት ማደገኑ አዳምጫለሁኝ። አብን ላይ አውሊያ እንደያዘው አንዳች ነገር ከመከመር ራሱ ካደራጀው አዲስ የዘውጌ ድርጅት ጋር ይታገል መጀመሪያ ጋዜጠኛው ድፍረቱ ተቆርቋሪነቱ ለኢትዮጵያ ከሆነ … ።

ይህም ብቻ አይደለም አማራ ነው ብለው ስላሉ ይሆን የአዲስ አባባው ጭፍጨፋ ሆነ እስርት ድርጅታቸው ዝም ያለውን ወደሚለውም ይወስዳል ልክ አብረዋቸው የነበሩት አረበኞች አገር ሲገቡ በጭነት ተጭነው ወደ ባዕታቸው እንዲገቡ ሲደረጉ ተረሳን እንደሚሉት? ልክ በዛው መጣን ያን ሊያካክስ በሚችል መንገድ ነው አቤን ኢሳት ላይ የጠበቀው የገጀሞ ቋያ ፍትጊያ። ኢሳት እና ኦቢኤን። ሁሉም በመዳፉ ባለው አቅም ቀዝቃዛውን ጦርነት ጀምሯል።

በዚህ ውስጥ ያ ትንታግ ጀግና አቤዋ ጥግ አጥቶ ባይታዋር ሆኖ ነው ያዬሁት። ተጠቃሚው እውነት ለመናገር ህወሃት ብቻ ነው። ኦቢኤን እራሱ የሰራውም ይኽንኑ ነው። ቢያንስ በእጃችን ውስጥ ባለው አቅም እራስን ላለማጋለጥ መጣር ይገባ ነበር። ጥቃት በዬትኛውም ሁኔታ አይመችም። ያ ክፉ ቀን ሊታሰብ ይገባል። ሁሉም በእጁ ባለው አቅም በእጁ የገባውን ነፍስ አጋልጦ ለመስጠት ተሰልፏል። ያማል።

... ሁለቱን በጥምረት ሳገናዝበው አላዛሯ ኢትዮጵያ እንዴት በዬዘመኑ የሰው ድሃ እንደምትሆን አስተዋልኩበት። ራሳችን በራሳችን አቅማችን እዬበላን የምንሄድ ፍጡራን። "አናሳዝንም ወይ?" ትንቢተኛ እንቡጥ ባለቅኔ ትንግርት ነው ተግባራዊ ሆኖ ያዬሁት። የአላዛሯ ኢትዮጵያ ፖለቲካ አይዲኦሎጂው ሴራ ብቻ መሆኑንም አስተዋልኩኝ።

·       የመከራ ቁልል።

የኢትዮ አርትራን ግንኙነት ቀደሞ በመቃወም የኢሳት መንፈስ ግንባር ቀደሙ ነበር። አይሳካም የሚል ዕድምታ ነበረው። የምሥራቹ ሲጦፍ ደግሞ የእኛም እጅ አለበት ነበር። አሁን ደግሞ የራሱን እጁንም የቆረጠ ነገር ተፈጽሟል። አለንበት ስላለ ግንቦት 7። በዚህ የኢንሳ የተግባር ማዕቀፍ ውስጥ ኤርትራ ዋንኛ ኢላማ እንደሆነች የተዳፈነው ነገር የአደበባይ ቄጤማ ሆኗል። ይህ ከአገር ክህደት ጋር ይሁን አይሁን አላውቅም … እንዴት ሊመዘን እንደሚችል … አደብ አጣን። ግን ለምን?

ብቻ በቀጣዩ ኢሱ እና አብዩ የሚያሻክር ጉዳይ አለበት። ኮነሬሉ አብይ አህመድ ድርሻ ስላላቸው። ይህ ጉዳይ ... የኤርትራና ኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታም ያካታል። ከዚህች ቃለ ምልልስ በኋዋላ ኢሱና አብዩ አብረው በቀደመው መልክ ውስጥ ለውስጥ በጀመሩት መልክ ይቀጥላሉ ለማለት ይከብዳል።

በምድር ተፈጥሯቸውን መተርጎም ከማይችሉት መሪዎች መካካል ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ አንዱ ናቸው። ይህን መረጃ ቆቅ ሆነው ነው ወደ ምርም ማዕከላቸው የሚያስገቡት። ሰተት ብለው ሌላ የቅድመ ሁኔታ ስውር ሽልማት ተሸልመዋል። አላዛሯ ኢትዮጵያ ብተሰቀዝ ምን ማን ያተርፍ ይሆን?

