ከመስከረም 5/2011 ዓም ጀምሮ አዲስ አበባ ለኦሮምያ ገፀ በረከት ተስጥታለች ስል ተረብ የሚመስላቸው ነበሩ።

 

ከመስከረም 5/2011 ዓም ጀምሮ አዲስ አበባ ለኦሮምያ ገፀ በረከት ተስጥታለች ስል ተረብ የሚመስላቸው ነበሩ። ከእኔ ጋር የዘለቁ ጥቂቶች እንደሚያውቁትም ከሁሉ ተለይቼ የዘመኑ የፖለቲካ ባህሬ የገዳ ወረራ፤ የገዳ መስፋፋት፤ የገዳ አስምሌሽን፤፦የገዳ ዲስክርምኔሽን ነው። ጥቂቶች "ተረኝነት" ሲሉ ይህም የደፈሩ ናቸው የሚናገሩት እጭ ፖለቲካ ነው።





 
 
በዚህ ልክ የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ ካያችሁት ተስፋችን ይርቃል። አቅምን በቅጡ ለማስተዳደር ይሳነናል እያልኩ አስተምሬያለሁ። ተናግሬያለሁ። ከእኛ ቤት ከሊቅ እስከ ደቂቅ ብዙ ሰው አለ። ነገር ግን ፋክቱን ደፍሮ የሞገተ የለም። አሁን አቶ ሌንጮ ለታ ወጥተው ይህ የኦሮሞ መንግሥት በኢትዮጵያ ታሪክ ዴሞክራሲን ዕውን ካደረገ፤ ባህሉ ከሆነ ማህበረሰብ የወጣ እያሉ እንኳን ሥልጣን ላይ ያለው እንኳንስ የኦሮሞ ፖለቲካ የኦሮሞ ኢሊትም ስልጣን ላይ አለ ማለት አይቻልም የሚሉ ኢትዮጵያዊ ፖለቲከኞችን እያዳመጥኩ ነው። እኔ በታህሳስ 2019 አሁን ሥልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት እንኳንስ ለኢትዮጵያ ለአፍሪካ ያሰጋል በሚል የፃፍኩትን ደጉ ሳተናው ድህረ ገጽ ሼር አድርጎት እስከ 400 ወገኖች "አዛምተውታል።"
 
የሆነ ሆኖ ዕውነት እና ንጋት እንዲሉ ቀድሜ አያይዙን አይቼ የተናገርኳቸው ፋክቶች ሁሉ ዕውን እዬሆነ ነው። ለመሆኑ ኦሮምያ ስለ በዓሉ መግለጫ ሲያወጣ እንደ ብሄራዊ መንግሥት ለምን ሆነ ብላችሁም አልጠዬቃችሁም። አዲስ አበባ ያሉ ተቋማት ሁሉ በኦሮምያ ሥር ናቸው ሰላማዊ ሰልፋ የሚከለከለው በእነሱ ፈቃድ አለመስጠት ነው ሲባል አልተግባብቶም ነበር። ይኽው አይኑን አፍጦ መጥቷል። በደነደነ ጉልበት በጦር በታገዘ ማንአህሎኝነት። አዲስ አበቤን ማግለል፤ መጫን፤፦ባይታዋር ማድረግ ማስደረግ። ለአዲስ አበቤ ሲፈናቀል ቤት የሚያከራይ በገንዘብም በእስራትም ይቀጣል። ኢትዮጵያ በኦነግወገዳወኦዳ ሃይጃክ ተደርጋለች የምለውም ለዚያ ነው። ግን የማያልፍ የሚመስለው ሁሉ ያልፋል። አይዟችሁ። 
 
አስምሌሽኑ ሆነ ዲስክርምኔሽኑ በአዲስ አበባ ላይ የበረታ ነው። ይህን ታግሎ ለማሸነፍ በሳል ፖለቲካ ይሻል። የአደመጠ ያልወደቀ። ኢትዮጵያ በገበርዲን እና በከረባት ፖለቲከኞች ብቻ አትፈወስም። 
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
06/10/2023

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።