ልጥፎች

ፍቅር #ተፈጥሮ #ግሎባል #የትምህርት #ካሪክለም #ሊነደፍለት ይገባል።

ምስል
ፍቅር #ተፈጥሮ #ግሎባል #የትምህርት #ካሪክለም #ሊነደፍለት ይገባል።   "የደጋግ ሰወች ልጆች ስሙኝ በረድኤት ታደሱ፤ አበባ በምድረ በዳ ጠል እንዲያብብ እንደሱ አብቡ። (በረድኤት ታደሱ) ዬሽቶ ማዕዛ ደስ እንደሚያሰኝ ማዓዛ ትምህርታችሁ እንደዚያ ደስ የሚያሰኝ ይሁን።"   አሜን ብዬ ልጀምር።   ፍቅር ተፈጥሮው ጥልቅ ነው። የዛሬ 7 ዓመት አንድ የጀርመን አውሮፕላን አብራሪ ፈቅዶ ከተራራ ጋር አውሮፕላን አጋጭቶ እሱን ጨምሮ ወደ 150 ሰወች አጠፋ። ፈጀ። 15 ቀን CNN ዘገበው። ሬሳው ከአውሮፕላን ላይ ሰው ተንጠልጥሎ ለቀመው። እጅግ አሰቃቂ ነበር። መተኛት መመገብ አቃተኝ። ከዛ የሰውልጅ ክፋነትን ከምን አመጣው የሚል ምርምር ቤቴን ዘግቼ ሰራሁኝ። ከማህፀን እና ከአብራክ አለመሆኑን ተረዳሁ። ዬሰው ልጅ ሲፈጠር ንፁህ ሆኖ መፈጠሩን ለራሴ ሙግት መልስ አገኜሁ። ሁለተኛ ደረጃ አቅጣጫዬ ዬሰው ልጅ ከአብራክም ከማህፀንም ክፋትን ካልተማረ ከዬት ዬሚለው ሆነ ፍለጋዬ። መልሱ ከቤተሰብ፤ ከማህበረሰብ ዬሚል ሆነ። ለምን ዬሚለውን ሦስተኛው ጉዞዬ አንድ ጭብጥን ሸለመኝ። ዬሰው ልጅ ሲፈጠር ሙሉ ሆኖ ሲኖር አንገቱ ተቆርጦ። ማዘዣ ጣቢያ አልባ። መኖር በዓለም አቀፍ ደረጃ ሞተር ዓልባ። ፕላኔታችን አሳሰበችኝ። ነገ አስጨነቀኝ። ምክንያቱ ቀላል ግን ትኩረት ያላገኜ። ለክፋ ነገር ማርከሻ አልተሰራለትም። ክፋ ነገር ካለ ዬሚመክት ዬደግነት ትምህርት ቤት ሊኖር ይገባ ነበር። ያ ደግሞ ዬፍቅር ተፈጥር ካሪክለም ተሠርቶለት በመደበኛ ዬዓለም ዜጋ መማር አልቻለም። ዬፍቅር ተፈጥሮ ኮሌጅ፤ ዩንቨርስቲ፤ ኤክስፐርት፤ ሳይንቲስት፤ ፈላስፋ፤ ሙዚዬሣ።ም፤ ሚዲያ፤ መጋዚን፤ ግሎባል ቀን፤ ዬመንገድ ትርዒት ዬለውም። ዓለም በዘመኗ በፍቅር ተፈጥሮ ህግጋት ላይ አጀንዳ ቀር...

