የምዕት #የደግነትወሰባዕዊነት ጉልላት ኢትዮጵያዊው ቅዱስ እዮብ እና የመልዕክቱ ሙሴነት።
የምዕት #የደግነትወሰባዕዊነት ጉልላት ኢትዮጵያዊው ቅዱስ እዮብ እና የመልዕክቱ ሙሴነት።
"የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤
እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያሳካለታል።"
ማህበረ ቅንነት የኔወቹ እንዴት አደራችሁልኝ? ደህና ናችሁ ወይ? ልዕልት ኢትዮጵያስ ከቶ እንዴት እዬሆንሽልኝ ነው። ትናንት ስባትል ስለዋልኩኝ ዛሬ ነው ያዳመጥኩት ንግግሩን። ትህትና ዕውን በዕውን ቁሞ ሐዋርያ የሆነበት አጋጣሚ ነው። ዶር ብንያም የተሰጠው የክብር ዶክትሬት ያልተገባው ስለመሆኑ በትህትና ሞግቷል። ትውልድ እንዲህ ይገነባል።
የታዳሚውን ዕድምታ፤ ተመስጦ፤ የማድመጥ አቅም፤ ውስጣቸው ያለው ርህርህና ያጽናናል። ያስተምራል። ይመራል። ይፈትሻል። ይመረምራል። ይዳኛል። ይመዝናል። ይመክራል። ይገስፃል። ይሞግታል። ብዙ በጣም ብዙ የምርምር ሥራ ቢሠራበት የኢትዮጵያዊነት ኃይለ አቅም ምን ያህል ጥልቅ እና ምን ያህል የተመሰጠረ አድብቶ ዘመኑን እዬጠበቀ ስለመሆኑ ራዲዮሎጂ ነው። ለዚህ ገዢው አደብ ገዝቶ እራስን በዕውነት ቴርሞ ሜትር ሙቀቱን መለካት ነው።
መመረጥ፤ መመረቅ። ሰማዕትነት። መሰጠት ምን እንደሆን? ምን እንደሚመስል በዕውን ተቋም የሆኑበት ሰብዕና እንዲህ ጉልላት ሆኖ ማዬት የፈጣሪ ታምር እና ገድሉ የማዬት ዕድል ነው ዬተሰጠን። እግዚአብሄር ሥጦታው፤ የሽልማት ደረጃው ጥልቀቱ ለመግለጽ ቃል መግለጽ ይሳነዋል።
ውጭ አገር ፖሊሲው ደግነት፤ ርህርህና፤ ተፈጥሯዊነት፤ ግሎባልነት፤ አጽናኝነት ነው። ስለዚህም ይህ በመንግሥትም በግልም፤ በማህበረሰብ የሚደረጉ መልካምነቶችትልማቸው በቅንነት ይስተናገዳሉ። እኔ በምኖርባት ቅድስት አገር ሲዊዘርላንድ ይህ ዕውን ሆኖ አያለሁኝ። በእኔ በህይወቴም።
ሆስፒታል ስሄድ ሊፍት አልጠቀም። በደረጃው ነው እምጓዘው። ደክሞኝ ሳርፍ አላፊ አግዳሚው ስታፎች እንርዳሽ እያሉ ይጠይቁኛል። ወንበር ቀጣዩ መምሪያ ላይ አለ ከዛ እርፍ በይ፤ ቀጠሮሽ እሚያልፍ ከሆነ ኢንፎርም እናደርጋለን ይሉኛል። እኔ ደረጃ መውጣት እንደ ጅም ነው ዬማዬው ለዛ ነው ሊፍት እማልጠቀመው። የእነሱ ሰዋዊነት ግን የሰርክ ምግቤ መሆኑ መታደሌ እላለሁኝ። የዬክፍሉ የሃንድሊግ ዕፁብነት ደግሞ ተነግሮም አያልቅ።
ከእኛ አይዟችሁ እንኳን ያስቀጣል፤ ያስግዛል፤ ያሳደድላል፤ መሪ የሚባሉት ሁሉም በዕንባ፤ በሶቆቃ፤ በመከራ መካከል ያሉትን የሚያጽናኑ ወንጀለኞች ናቸው። የእግዚአብሄር ታምሩ በዕንባ ዋናተኞች ባዕት ያልተገኙት የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ወሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ ለክብር፤ ምክትል ጠቅላይ ሚር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮነን ልጃቸውን ለማስመረቅ በተገኙበት ቅዱስናን የክብር ዶክትሬት ለመስጠት፤ በሥርዓቱ ለመገኜት አጋጣሚው ቅጣት ነው። ምክንያቱም ሕይወቱ በለለበት በዛ በረከት ውስጥ ተገኝቶ ደግነት፤ ርህርህና ቁሞ ሲሞግት ለማዬት መብቃት በራሱ የፈጣሪ ታምር ነው። "አድርገኽልኛል እና አመሰግንኃለሁ።"
በሌላ በኩል "ተናገሩ ድንቅ ሥራውን መስክሩ።" ታምራቱ ሐዋርያ ሆኗል። በኢትዮጵያ ጭካኔ በሚመራት አገር፤ በዞግ በሚታመስበት ባዕት ግዑዙ ሳይቀር በተኮደኮደ ኢ-ሰባዕዊነት ማህበርተኝነት በተመደበባት ኢትዮጵያ ይህን ጥሶ እንዲህ አይነት ገድል መፈፀም መመረጡ ለዘመናችን ቅዱስ መዳህኒት ነው።
