የጽናት ዋልታ ፈላስፋው ፕ/ ምንዳርአለው ዘውዴ - ሰማዕትም!
እንኳን ደህና መጡልኝ።
„አንቺ
አገር ኢትዮጵያ?!“
እውነትም ምንዳርአለው ዘውዴ!
"ምድር ሁሉ እግዚአብሄርን አመስግኑ ዕለት ዕለት ማዳኑን አውሩ። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፳፫
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
22.01.2019
ከእመ ዝምታ።
የጽናት ዋልታ!
„ሰው የሰማ ዕለት ያብዳል ይላሉ“
ጎንደሬዎች ሲተርቱ። እንዲህ ዓይነት የመከራ ናዳ በድንገት
ሲሰማ።
· መነሻዬ።
„ትግሬ ሆነው ይህንን ግፍ ሲሰሙ ምን አሉ ግን? ያሳዝናል በልጆቻችሁ ለ27 አመት ያልተሰራብን ግፍና ወንጀል የለም:: እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጠን ብቻ:“
ውዶቼ
እንደምን አላችሁልኝ? የ27 ዓመታት ደመመናዊ ፍዳ - መሳደድ በዬሁኔታው እንዲህ የመርዶ መባቻውን በተለያዬ ሁኔታ እንዴት ናችሁ
እያለ ራሱን ገልጦ እያሳዬን ነው … ጠንከር ብለን መጋፈጥ ነው። ጆሮም አላድምጥም አይልም፤ ዓይንም አላይም አይልምና። ባንታደል የሆነ ነው ...
· ግርምታ።
„አንቺ አገር ኢትዮጵያ“ ርዕሱ የእኔ አይደለም የባለ ቅኔው ጠ/ሚር አብይ አህመድ የቅኔ ዕርእስ ነው። ትርጉሙን እንደ
አቅሚቲ እኔው ሠርቸዋለሁኝ። ረጅም ጊዜ ነበር የወሰደብኝ ወደ ሦስት ወር ያህል። የፈተነኝ ጉዳይ ነበር።
መጻፍ ለእኔ ሥራ አልነበረም ይህ ግጥም ግን እሽት ነበር ያደረገኝ። እርግጥ ነው በዶር አብይ አህመድ
በሳቸው ውስጥ ሆኜ ለመተርጎም አላስብኩትም፤ እንደዛ አይደፈረም። የሳዕሊንና የባለቅኔን ሥነ- ውበት መተርጎም እንደ አድናቂው አቅም ይወሰናል። ስለሆነም እንደ አንድ አድማጭ
ሆኜ የእኔ ቢሆን ብዬ ለመሥራት ነው ሦስት ወራት የፈጀብኝ።
ክብረቶቼ የአገሬ ልጆች ነገረ አርሲ ጉዳዬ ነው። የዛሬን አያድርገውና ቀደም ባለው ጊዜም አርሲዎች
በተለይ ሮቤ እና አሰላም ዋናው የኢሠፓ ቢሮ፤ እንዲሁም መሪው
ቅኑ እና ደጉ ሰው ወዳዱ ጓድ ስለሺ መንገሻን ጨምሮ ተዛውሬ እንኳን „የእኛ ልጅ ጎንደር አለችን“ ይሉ ነበር።
አርሲን እወደዋለሁኝ። አርሲ
ሲነሳ ልቤ ትርትር ይልብኛል። ናፍቆቴ የልብ ነው። ስስቴም የህሊና። ከበቆጂ ልጀምረው፤ በቆጂ፤ ዲክሲስ፤ ሮቤ፤ ሴሩ፤ አምኛ፤ እንዴት ይረሳኛል? ያ ሞንሞና ሰው
ወዳጁን ህዝብ እና አዬሩን እንዴት ልርሳው? የአንድአቤትን የእስቴውን
እርጎ እዛ አግኝቼው ነበር አምኛ ላይ። የሲዊዙን ቤርኒ አትክልትም እንዲሁ … የውልቂጤን አይቤም ሮቤ ላይ እንዲሁ … የጭኮ የገንፎ ዓይነትም
ልዩ ጣዕም እና ማዕዛው ይመጣብኛል፤
ብቻ አርሲ ዛሬ እንዲህና እንዲያ ሲባል ግርም ይለኛል። እኔ ብሄድ ምን ይሉኝ ይሆን እላለሁኝ። ባለፈው ጊዜ ግንቦት 7 ስብሰባ ጠርቶ እክል እንደገጠመው አዳምጬ ነበር። እንዲህ ሰው ጠል አርሲ አልነበረም።
አርሲ ማንን ይመስላል ቢባል ጸሐውንፊ፤ ጹኑውን ፈላስፋውን ፕ/ ምንዳርአለው ዘውዴን ይመስላል ነው እኔ እምለው።
ፍጹም የሆነ ኢትዮጵያዊነትን ነው እኔ እማውቀው። ዘንበል ያለ፤ የተከዘ፤ የወዬበ ኢትዮጵያዊነት እኔ