ስለዚህ ግንቦቶች እኛም አለንበት ያሉትን የጸሐፊውን ዕድምታ ይንደዋል፤ በቀጣይም ለኢትዮጵያ መንግሥት አደጋ አውጇል። ተመስጥሮ የተያዘው ነገር ሁሉ መናድ ይጀምራል። ስምምነቱ አደጋ ላይ ወድቋል።

ስለዚህ ህወሃት በእጥፍ ድርብ አትርፎበታል ማለት ነው። አቤ ራሱ በራሱ በገነባው ድርጅቱ ውስጥም ሰፊ ግለት ሲፈጸምበት ስላየሁኝ ብቻውን ቆሟል ማለት ይቻላል። ያን ገናና ቀን አለማሰብ ደግሞ ማተቢስነት ነው። ይህ ብቻ አይደለም በዚህ ጥልቀት ወደ ውስጥ ስናስበው የብአዴን ፈተናንም በቀጣይነት መለካት ይቻላል። ምክንያቱም አብይወለማ ሙያቸው የሚሰጣቸው ይለፍ ስላለ።

በሌላ በኩል ልዕልት ትግራይ በጀመረችው የጥንካሬ አብራክ እንድትቀጥል ሌላ ድርጅታዊ ተግባር ኢሳት ሠርቶላታል። ጠቅሟታል ማለት ነው። ኤርትራ ከማዳፏ ጥልቅነት አገኘች፤ የሄርድስ መለስ ህልፈት፤ የአባ ጳውሎስ ህልፈት ደምመላሽ ተገኘላቸው። ወጪ ሳያወጡ።፡„አይቡን አይቶ አጓቱን ጠገቡ" ይላል የጎንደር ሰው። "በሬ ሆይ ሳሩ አይተህ ገደሉን ሳታይም“ ይላሉ እነዚኸው ፊደልኛዎች … ንደቱ የቀረው የለም ... ያልነካው ቀጠናም የለም።

·       ህግነት።

በልክ ለመራመድ፤ በስክነት ለመጓዝ፤ ጥበብን ቅረበኝ ለማለት የራስ ፈቃድን ይጠይቃል። አደጋውን መቋቋም የሚችለው ህወሃት ብቻ ነው። ገሮች በዚህ ፈተና ውስጥ ከቀደመው ፈተና በላይ ከግማድ በላይ አሳር አለባቸው...

አሁን ጋዜጠኛ አበበ ገላው አንደሚነገርን ሁሉ የመሰለውን ነገር የመናገር ነፃነት ማግኘቱን ገልፆልናል አገር ቤት። ይህ ጊዜያዊ ነው። ብሮድ ካስት አሁን የኦነግ መንፈስ ነው የሚመራው። መከላከያው የአዬር ሃይሉ ኦነጋዊ ነው። ሰንቱ ምንቶስው ቅብጥሮሶው ያው በዛው ነው እሱ በእሱ …  ያው ዶር ብርሃነመሰቀል አበበ „አብይ የኦነግ ወራሽ ነው“ ባሉት መሰረት።

ኦህዴድም አቋም መግለጫውን ሲያወጣ የኦሮሞ ህዝብ እና የኢትዮጵያ ህዝብ እያለን ነው … ለቄሮም ጥሪ ተላለፈለት ነው የሚለን አደራዳሪ ሦስተኛ መንግስት ተመደበለት አለመባላችንም ደግ ነው። እሳቸውም ፊንፊኔ ሲሉ፤ የኦሮሞ ህዝብ እና የኢትጵያ ህዝብ ሲሉ ዕድምታቸው ጠፍቷቸው አይደለም። ባለቅኔ ስለሆኑ።

ድብቅም የለበትም የህዝብ አሰፋፈር ስብጥር ቀን ከሌት እዬተከወነበት ስለሆነ … ምን ታደርጋላቸሁ ተብሎ በአደባባይ ተገልፆል።


አቶ ለማ መገርሳ አንድ ሚሊዮን ኦሮሞዎችን አዲስ አበባ ለማስፈር ሲባል ሆን ብለው 
ከሶማሌ ክልል ራሳቸው እንዳፈናቀሏቸው ተናገሩ
February 26, 2019
ስለ ሦስቱ ጥምር የሲኦል መንገዶች።

