ሶዶ ጉራጌ ወረራ እና አስምሌሽን በኦነግ ተፈፀመበት። አፋር ላይም አፈና አለ።

 

ሶዶ ጉራጌ ወረራ እና አስምሌሽን በኦነግ ተፈፀመበት። አፋር ላይም አፈና አለ።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"

 
#የጉራጌ ህዝብ ቀደምት እና ቁምነገር የሆነ ህዝብ ነው።
#የጉራጌ ማህበረሰብ ኢትዮጵያን ከመሠረቱ በኽረ ማህበረሰብ አንዱ ነው። ጉራጌ ጭምት፤ ትሁት፤ ትጋት፤ ጥንካሬ ብርታት እና ቅንነት የተሰጠው ጨዋ ህዝብ ነው። ጉራጌ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ፈላስፋም ነው።
በቤተሰብ አስተዳደርም ጤናማ እና ተፈጥሯዊ ሥርዓትን የሚከተል ድንቅ ህዝብ ነው። ጉራጌ ህይወቱ፤ ትንፋሹ ሥራ ነው። ባህሉ የሥራ ተቋም ነው። በጎራጌ ማህበረሰብ ጭምትነት የምንማርበት እንጂ የምናፍርበት ምንም አይነት የሥነ ምግባር ጉድለት ወይንም ግድፈት አይቼ አላውቅም።
ብዙ ነገር ያለው፤ ብዙ ነገር ማድረግ የሚችል ሆኖ በልኩ የሚኖር ትምህርት ቤት የሆነ ማህበረሰብ ነው። በጉራጌ ውስጥ ያለው ጥንካሬ ምንጩ ኢትዮጵያዊነት ነው። ኢትዮጵያ ትቅደምልኝ የሚል ቅን ክቡር ህዝብ ነው ጉራጌ። የጉራጌ ህዝብ አሁን ግን በጣም ችግር ውስጥ መሆኑን እያዳመጥኩ ነው ግፋ ከተቻለ። ውሃ ለጠዬቁ ባሩድ አልበቃ ብሎ አሁን አስምሌሽን እዬተፈፀመበት ነው። ዲስክርምኔሽንም እዬተካሄደበት ነው። 10 ቀበሌወች በመንግሥት ሙሉ ፈቃድ ሰሞኑን ተወሯል። መወረር ብቻ ሳይሆን ያልታዩ፤ ያልተደመጡ ፋሺስታዊ ብቀላ እንደተፈፀመበት መገመት ይቻላል።
የጉራጌ ልጆች ሊቃናት እና ሊሂቃን ዝምታቸው ግን ያስፈራል። በዚህ የመዋጥ የመሰወር አደጋ ዝምታው ይጨንቃል። ቢያንስ ሎቢ ላይ መትጋት እንደምን ያቅታል። ሰላማዊ በሆነ መልኩ ማህበራዊ ሚዲያ ላይም የህዝቡን ጉዳት ማሳወቅ ከእያንዳንዳችን በግል ከሁሉም በጋራ ይጠበቃል።
ይህን ትጉህ፤ ንቁ ለኢትዮጵያ ልቅና ልዕልና ሰፊ ድርሻ ያበረከተ ህዝብ በቁጥሩ ማነስ ምክንያት ቸል ሊባል አይገባም። አካል እዬተጎዳ እና እዬተሰቃዬ ዝምታ ያስፈራል። በተለይ ተወላጆች ሆነው ጥሩ ቦታ ላይ የሚገኙት የታሪክ ኃላፊነት ያለባቸው ይመስለኛል። እንደ ጠፋት፤ እንደተዋጡት የጋፋት ማህበረሰብ ፈተናው ቅርብ ሆኖ ይታዬኛል።
ከዚህ አንፃር የኢትዮጵያ ሰባዕዊ መብት ኮሚሽንም ጉዳዩን ባሊህ ሊለው የሚገባ ይመስለኛል። በሌላ በኩል ከክልሉ አስተዳደር ጋር ባለመግባባት አፋር ላይም በርካታ ወገኖች እንደታፈኑ አዳምጫለሁ። ቀጣዩ የአፋር ዕጣ ፈንታም ከጉራጌ የሚለይ አይሆንም። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነትን የዋጠ ያዋህደ ህዝብ ብቻ ሳይሆን አፋር ቀደምትም ነው። አፋርን የሚረዳው አፋር በጁቡቲ፤ አፋር በኤርትራ ስለሚኖር ዘር የመትረፍ ዕድል ይኖረዋል። ጉራጌ ግን ይህ ዕድል የለውም።
ውዶቼ እንዴት አደራችሁልኝ። ደህናም ዋሉልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተሥላሴ
SerguteSelassie
05/10/2023
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።