አላውቅም፤ አላዬሁም። እንግዳም ለአሪሲዎች ንጉሳቸው ሆኖ ነው እኔ እማውቀው። ስጦታ በጣም ነው የሚወዱት። ዛሬ ደግሞ አትምጡብን
ነው የሚደመጠው ያ የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ክፉ ዘመን ያወረሰው ቅርስና ውርስ ሰውን መጥላት ነው።
የሆነ ሆኖ ዛሬም ሌላ የታሪክ ገጠመኝ አዳመጥኩኝ። እንዲህ ነው አገር መውደድ ማለት፤ ታታሪ፤
ትጉሁ፤ ልቅናው ዝልቅ፤ ጽኑ፤ ብረት መዝጊያ የሆነ ለአገሩ ታማኝ በመሆን ያን ሁሉ ፈተናን ታግሶ መኖር የሚችል የብጡልነት ቅኔያዊ ተቋም።
የ27 ዓመቱ ብሄር ብሄረሰቦች የእኩልነት ድሪቶ ይህን መሰል ብቃት አፍ ባለው መቃብር ቤት ቀብሮ ማስቀመጥ ነው። እኒህ ታላቅ ሊቀ ሊቃውንት ሌላ ምንም ሰሃ የለባቸውም፤ እኒህ የአገር አንጡራ ሃብት
ፈላስፋ ኢትዮጵያን ጽላታቸው ማድረጋቸው ብቻ ነው።
በዛ ጨላማ ዘመን፤ በዛ ድቅድቅ ዘመን፤ በዛ አሳዳጅ ዘመን፤ በዛ ወላፈን ባዬለበት ዘመን፤ በዛ ወጀብ በሚነሽጠው ዘመን፤ በዛ የክት እና የዘወትር ልጅ በተፈጠረበት ጠጠራም ዘመን፤
በዛ ሲሶ እና እርቦ ዜግነት በተለዬበት የጠቃራ ልስን ድንብልብል ድፍን ዘመን እንዲህ ነው ዜጋው በአገሩ፤ በመሬቱ፤ በኑሮው፤
በህይወቱ ተዘቅዝቆ እንዲኖር የተፈረደበት።
የትግራይ ሊሂቃን ከውቅያኖስ በጭልፋ በቀረበው የሰብዕዊ መብት ረገጣ ያ ይፋ መሆን አልነበረበትም ብለው ሲገመድሉ በብዙ መልኩ አዳምጫለሁኝ - እያዘንኩኝ።
እነሱ እንኳንስ ሊጸጽታቸው እና ለቀሪ ግና ላልተፈጠሩት የተጋሩ ህፃናት ሊያስቡ ቀርቶ በእልህ እና በመታበይ ነገን ለማጨለም ሲተጉ
ነው እኔ እማዳምጠው - ማህጸኔ እያለቀሰ።
አንዱ ከረዳት አውሮፕላን አብራሪነት ገበሬ፤ ሌላው ደግሞ ከዩንቨርስቲ ሊሂቅነት ወደ ገበሬነት።
ይህ በራሱ የ27 ዓመቱን የአሳር ዘመኑን ያነባል
- ይተረጉማል ያመሳጥራል። ይህ ይቀጥልለኝ እያለን ነው የአቶ ዳውድ ኢብሳ ኦነግ እና ደንበኞቹ። ራሱ በኦህዴድ
ውስጥ ያሉ የሚታመሱ ነፍሶች ይህ ይቀጥልልን ነው ጉዳያቸው …
እኒህ ታላቅ የአገር ጉልላት፤ የአገር እጬጌ፤ የአገር ታቦት እንዲህ ባለ ጽናት፤ እንዲህ ባለ
እዮራዊ ብቃት እና ብርታት፤ እንዲህ ባለ መሆን ዛሬን አምጠው ሰጥተውናል። በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ ሆነው በገሬው ማሳቸውን እያረሱ፤ እያረሙ እዬጎለጎሉ፤ ዕውቀትን እንደ ፏፏቴ ሉላዊውን
ዓለም ሳይቀር አስተምረዋል፤ አመራምረዋል፤ አስብለዋል። እንዲህ ዓይነት ሰብዕና በ100 ዓመት የሚገኝ ነው። አላዛሯ ኢትዮጵያ አገሬ እንኳንም ደስ አለሽ።
በሳቸው የልብ ቅንነት ጸሎት ነው ዛሬ ተፈውሶ እንዲህ የተገኘው። የቅኔው ሉዑል ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን
የወንድ ልጅ ዕንባው በሆዱ ነው፤ "ብቻውን ነው ወንድ የሚያለቅሰው" የሚለው እንዲህ ነው። አዬ ታቦት ጸጋዬ! ይህን ታሪክ እና የወንድ ልጅ
ዕንባው ትንቢቱ እና ቅኔው ሳሰበው ብላቴው ነብያነት ነበር ማለት እችላለሁኝ።
የአላዛሯ ሃብት የመንፈስ እንዲህ እየተሳደደ፤ እንዲህ እዬባከነ፤ እንዲህ አልሆኑ ሆኖ ተቀብሮ
