ምንጃር ሸንኮራ አውራጎዳና የሰባዕዊ መብት ጥሰት፤ የተፈጥሯዊነት ቅጥቀጣ። 3000 ተፈናቃዮች የተጠለሉበትን ልቀቁ ተባሉ፤ በቀያቸው ያዘመሩት ጤፍ እና ማሽላለእንሰሳት መኖ በግፍ ስለመዋሉም ዜናወች እዬተደመጡ ነው። አጣሩት።

ምንጃር ሸንኮራ አውራጎዳና የሰባዕዊ መብት ጥሰት፤ የተፈጥሯዊነት ቅጥቀጣ። 3000 ተፈናቃዮች የተጠለሉበትን ልቀቁ ተባሉ፤ በቀያቸው ያዘመሩት ጤፍ እና ማሽላለእንሰሳት መኖ በግፍ ስለመዋሉም ዜናወች እዬተደመጡ ነው። አጣሩት።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 

 
በምንጃር አውራ ጎዳና ላይ በግፍ በኦሮምያ ልዩ ልዩ ኃይል እና በፌድራሉ ሠራዊት የተፈፀመው ግፍ ቀጥሏል።
1) ነዋሪወችን አፈናቅለው የነፍስ ወከፍ ንብረታቸውን በአደባባይ ዘርፈዋል።
2) ነዋሪወች የዘሩት የማሽላ እና የጤፍ አዝመራ ልክ እንደ ግጦሽ መሬት ላይ እንዲቀር ዘመቻ ተከፍቶበታል ይላል ዘገባው።
3) ነዋሪወች ወደ ቀያቸው ሊመለሱ ቢፈልጉም የፌድራሉ ሠራዊት አግዷቸዋል።
4) ነዋሪወች የተጠለሉበት የመልካ ጅሎ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለትምህርት ስለሚፈልግ 3000 ተፈናቃዮች መጠለያ ማጣታቸውን ተገልጧል።
5) ተፈናቃዮችን እስከ አሁን አንድም የግብረ ሰናይ ድርጅት፤ ሰባዕዊነት የሚሰማው ግለሰብ አልጎበኜንምማለታቸው ተደምጧል። እሩህሩሁ ረፕ/ ሲሳሳይ በመታሰራቸው ባሊህ ባይ አለማግኜታቸውን አዳምጫለሁኝ።
ተፈናቃዮች የመልካ ጅሎ መጠለያ ለመደበኛ ትምህርት ተፈልጎ ሥራ ሲጀምር ቀጥታ የጎዳና ተዳዳሪ ይሆናሉ ማለት ነው። ይህንን ሥርአቱን አበክረው የሚደግፋ ሚዲያወች ጉዳያቸው ሆኖ ሲሞግቱ አልተደመጠም። ይልቁንም ብልጭልጭ ጉዳዮችን እያገነኑ ይህን አይተው ኖረዋልን እያሉ ሲያለዙ፤ ሲያባጭሉ፤ ጭካኔን ሲያበረታቱ አስተውላለሁኝ። ፕሮፌሽናል ጋዜጠኞች ሳይቀሩ ለጭካኔ ድጋፊ ሲሰጡ ከመስጠት በላይ የሚያሳዝን ነገር የለም።
የሆኖ ሆኖ የምንጃር ሸንኮራ የአውራጎዳና ምንዱባን ማን አላቸው? ማንስ ይድረስላቸው። የኢትዮጵያ ሰብአዊ ኮሚሽንስ ቢበዛበትም ጫናው ባሊህ ሊለው ይገባል ባይ ነኝ ይህን ያፈጠጠ የወረራ፤ የአስምሌሽን እና የመስፋፋት አና ያለ ድዌ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
05/10/2023

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።