ምን ለማለት ነው ከዚህ ላይ አሁን ያለው ነፃነት አንፃራዊ ነው ለማለት ነው … አይቀጥልም አንድ ብዕረኛ በአደባባይ ጦርነት እገጥማዋለሁኝ ሳናጃ ስንማዘዝ ያን የሚመራ ፊሻካ ነፊ ያስፍልግኛል ያሉት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ቅቤ አልነበረም … ስብሰባዎች ሁሉ „የለውጥ አደናቃፊ“ በሚለው ሽፋን ውስጥ የነፃነት ግንዛት እዬታወጀ ነው።
https://www.youtube.com/watch?v=aGQfuWK7MD4
/ ዶክተር አብይ አህመድ በአዲስ ወግ ላይ ኢትዮጵያን በተመለከተ ያደረጉት ንግግር

ዕድሜ ይስጠው ሁሉም ነገር፤ አሁን ያለው ነገር ጤዛ ነው የሚሆነው። አዲስ አበባ ወጣቶች በአደባባይ ሲረሸኑ የሆነውን ተመልከተናል …  ርዕሰ መዲና ላይ … ጌዲኦ እና የኦሽቲዝም ዕጣ ፈንታ ቤተኘነት አስተውለናል … የባስኬቶ ጉዳይም ባለቤት የለውም። 

በዚህ ውስጥ አብይወለማ ሙያቸውን ለሉዕላዊነት ማወል ሳይችሉ ልባቸው ከሸፈተ አደጋው ከመቼውም ጊዜ በላይ የከፋ ነው የሚሆነው። በእጃቸው ነው ሁሉም ነገር የሚቆረጠው። ለዚህም ነው እኮ አቶ ደመቀ መኮነን ከስልጣን ለማስነሳት መሰከረም ላይ ተግተው የነበረው፤ ለነገሩ በህይወት እንዲሰነብቱ ከተፈቀደም መልካም ነው።

እነኛ መልካም ነገሮች በመልካምነት ይቀጥላሉ ለማለት ምልክቶች አያስደፍሩም፤ ለስልት እንደሆነ ነው አሁን አሁን እሚሰማኝ፤ የቅድስት ኦርቶዶክስ አንድ መሆን ያስፈነጠዘንን ያህል ሌላም መከራም፤ ሌላው ገማና አለበት። እንሱ አዲስ ጳጳስ አዘጋጅተዋል።

… እኒህ ሊቀ ጳጳስ አገር ከመግባተቸው በፊት ኢሳት ቃለ ምልልስ አድርጎላቸዋል። ሂሳቡ በምንኛ እንደሆነ አላውቅም እዮር ይጠዬቅ … በዚህ ስሌት ስንሄድ ልክ የፖለቲካ ድርጅቶች አገር እንዲገቡ በተደረገበት መሰመር ህውከትን መዳፍ ውስጥ በጥበብ አስገብቶ ሰላምን ማግኘት ይመስላል።
   
በሌላ በኩል ሂደቱን ቁጭ ብዬ ስገመግም አሁን ቀደም ባለው ጊዜ የአብይን ሌጋሲ እንደግፋለን ያለውን ነፍስ ሁሉ ኑዛዜ ላይም እዬተሠራበት ነው በሌላ አቅጣጫ ደግሞ። በተለይ በተዋቂ ግለሰቦች ዘንድ። ለምሳሌ አቶ ኦባንግ ሜቶም አናዞታል አቶ ምንላቸው ስማቸው … ውጭ አገር ላይ።

የሰው ልጅ የሰውን ዐዕምሮ የሚያነብበት ፕላኔታችን መሳሪያ አልፈለሰፈችም። በሚታዩ መልካም ነገሮች ድጋፍ መስጠት እና ጸጸትን ማሳነቅ ሌላው የሥነ - ልቦና ጫና መፍጠሪያ መሳሪያም ይመስለኛል። የሴራው አይዲኦሎጂ እንዲህ ነው። ዕውነትን የወገኑ ነፍሶች ምንጊዜም ተፈታኞች ናቸው። ተጠራጣሪዎች እና ሸረኞች ደግሞ የነፍሳቸው ኦክስጅን ይኸው ነው። ጊዜ እዬጠበቁ ማራገፍ።  

·       ወይ ቅንነት የት ላይ ይሆን ያለኸው?

