ስለምን ኃላፊተት እና ተጠያቂነት የሚሰማው ትውልድ ማብቀል ተሳነን?
ስለምን ኃላፊተት እና ተጠያቂነት የሚሰማው ትውልድ ማብቀል ተሳነን? "በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀምጠን ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን። (መዝሙር ፻፴፯ ቁ ፩) እንዴት አደራችሁልኝ ማህበረ ክቡራን እና ክቡራት? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ አምላኬን ተስፋ አድርጌ ደህና ነኝ። ሰሞናቱ እንደ ደመናም፤ እንደ ወጀብም፤ እንደ ዝናብም ይቃጠዋል በቅድስቷ በዕቴ በቪንተርቱር ከተማ። ማሰብ። ማሰብ። ማሰብ። እያሰብኩ ሃሳብን አስበዋለሁኝ። ስለምን ኃላፊነት እና ተጠያቂነት የሚሰማው ትውልድ ማፍራት ተሳነን? እኛም ሆን የቀደሙት ስለምን መዝራትን ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ ከማብቀል፤ ተጠንቅቆ ከማሳደግ ጋር ምኑ አፋተን? #በኃላፊነት እና በተጠያቂነት መሐል ጉልቻው ከፈረሰ ቆዬ። ግን ለምን? #አደራ ምንድን ነው? #ትውፊትስ ምንድን ነው? #ትሩፋትስ ምንድን ነው? #ቅርስ ውርስስ ምንድን ነው? #ታሪክስ ምንድን ነው? #ባህልስ ምንድን ነው? #ወግ - ልማድስ ምንድን ነው? ግን ምንድን ነው እራሱ #ምንድን ነው? መልስ ይሻል? እንጀራን እዬበሉ እንጀራ የተፈጠረበትን ሥልጣኔ ማብጠልጠል? አማርኛ ቋንቋን እዬተናገሩ አማርኛ ቋንቋን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት መፍጨርጨር? ሰንደቅ ዓላማው ባስገኜው የነፃነት ትንግርተ ቤተ - መንግሥት ተቀምጦ ሰንደቅ ዓላማን መፎካከር? ግን ምንድን ነው? እራሱ ምንድን ነው ምንድን ነው? ኢትዮጵያ በሚለው ሙሉ አቅም ባለው ኃይለ ሚስጢር ለሥልጣን ተበቅቶ፤ ለሽልማት ተበቅቶ፤ ለክብር ለዝና ተበቅቶ አዬር ላይ ተንሳፎ በቅሎ ዙፋን የተጨበጠ ይመስል "የራሴ ጥረት ስኬት" እያሉ መጎረር በማጓራት መጯጯኽ ምንድን ነው? ግን እራሱ ምንድን ነው ምንድን ነው? የተሰደደውም ኢትዮጵያ በሚል ኃይ...