አሉታዊው ስስት እና ገፈፋ ጠንቅ ነው። ድዌም። ፖርሳ ዬሰከነ መስከንን በእጃችን እንሥራው።

ምስል
  አሉታዊው ስስት እና ገፈፋ ጠንቅ ነው። ድዌም። #ፖርሳ ዬሰከነ መስከንን በእጃችን እንሥራው። ስስት ሰፊ ትርጉም አለው። እኔ አሉታዊ ስስት ላይ ነው ማተኮር እምሻው። "ለመብል ሁሉ አትሰስት ላዬኽውም እህል ሁሉ አትሰስት፤ ብዙ መብላት ደዌ ይሆናልና ስስትም ጓታን ያበዛዋል እና አትሰስት፤ ስስት የገደላቸው ሰወች ብዙ ናቸው፤ መጥኖ ዬሚበላ ግንሰውነቱ ጤና ነው።"     ስስታም ዓይኑ ጠባብ ነው። ይቅበዘበዛል። ጎላ ብሎ በወጣው ላይ አንቴናውን ይዘረጋል። የእህል ስስት ለቁንጣን ይዳርጋል። የሥልጣን ስስት ደግሞ ለፋሺዝም። ስስት የህሊና ቀውስም ያስከትላል። ቀውሱ #ማናንሼ እለዋለሁኝ እኔው። የማንነት ቀውስ ያለበት ሰብዕና ውስጡ ሰላም የለውም። ይናደፋል። ይቦጭራል። ሁልጊዜ ግስላ፤ አራስ ነበር ነው። ሥልጣን ኖረውም አልኖረው ቅምጥ ፍላጎቱን ለማስቀጥል ሩጫው አጋጣሚውን በመጠቀም ይሆናል። አድብቶ ይጠብቃል። ብቅ ብሎ ይሰወራል። አረሳስቶም ጠቀራውን ያንዶለዱለዋል። እሳቱን ጫጭሮም ዞር ይላል። ገባ ወጣ ነው። ለምዱ እስቲገለጥ። አክ እስኪባል። መነገጃው ግን ያው የፈረደበት ኢትዮጵያዊነት ነው። እያከሰለ በምራቁ ቀለም ቀቢነት ያጎሳቁለዋል። እርግጥ ጠንቀኛውን ዬአንድ ለአንድ አጋበስባሽ ስስቱን አምቀው የያዙ ጊዜ ራዲዮሎጂ ሆኖ እስኪያጋልጣቸው ብዙ ማገዶ ይጠይቃል። ሰብዕናቸው #ግራጫ #በሲቃ ነው። አካሄዳቸው #ተርገብጋቢ እና #ገርበብ ያለ ነው። አልፎ አልፎ ፍንጭ ቢሰጡም ለሰከኑ ዬሰብዕና አጥኝወች ካልሆነ በስተቀር ተሎ ለማዬት ያስቸግራሉ። የሆነ ሆኖ አቅም፤ አቅል፤ ብቃት፤ ታሪክ ላለው ማህበረሰብ ስስታም ግለሰቦችም፤ ስስታም ተቋማትም የትውልድ ጠንቅ ናቸው። ካንፓቸው እና ካንፓሳቸው #ጥላቻ ነው። ምርታቸው ዲዲቲ ነው። ከሚጠሉት ዘለግ ...

የመኖሬ ወይንም የህወቴ ፍልስፍና በጥቂቱ።

ምስል
ዕለተ ሮቡ ዕለተ ማዕዶተ ተናኜ በከበቡሽ ቁራሽ እንጀራ በቢሆነኝ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „የሚያስፈልገኝን እንጀራ ስጠኝ እንዳልጠግብ፣ እንዳልከዳህም“ (ምሳሌ 30 ቁጥር    • ዕፍታ። ዕለተ ማዕዶተ ተናኜ ፈንገጥ ያሉ ዕይታዎቼ የሚቀርቡበት ነው። የሃሳብ ቀን። • የመኖሬ ወይንም የህወቴ ፍልስፍና በጥቂቱ። የህይወት ፍኖተ ካርታ ልንለው እንችላለን። ህይወቴን እምመራበት በርካታ መርሆዎች አሉኝ። ዝርግነት አልወድም። ዝርግ ሰውም ክፍሌ አይደለም። ልሙጥነትም ተጠግቶኝ አያውቅም። ጠፍጣፋነትንም እጠዬፋለሁኝ። ውራጅ ሰብዕና የለኝም። ራሴን ተውሼም አልኖርኩም። ልብ እንዲገጠምልኝ አልፈቅድም፤ ምን እንዳለኝ፤ ምን እንደምችል፤ ምን እንደሚፈቀደልኝ፤ ምን ደግሞ እንደማይፈቀደልኝ ጠንቅቄ አውቃለሁኝ። በሚገባ። እራሴ ተቋም ነኝ። ዝንቅ ያልሆነ ወጥ አሻራም አለኝ። (1) መኖር ነፃነት ሊኖረው ይገባል ብዬ አምናለሁኝ። (2) ለነፃነቱ ደግሞ መታመን። (3) ለመታመኑ ተፈጥሯዊነት። (4) ለተፈጥሯዊነቱ ጥሩ አስተዳዳሪነት። (5) ለጥሩ አስተዳዳሪነቱ ጥሩ አድማጭነት። (6) ለጥሩ አድማጭነት ጥሩ ዕውቅና። (7) ለዕውቅናው ውስጥን ሳይሰስቱ ወይንም ሳይነፍጉ መስጠትን። ( መስጠትን በተሰጠው ልክ ሚዛኑን አስጠብቆ እራሰን ሳይሸሹ ወይንም ከራስ ጋር ድብብቆሽ ሳይጫወቱ። 1) በቅድሚያ ስለ ነፃነት። ነፃነት ነፃነትን ይፈልጋል። ለነፃነት ነፃነት መስጠት የባለቤቱ ጉዳይ ነው። ለምሳሌ አድዋ ግሎባል የነፃነት ክስተት ነው። አድዋ የነፃነት ክስተት ሆኖ ግን ነፃነቱን ተቀምቶ በኦዳ ሥርዕዎ መንግሥት ዘንድሮ አስተውለናል። ስለዚህ የዓድዋ ነፃነት ለራሱ ነፃነት አልበቃም ማለት ነው። ስለምን? አድዋ ክስተት እንጂ ሰው ስላልሆነ። ስለዚህም አድዋ ነፃነ...

