Julay 12/ 2021

 

ከአራት ወር በፊት አዲስ አበባ በዝምታ ምርጫዋን አጠናቀቀች ብዬ ጽፌ ነበር። ያልኩት አልሆነም። የአጣዬ መቃጠል ለዛ ድል ነበር። ስጋት ሽብር ለማህበረ ኦነግ የድል ርካብ ነው። መከራውን በልኩ መረዳት ይጠይቃል። እኛ ገና ለብም አላልነም።
"ተረኝነት" የሚሉ ፖለቲከኞች የገዳን ወረራ፣ የገዳን አስምሌሽን፣ የገዳን መስፋፋት ሲያቆላምጡት ባጅተዋል። የትግራይ እና የፌድራሉ ጦርነት የገብር አልገብርም መሆኑንም በጥዋቱ ገልጫለሁ። የኔታ ጎዳና ያዕቆብም ቆፍጠን ባለ አማርኛ ትግራይን የማበልፀግ ጦርነት ሲሉ ዕይታቸውን አጋርተዋል።

 
ከሰሞናቱ አጤ አብይ ደግሞ ብልፅግናን ቢቀላቀሉ ይህ አይሆንም ነበር ሲሉ ውስጥ ዕቃውን የሂደቱን ዘረጋግፈውታል።
አያችሁ መደማመጥ ቢኖር ያለ አቅም የምናፈሰውን አቅም አደራጅተን በሃሳብ የመሞገት፣ የማደራጀት ተቋማዊ ትግል መጀመር ይቻል ነበር።
እኔ በግል ካልሆነ በድርጅት ደረጃ ከአጤ አብይ መዳፍ ውጪ የሆነ ድርጅት ስል ባጅቻለሁ። የሆነው የግርዶሽ ማርገጃ ነው። ለዕውቅናው በስውርም በግልፅ ተሆነ።
መጪው ጊዜ ከባጀው ይከብዳል። ውኃ ያዘለ ተራራ ነው። በተለይ ለአማራ። የሆቴል እዬተከፈላቸው ከአውስትራልያ፣ ከስሜን አሜሪካ፣ ከአውሮፓ ሽርሽር ላይ የባጁት የሞጋሳ ምርኮኞች ከእንግዲህ አፍንጫህን ላስን ይጠብቁ።
እንደ አሮጌ አካፋ እና ዶማ ይወረወራሉ። የጨበራ ተዝክሩ በኦነግ አሸናፊነት ተደምድሟል። ስልቡም ተሰልቦም፣ ተሰልስሎም ደመነፍሱን ይወዛወዛል።
አዲስዬም አዲሱን ዘመናዊ የሉባውያን መረገጥን ታሽሞንሙን። የገዳዋ የምርጫ ቦርድ ልዕልትም ከአማካሪዋ ጋር ደረብ ካለ የዶላር ጉርሻ ጋር መፎረሽ ነው። ድል በድል¡ ኢትዮጵያን ክዶ ኦሮማይዜሽን ነገሰ።
አቶ ያሬድ ጥበቡ ከኤርትራዊው ጋዜጠኛ ከአቶ ሰናይ ጋር በነበራቸው ቆይታ ቦንብ የሆነ መረጃ ዱብ ሲልላቸው ግራ ገብቷቸው ነበር።
ጋዜጠኛው ኤርትራ ውስጥ ከነበሩት የታጣቂ ኃይሎች በተለዬ የሻብያ ከፍተኛ አካላት ኦነጋውያንን ሰብስበው የኢትዮጵያን አፈ ታሪክ መደርመሴ ከተቻል አፍሪካዊ ልዕልና ለማምጣት ከጣራችሁ ከእናንተ ጋር እንሠራለን ሲሉ ሰምቻለሁ።
ሰሞኑን ዶር አብይ አህመድ ጅማ ላይ በአፍሪካ ትልቅ እንሆናለን ሲሉ ከማውቀው ዕውነት ጋር ተመሳሰለብኝ በዚህ ላይ ምን አስተያዬት አለወት ሲል ነበር አቶ ያሬድ ጥበቡን የጠዬቃቸው። እሳቸው ጉዳዩ አዲስ እንደሆነባቸው በመግለፅ ምንም ሳይሉ ነው የቀሩ። ጊዜ የሚያስፈልገው መረጃ ነውና።
አንድም ቀን ዶር አብይ አህመድ ኤርትራ ሲጓዙ የአማራ ሊቃናትን ይዘው ሄደው አያውቁም። ለምን? ይህን ለረጅም ጊዜ ፅፌበታለሁኝ። ዕንቆቅልሹ የተፈታልኝ ግን ጋዜጠኛ ሰናይ ካወጣው ሚስጢራዊ ቦንብ መረጃ ነው።
ሩጫው ከሥር አልተነሳም። ለዚህ ነው ነገ ከብዶ የሚታዬኝ። ኢትዮጵያን በነበረ መክሊቷ የማግኜት ሁኔታ ቀኑ እያለቀ ነው። አዲስ አበባ ምርኮኛ ሆናለች። የአቶ እስክንድር ድካምም ተጠለፈ። እና ለሽታ አሰኜው። ምዕራፋ ተከረቸመ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
12/07/2021
እኛ የት ነን?
እነሱስ የትኛው እርካብ ላይ ናቸው?

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።