እንዲቀር ነው ዛሬም ማፈረስን አቁመን የእውቀት ሽግግር እናድርግ በሚለው ተፈጥሯዊ እና ሰዋዊ የለውጥ ታግሽ ጉዞ አሻም ያሉት ጉለሌ ላይ እና መቀሌ
ላይ ከዝነው አሁንም ህዝብን እያመሱ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጋው ወገናች አገር ውስጥ ተፈናቃይ ያስደረጉት። ለዚህ መታመስ ተባባሪው
ደግሞ የጎንደር የቅማንት ሊሂቃን ናቸው የህውሃት ማንፌሰቶ የንስሃ ልጆች።
ወደ ቀደመው ምልስት ሳደርግ እኒህ ታላቅ የአገር የወገን የሁላችንም ባለውለታ እነሆ ዛሬ ጸሐይ ሆነው ብቅ ብለዋል። በህይወት ስለኖሩ
እዬነገሩን ነው። ገዳያቸው ያልታወቀው፤ አፋኛቸው ያልታወቀው፤ እነ ፕ/ እምሩ ስዩም እና ስንት ትንታግ ወጣት ደግሞ እንደወጡ ቀርተዋል።
እንዲህ የበቀለ
ሲደርቅ፤ የበቀለ ሲከስል፤ የበቀለ ሲመክን ማዬት የህውሃት ህልም ነበር፤ አደረገውም አንድ ትውልድ … እንዲህ ሆኖ በነነ … እግዛብሄር አምላክ ያን ጭራቅ ዘመን አያምጣብን። አሜን!
· „ልብ ያለው
ሸብ“
የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን ያገኘውን በረከት፤ አሁን ያገኘውን እዮራዊ ምርቃት የመጠበቅ ግዴታ አለበት።
ያ ጨጎጎት ክፉ ዘመን መልሶ እንዳያገግም ከእያንዳንዱ በግል ከሁሉም በጋራ ቅንነትን ለአገር ስጦታ ማቅረብ ይጠበቅብታል። ህዝቡረ አሱ ወታደር መሆን ይነርበታል።
አላዛሯ
ኢትዮጵያ ከሁሉ የምትጠብቀው አንዱ ዋነኛ ነገር ቅንነትን ነው። ከሴሮኞች፤ ከተንኮለኞች፤ ከክፎዎች ርቆ እግዚአብሄር በሚወደው መልካምነት
ውስጥ ለመኖር መፍቀድ ዘመኑ የጠዬቀው ልዩ ተጋድሎ ይመስለኛል።
በተረፈ የተከበሩ ፕ/ ምንዳርአለው ዘውዴ እንኳን ኖሩልን። ጀግንነት ብቻ ሳይሆን ጀግንነትን
በሰማዕትነት ጠልፈው ዛሬን ስለሰጡን እናመስግነወታለን። ክቡርነተዎት ክብራችን፤ ኩራታችን፤ አስተምህሯችንም ነውት። እንኳንም ኖሩልን!አቅለዎት፤ አደበዎት፤ ችሎታዊት የመቻቻልም ተቋም ነው።
እርስዎ ታሪካችን - ትሩፋታችን - ትውፊታችን ነዎት። እርስዎን በ100 ዓመትም አናገኝወትም።
እንኳንም ኖሩልን። ጽናተዎት አንድ ትውልድ ይገነባል። ፈተናን
ታግሶ በማለፍ እና በማሳለፍ ብቻ ሳይሆን ጽናት እና ተጋድሎወት ሐዋርያ ነዎት።
መጸሐፍ ድርሳን መወድስ ሁለማና ነዎት! ግዕዝ ተምረው ቢሆን እንዲያው ምን ይሆኑ ነበር እያልኩ
ሁሉ አሰብኩኝ። አስናቀው ነዎት! ቅኔ ነዎት! ምስባክም ነዎት! ቀሪ ጊዜዎት የሐሤት፤ የፍሰሃ፤ የደስታ፤ የሰናይ ይሆንለዎት
ዘንድ ከልብ እመኛለሁኝ - በትህትና እና በ አክብሮት። ሽልማታችን ነዎት! ድምጸዎትን በመስማቴ ደስ ብሎኛል። እግዚአብሔርንም አመስግኜበታለሁኝ። ይኑሩልን ለቅኖች እና ለአላዛሯ
ኢትዮጵያ!
https://www.youtube.com/watch?v=76IFoT-5yrg&t=582s
አብይ ኬኛ በ2017 የተጻፈ።
https://www.youtube.com/watch?v=76IFoT-5yrg&t=582s
አፈሬ ነው መስመሬ(23 06 2018)
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው!
የኔዎቹ መልካሞቹ ኑሩልኝ!
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