ህይወት እራሷ ጥያቄ እና መልስ ናት። ትጠይቃለች ወይ ትምለሳለች።

ምስል
  ዕለተ ሮቡ ዕለተ ማዕዶተ ተናኜ በከበቡሽ ቁራሽ እንጀራ በቢሆነኝ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „ሰነፍ ሰው ቁጣውን ያወጣዋል ጠቢብ ግን በውስጡ ያስቀረዋል።“ (ምሳሌ 29 ቁጥር 14)     ዕለተ ማዕዶተ ተናኜ ፈንገጥ ያሉ ዕይታዎቼ የሚቀርቡበት ነው። የሃሳብ ቀን። ከዚህ ቀደም የሠራኋቸው ያደሩ ጉዳዮችን በቋሚነት በዬዕለቱ የምሠራባቸው ዘርፎችን ነው። አሁን ወደ መደበኛው ተግባር።፡ ዛሬ አንድ የራሴ የሆነ ነገር ላቀርብ ፈለግሁኝ። ምን ስለምን? ህይወት የጥያቄ እና የመልስ ጭማቂ ናት በእኔ ፍልስፍና። ህይወት እራሷ ጥያቄ እና መልስ ናት። ትጠይቃለች ወይ ትምለሳለች። ህይወት ኑሯዋ ጥያቄና መልስ ነው። ኑሯዋ ብቻ ሳይሆን የመኖሯ ዛይቢያ መተንፈሻ ቧንቧዋ ጥያቄ እና መልሰ ነው። ኦክስጅኗ። እህል አብስሎ ለመብላት እሳት፤ ፈጭቶ ለመብላት ወፍጮ፤ ለመጓጓዝ የየብስ - የሰማይ እና የባቡር መጓጓዣ። እህል ለማምረት ማረስ - መዝራት - ማረም - ማብቀል - ማጨድ - መከመር፤ መውቃት - በመንሹ መለዬት። ከዛ ማስቀመጫሳ? ሲባል እንደ አካባቢው ሁኔታ ዕቃ እንዲህ እንዲህ እያለ አቤቱ ህይወት ለራሱ እራሱን እዬጠዬቀ ኑሮውን የሚያቃልል መሳሪያ ፈለሰመ። ፍልስፍናው ምንጩ ህይወት የሚያቀርበውን ጥያቄ ለመመለስ ነው። እኛ የምንወድቀው ወይንም አልሆነ ቦታ እምንቀረቅረው የህይወትን ጥያቄ መመለስ ሲሳነን ወይንም ስንዘለው ነው። መጀመሪያ የራሳቸውን የመኖር ጥያቄ የመለሱ ሰዎች ደልዳላ መኖር ይኖራቸዋል። ለምን እሰደዳለሁኝ? ለማን እሰደዳለሁኝ? እንዴትስ ተሰደድኩ? ስሰደድ ምን ላተርፍ ምን ልከሰር? ብከስር አማራጭ የህይወት መስመሬ ምን ይሆናል? ከጥቂቶች በስተቀር ያልመለሰነው ጥያቄ ውስጥ ተዘፍቀን ህይወት እና እኛ አራባ እና ቆቦ። ብንማረው፤ ...

እመት ውርጭ

ምስል
ዕለተ ሮብ ማዕዶተ ተናኜ በከበቡሽ ዬቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ።   "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯) እመት ውርጭ ኢትዮጵያዊነትን አትፍጪ! ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17/03/2021 አረንዛነት የትውልድ ዕዳ ነው። ዕዳ ከሜዳ ስለከበከብን አብረን እንፈር!  

#ህፃናትን ወደ እርጅና የቀዬረ ገመናዊ ዘመን። ሎቱ!

