አቅምህ ለህልውና ተጋድሎህ ብቻ ይሁን።

 

አቅምህ ለህልውና ተጋድሎህ ብቻ ይሁን።
 

አማራዊ ማንነት፣ አማራዊ የተፈጥሮ ኃብት፣ አማራዊ ትውፊት፣ አማራዊ ትሩፋት የህልውና ተጋድሎ ላይ ናቸው።
ጋሞዊ ማንነት፣ ጋሟዊ ትውፊት፣ ጋሟዊ ትሩፋት፣ ጋሟዊ ታሪክ የህልውና አደጋ ላይ ናቸው።
ጌዴኦዊ ማንነት፣ ጌዴዋዊ ትውፊት ታሪክ ተመክሮም የህልውና ተጋድሎ ላይ ናቸው።
ጉራጌያዊ ማንነት፣ ትውፊት፣ ትሩፋት፣ መክሊትም የህልውና ችግር ላይ ናቸው፣
ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ልሙጡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቁም መራራ መከራ ላይ ናቸው፣
የኔታዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ህልውና በከፋ እንቆቋዊ ጥቁር ዘመን ላይ ትገኛለች፣
አዲስ አበቤ በጣሊያን ጊዜ ከነበረው እጅግ በከፋ ጭቆና እና ስቃይ ላይ ይገኛል፣
ደቡብ ለወራሪው እና ለተስፋፊው ኦሮሙማ መቋደሻነት በቅርጫ መሰናዶ ላይ ነው የሚገኜው፣
አዬሩ በመንግሥት በተደራጀ ሽብር፣ ቀውስ፣ ስጋት ላይ ነው ያለው፣ ሁለመናው ኩፍትርትር ያለ ነው።
በዚህ ማህል ኮሮና ከአጀንዳ ውጪ ሆኗል። ኢትዮጵያ የኮሮና በሽታ አደጋ ዕውቅናው እዬተጣሰ ነው። መኖርን የሚቀሙ የሜንጫ፣ የጉጠት፣ የመጥረቢያ፣ የካራ ኮሮናዎች ድል ላይ ናቸው። ደምን እዬተጎነጩ ፌስታ ላይ ናቸው።
ኢትዮጵያ ምጣት ላይ ናት። ይህም ሆኖ ህሊናቸው የተሰወረ ወይንም የተደገመባቸው ፋሺስታዊው የጭካኔ ሥርዓት ይቀጥል ዘንድ ጉዝጓዝ በማንጠፍ ላይ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ በዝንጉዎች ህብረት ልታመልጥ ትችላለች።
እርኃቡን፣ ወረርሽኙን፣ የተፈጥሮ አደጋውን፣ አንበጣውን፣ ኮሌራውን፣ ፈንጣጣውን፣ የውጭ ግንኙነቱን ስታስቡት ትንፋሽ ያጥራችኋል።
ኢትዮጵያ እራሷንም ለማኖር ጋዳ ሆኖባታል። ጭንቅ ላይ ናት። ህማማት ላይ ናት። አምጣችሁ አትወልዷት ነገር አቅም የለም። ምን ይሻላል?
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
በቃን የገዳ ሥርዓት!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።