#ስሜናዊነቴ ህወሃትን ቤቴ ለማለት ከሆነ በአፍንጫዬ ይውጣ።
#ስሜናዊነቴ ህወሃትን ቤቴ ለማለት ከሆነ በአፍንጫዬ ይውጣ። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #ምዕራፍ ፲፰። #እፍታ ለአፍታ። አወን እርግጥ ነው በአባቴም በእናቴም ስሜናዊ ነኝ። ስሜናዊነቴ አንዱ ማንነቴ ነው። ግን ያን ጊዜ የማይስተምረውን የጭካኔ አስኳል ጋር ለሠርግ - መልስ፤ ለቅልቅል እና ለግጥግጥ ከሆነ ስሜናዊነቴ በአፍንጫዬ ይውጣ። የሚገርመኝ የጽጥምዶ ባላንበራሶች ዛሬ ደርሰው የወልቃይት፤ የጠገዴ፤ የአዲረመጥ፤ የአዳርቃይ፤ የጠለምት፤ የራያ ተቆርቋሪ ሆነው መምጣታቸው ነው። እንደ ሽንብራ ቂጣ መገላበጡ የእውነትን ልክ #ሊከልሰው ፈጽሞ አይችልም። ዛሬም ህወሃት ከዛ #ከታቆረ ሃሳቡ ፈቀቅ ሊል ያልቻለ፤ ድውይ ድርጅት መሆኑ ዓለምም እያዬው ነው። ኡኡታው፤ ለማሳጣት ከፍ ዝቅ ማለቱ፤ መሸነፋን ለመቀበል አቅል አጥቶ መክለፍለፋ ዘመን ሊያስተምረው አልቻለም። እንጂማ ቢገባው የእሱ አንቱነት ከግንቦት መግቢያ 2023 ጀምሮ ማክተሙን አላወቀም። #ለማንኛውም ሰብ ይሁን ተቋም እኔ የምለው …… 1) መውደቅን መቀበል ብልህነት ነው። መሸነፍን መቀበል ብልህነት ነው። ምክንያቱም በመውደቅ ውስጥ መነሳት፤ በመሸነፍ #ከርስ ውስጥ ማሸነፍም ስለሚቻል። መሸነፍ ብቻውን አይቆምም። የሙሉ ዕድሜ ተመክሮ መግቦ ነው። በመሸነፍ ውስጥ እራስን የማየት አጋጣሚ ይገኛል። መሸነፍን ለሚቀበል። ዕውቅናም ለሚሰጥ። ይህ ሲሆን በመሸነፍ ውስጥ ዳግም ጥፋትን ላለማጨት ህሊናን ያሰናዳል። 2) መውደቅም ቢሆን ከብዙ ኪሳራ ጋር ቢሆንም፤ እራስን ከወደቁበት ረግረግ ለማውጣት የጥሞና፤ የተደሞ ጊዜ ቢሰጠው በአዲስ አቅም፤ በእሸት ጉልበት አገግሞ ቀና ማለት ይቻላል። ግን ...