ምስል
#ህፃናትን ወደ እርጅና የቀዬረ ገመናዊ ዘመን። ሎቱ! የለጠፍኩት ፎቶ ይነበብ። አደራ።      #በዚህ ውስጥ አለን ወይንስ የለንም? ከእኛ እዬነጋ ነው እንዴት አደርሽ እናት ዓለም ጦቢያ? አንችንም ሥምሽን ለመቀዬር የገዳ ኢንፓዬር እያደባ ነው። የማይበወዝ፣ የማይቀረፍ፣ የማይሰነጠቅ፣ የማይዘረፍ፣ የማይናወጥ ምን ነገር ሲኖር ገዳ እና ጽልመት ተፈጥሯዊ ናቸውና። የአናርኪዚም መናህሬያ ቀውስ ባጀቱ እራቱ። ማህበረ ቅንነት እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? አባ ቅንዬ አቶ ሰለሞን ኃይሌን አላዬሁም። ዕልፍኛችን ብርድ ብርድ ይለዋል፣ እሳቸው ከሌሉ። ባሉበት ደህና ታድርግልን ድንግልዬ። አሜን። ነገረ ድርቅ ጉጂ፣ ሱማሌ፣ ነገሌ ቦረና፣ ዋግ ህምራ እንደምን እዬሆኑ ይሆን? ዋግ ህምራ? በግራ በቅኝ እዬተቀጠቀጠ ነው። #አፋር እና አማራ ትንፋሻቸው እንዴት እዬሆነ ነው። አዲስ አበባ ዩንቨርስቲም ቁንጣን ያላስቻላቸው እያተራመሱት ነው። ማን ይሆን ተባራሪው? ግን እናንተስ የገዳወኦዳ ኢንፓዬር የወሩራ ጽንፍ እንዴት ይኳችኋል? አስምሌሽኑ፣ ዲስክርምኔሹን ገና ጫፍጫፋን ነው። ወደ ዋናው ምዕራፍ አልተገባም። ጥናት መቀነቱን ለሁላችን ይስጠን አሜን። ግን የትኛው የፖለቲካ አቅም ይህን ሁለገብ የገዳኦዳ ወረራ፣ መስፋፋት፣ አስምሌሽን፣ ዲስክርምኔሽን መቋቋም ይችለው ይሆን? በብትን ትርትር ጉዞ? #መጥኔ ለኢትዮጵያ! #መጥኔ በዬዘመኑ ዕድሜውን በግፍ ለሚነጠቅ የአገሬ ወጣት፣ #መጥኔ ለእኛ ዘመን ለዘመን ከውድቀት ወደ ውድቀት ለሚንከባለለው ፖለቲካ አብረን ለምንዳክር። አይዞን። ፈጣሪ ብቻ እንማጠነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17/03/2022 እንበርታ! አንዛል! ህፃናትን ወደ እርጅና የቀዬረ ገመና!  

#ኮፒ ራይት የማይጠዬቅበት የተጋድሎ ዘርፍ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ብቻ ነው።

ምስል
  #ኮፒ ራይት የማይጠዬቅበት የተጋድሎ ዘርፍ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ብቻ ነው።     በሌላው ቤት ካለ ቤተኞቹ ማንም ዘውታ የለበትም። የአማራ ፖለቲካ ሁነኛ ባለቤት ስለለው ያገኜ ሲዳክርበት ውሎ ያድራል። #በሩ 24 ክፍት ነው። የአማራ #የትርታ ተጋድሎ በወጠነው ሁሉ ሁሉ አራጊ ፈጣሪ፣ አዛዥ ነዛዥ ነው። ግንስ አንዳቸውም ከሞት መታደግ፣ ከመፈናቀል ማስቆም፣ ከመታረድ መታደግ አልተቻለም። የ40 ዓመቱ መከራ በአራት እጥፍ ተመንድጓል። ዘመናት መሠረት የያዙ ማናቸውም ትውፊት እና ትሩፋት አይሆኑ ሆኖ ከስሏል። በዚህ ለመቀጠልም አልተፈቀደለም። የመስተዳድሩ ፕሬዚዳንት ዶር አብይ አህመድ በአዳዲስ ቀውሶች #የሚያርሱት አልበቃ ብሎ ሌላውም ተደርቦ ጥልቅ እያለ መከራውን በእጥፍ ድርብ ያነባብረዋል። ትናንት ልዩ ኃይል ነበር ዛሬ #ፋኖዊነት ። ነገ ደግሞ #ማናዊነት ይመጣ ይሆን? ሁሉም ነኝ ይላል። ተግባር ላይ ያሉት ደግሞ ድምጣቸውን አጥፍተው ይተጋሉ። ሌላውወይ ሲወድቅ፣ ወይ ማህበራዊ መሰረቱ ሲሳሳ ሄዶ ይዶላል። እናም ዕዳ ከሜዳ ሆኖ ጠንቅ ሆኖ እንደ አርበኛ አስቻለው ደምሴ አደናው፣ እርሸናው፣ እስሩ እንግልቱ ቀጥሏል። ከፋኖ እራስ መውረድ ያለበት ሁሉም ነው። ከሊቅ እስከ ደቂቅ። ፋኖ የዛሬው የፖለቲካ ድርጅት ሳይፈጠር የነበረ #የደም #ማህተም ነው። ሰው ሠራሽ አይደለም። አላያችሁም ጎንደር ሀምሌ 5/ 2008 አብዮት ሲፈነዳ እነ ዋዋ አርበኛ ጎቤ ያን የመሰለ የተደላደለ ኑሯቸውን ትተው ሲደርሱለት። ያንጊዜ "ኢዜማ፣ ባልደራስ፣ አብን፣ "ብልፅግና፣" ህብር ወይንም ኢኃን" ነበሩን? አሁን እነሆ ከፖለቲካ ድርጅት ጋር ወስደው ዘፍቀው ተው እያልኩ እዬተናገርኩኝ በግራ በቀኝ እዬታደነ ይገኛል። አዝናለሁኝ። እጅግ አድር...