ቅንነት እንዴት እናገኝው? ጨለማን እንደምን ታግሰን ብርሃን እንዴት እንፍጠር? ብቻ ይህ ውይይት ብዙ ነገሮችን እያነሳ ሞገተኝ ራሴኑ፤ ካሜራ ሲታሰብ የኢንጂነር ስመኘው በቀለ ህልፈት እና የካሜራው ቀድሞ መነሳት ደግሞ ምን ትሆን አንተስ አልኩኝ። ዋዜማ ጎንደር ሌላ የበጎ ተግባር ተከውኖ ነበርና ያስ መጽናኛ ነበርን ስል እራሴን  ከዕለቱ ጀምሮ እሞግታለሁኝ። የቆሞስ ተሰፋዬ ጌታቸው ህልፈትስ

መዳኛችን ለማግኘት ቅን ብንሆን ... ንጽህና ቢኖረን ... መታምን እንድንኖርበት ብንፈቅድ ፈጣሪም ቢረዳን ... በመልካሙ ቀን ያሳለፍነው ወላዊ ቤተሰባዊ ትትርና፤ ትጋት ክፉ ቀንንም ለማሳለፍ በእዮባዊነት ውስጥ ብናሰከነው ምን ነበረበት?

አሁን እንደነበርነው ብቻ ሳይሆን ከቅንጅት ስንብት በኋዋላ ከሆነውም የከፋ ነው። ያ ዕድል በጥበብ እና በክኽሎት ተይዞ ቢሆን ኖሮ ለአሁኑ አዲስ መከራ ደግሞ እንዲህ አንዳረግም ነበር።

መበተናችን ለትውልዱ ቀጣይ ተስፋ ፋይዳውና ውድቀቱ? ሁሉ ነገር ሊፈጠር ይችላል ግን ሁሉም ነገር አይጠቅምም። እንደ ተቋም ለራስ ድርጅትም ክብር መሰጠት ሚስጢርን የመጠበቅ፤ አካልን አሳልፎ ላለመስጠት አብዝቶ የመጠንቀቅ፤ ጊዜ ሲሰጥም በልክ መያዝ መልካም ይመስለኛል።

በመጨረሻ ይህ ገመና ነው። ገመናው ደግሞ ከትወልዱ የሃሳብ ብክነት ጋር መመዘን አለበት። እንዲህ ዓይነት ነገሮችን አደባባይ ላይ ሳይሆን ቤት ዘግቶ እንደ አንድ ቤተሰብ ቢሆን ምን ነበር?

ቂመኛ ባንሆን? ቀን ጠብቀን ቂምን እንደ ጋሻ ባንጠቀምበት ... በዚህ ውስጥ የሚታመሙ ሰዎችም ስላሉ ... ፈጣሪም ያዝንብናል ... ለዚህም እኮ ነው መጋቢት አንድን እንድናይ ያደረገን ... እናደክማለን - እኛው። አላዛሯን ኢትዮጵያን የዝብሪት ቤት አደረገናት እንዳያልፍልን ራሳችን የረገምን።

በዚህ ውስጥ ግን ኢትዮጵያን ለማጥፈት፤ ለማፍለስ የሚታሰበው ነገር ሁሉ ራስን ያጠፋል። ዛሬ አንድ ነገር አዬሁኝ። የኦነግ አርማ አኩል አዲስ አባባ ላይ እዬተውለበለበ ስለመሆኑ። የቀደመው ይሁን አይሁን አላውቅም ሊንኩን ግን ለጥፌዋለሁኝ። ምን ታመጣላችሁም ነውም … አሁን ከሆነ መቼም ጦርነት ታውጇል። 

https://www.youtube.com/watch?v=blT6vdIq_k0

አስራት ትዝብት - አዲስ አበባ ላይ የኦሮሚያ ባንዲራ ከኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በላይ ከፍ ብሎ ሲውለበለብ ዋለ

Published on Mar 26, 2019

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።


መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።