በጭካኔ የተበከለውን፤ በአረመኔነት የቆሸሸውን፤ በእንሰሳዊ ባህሪ የደለቡ ሰባዕዊነትን በሚቀጠቅጡ የዘመኑ ከንቱወች ይማሩበት ዘንድ ታምሩን ፈጣሪ ገልጧል። በዚህ ውስጥ የመሪነት፤ የማደራጀት፤ የማቀናጀን፤ አቅምን የመምራት አቅም በሙሴነት ተገልጧል። የማይቻለውን በመቻል እና በማስቻል ልቅና በልዕልና በትህትና ዘውዳዊነት ተገልጧል። ተመስገን።
ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለትናንትም፤ ለዛሬም፤ ለነገም ድልድይ ሐርድም /// ሶፍትም ዌር ነው ቅድስናዊው ጎዳናው ትውልድ ነው። የትውልድም ነው። በዚህ በተግባር በተባ፤ የአይዟችሁ ተቋም ውስጥ ፍካቱ ተቋምነቱ ኢትዮጵያ የራባት እና የጠማት ህልሟ ነው። ለኢትዮጵያ የፖለቲካ አቃቂር ሳይሆኖ ሰዋዊነት ላይ፤ ተፈጥሯዊነት ላይ የሚሠራ ቲም ነው የሚያስፈልጋት እምለውም ለዚህ ነው።
እንደምን #ታዳሚውን ኢትዮጵያዊው ትህትና፤ ኢትዮጵያዊው ርህርህና፤ ኢትዮጵያዊው ደግነት፤ ኢትዮጵያዊነት አጽናኝነት፤ ኢትዮጵያዊ አይዟችሁ ምን ያህል ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆኑን በዕውን የሚታይ የሚጨበጥ ፋክት ነው። ኢትዮጵያዊው የሚፈልገው ቨርዥን ይህን ብቻ ነው።
ኢትዮጵያዊው ወገኔ በማይፈቅደው፤ በማይፈልገው፤ በማይወደው፤ በሚጠዬፈው ኢሰባዊ ፖሊሲ፤ ኢሰባአዊ አይዶወለጂ እንደሚመራ የታዳሚው ግብረ ምላሽ ያሳያል። ለእኔ የበለጠ ተስፋ እንዲኖረኝ አድርጎኛል። አንድ ቅዱስ ቲም ይህን ምስቅልቅል ያለ የጭካኔ ዘመን ሊገላግለን እንደሚችል ማስረጃ ሆኖኛል።
እራሱን ትቢያ፤ የማይረባ፤ ድውይ አድርጎ ያቀረበው የደግነት ሐዋርያ ክቡር ዶር ብንያም ሙሴነት መልዕኩ፤ ገፁ፤ ሰብዕናው፤ ፀጋው እና ምርቃቱ ምስክር ሆኖ በመቅረቡ ታዳሚው ሚዛናዊ ርትህ ሰጥቶበታል። ፍትህ ሳይሆን ያልኩት ርትህ ነው። ከፍትህ በላይ የሆነ ርትህ ነው የሰጠው። የፈጠረውም ደስታ ሳይሆን ሐሴት ነው። ዕውነተኛው ፍርድ #ርትህን፤ ዕውነተኛው ደስታ #ሐሴትን ነው አምጦ የሚወልደው። ይህን በዕውን አይቸበታለሁኝ።
ሐሴት የገኃዱ ዓለም አይደለም። ርትህም የገኃዱ ዓለም አይደለም። #መንትዮሹ #እዮራዊ ናቸው። ሥጦታው ከመንፈስ ቅዱስ ነው። ለዚህም ነው እኔ እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መክሊት፤ መልዕክት ጥሪ አለበት የምለውም ለዚህም ነው። በሂደቱ አክብሮትን በአክብሮት፤ ሁላዊነትን በሰባዕዊነት፤ ምስጋናን በፍቅራዊነት አዋዶ ዬተራራውን ስብከት በዕውን አሳይቶኛል።
ሐሴቱ መልካዕምነትን እራሱን ዓውጇል። ሰባዕዊነት አሸንፏል። የደግነት መሪነት አቅሙን ጉልላት አድርጓል። እንኳን ደስ አለህ የደግነት ቆሞስ፤ የርህርህና ኤፒስ ቆሞስ፤ የአጽናኝነት ጳጳስ፤ የአይዟችሁ እጬጌ። ለኢትዮጵያዊነት ተፈጥሯዊነት ኑርለት። ዕድሜህን የማቱሳላ ያድርግልኝ። አሜን። ዶር አሜን፤ አባ ምስባክ፤ አባ ትህትና፤ አባ አብርኃም፤ አባ ሙሴ፤ አባ የፍቅር እልፍኝ ኑርልኝ። እንኳን ደስ አለን።
ሳልሞት ዬአይዟችሁ ልዕልና
የተራራው የትህትና ልቅና
ብንያም አፅናኙ ገናና
ቅኔኛ!
አናባቢ ተነባቢ የመሰጠት መገኛ
ቢኒኛ
የኔታ- እኛ
የደግነት ዕፁብ ሁነኛ
የአጽናኝነት ምስባካዊ ሐዋሪያዊ ዘበኛ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
21/07/2023
https://www.facebook.com/zemariErmyas/videos/978017750189252
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