ይህቺ ቀን #የተናደች ዕለት እርስወን አያርገኝ።

ምስል
  ይህቺ ቀን #የተናደች ዕለት እርስወን አያርገኝ።   የምጠብቀው የችሎትን ካባ ለብሰው ሰበር ችሎት ላይ ተሰይመው ደግሞ ማዬትን¡¿¿ #አሳቻው እና ሁለገብ ትትርናቸው። #የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚር፣ #ፕሬዚዳንት ,የኦዳገዳ የአስምሌሽን "ብልፅግና" #የጦርኃይሎችጠቅላይ አዛዥ፣ #የፓርክ አለቃ፣ #የደን ልማት ካፒቴን፣ #የአበባ ማምረቻ ድርጅት ተንከባካቢ ኤጀንሲ፣ #የኢቤንት ማናጀር፣ #የጓሮ አትክልት ሙያተኛ #የሆሚኮኖሚክስ ተመራቂ ሰላጣ እና ባቄላ¡¡¿ #የመብራት ኃይል ዳንሰኛ ኃላፊ ምን ቀረ? እ #የኮትስትራክሽንኃላፊ ፣ #የአማራ ክልል መስተዳድር ***ፕሬዚዳንት፣ #የስብከት ጠበብት፣ #የዕቃ ግምጃ ቤት ኃላፊ፣ #መሐንዲስ ፣ ጫማ ጠረጋዋንም ተሻምተውታል፣ ዘይት ማከፋፈሉንም እንዲሁ። ያልሰነበተው #ጽዳተኝነትንም …… አንድ ሰሞን አስኮባ ተሸክመው ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ ነበር። ዶር አብይ አህመድ አሊ እርስወ አቅደው፣ አደራጅተው፣ በመሩት የ90 ደቂቃ የባህርዳር እና የአዲስ አበባ ሰማዕታት የሽብር ናዳ እርስወ #በዕድሜ ልክ እስራት ሊቀጡ ሲገባ እነኝህን መከረኞች ፈረዱባቸው አይደል? #በእዮር አደባባይ እርስወን ቅዱስ አምላክ ማን ብሎ ይጠራወት ይሆን? #ከደቂቃኑ ከባከኑት፣ ከወደቁት መላዕክታን ዘር ይሆኑ? ቅጣተውት ከሰማዬ ሰማያት በላይ ሆነ? በእርስወ ጥፋት ሌላው ይቀጣል፣ ይገደለላል፣ ይዋረዳል፣ ቤተሰቡ ፍዳውን ያያያል። ለእርስወ ስልጣን ሲባል። መኖር ከስሎ፣ መንኖ ይገኛል እስከ የት ይሆን ጉዞወት? መጨረሻወትን ያዬ ሰው? እነኝህን መከረኞች በእርሰው የሽብር በጀት ተጠያቂ ሊሆኑ አይገባም። ዶር አንባቸውን የገደሉት ለሰሞኑ እራስወት እሩጠው እራሰወን ላስቀመጡበት ቦታ የሚበልጥ ሲነሪትም፣ ክህሎትም፣ ተቀባይነትም ሰልለው ስለ...