ለሶስት ዓመት በግዞት!

 

ለሶስት ዓመት በግዞት!

 
ለሁለት ዓመት በግዞት የአርቲስት ኃጫሉ ሃውልት እስከ አዋርድ።
ሰንበትን ለተቆርቋሪነት።
ሰንበትን ለሰባዕዊነት።
"ኢትዮጵያዊውም አቤሜሌክ ኤርምያስን፦ ይህን አሮጌ ጨርቅና እላቂውን ልብስ በብትህ ከገመዱ በታች አድርግ አለው፣ ኤርምያስም እንዲሁ አደረገ። ኤርምያስን
በገመዱ ጎተቱት፣ ከጉድጓዱም አወጡት፣ ኤርምያስም በግዞት ቤት አደባባይ ተቀመጠ።"
(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፲፪ - ፲፫ )
ኦነግ ኢትዮጵያ ሲገባ 5 ንፁህ የአማራ ልጆች በአደባባይ ተጨፈጨፋ። 1300 ጦላይ ተወረወሩ። ከእነዛ የተረፋት ሦስት ዓመት ሙሉ ታስረዋል። ጠያቂ የላቸውም። ሁነኛ የላቸውም።
5 ሰማዕታት በሥም አናውቃቸውም። ዶር አብይ ሲቀልዱ ለለውጥ እንደተከፈለ መስዋዕትነት ቁጠሩት ብለው ነበር። ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ።
ከዛ የተረፋት አማሮ ላይ የጫካ ክንፋቸው ሥማችሁ አማራ ይመስላል ብለው እንደ ጨፈጨፏቸው እነኝህም በሥማቸው እስር ቤት በግዞት የተቀመጡ ናቸው።
ሌሎቹ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ አዲስ አበባን ለማውደም በሠሩት የአርቲስት ሃጫሉ ህልፈት ምክንያት እንዳይሳካ ያደረጉ፣ ቤተ እግዚአብሔርን ከቃጠሎ ያዳኑ አርበኞች፣ ሰማዕታት ናቸው። ተረስተዋል።
ከእነኝህ ሌላም አዲስ አበባ በብሔራዊ ባዕላት ጎላ ብለው የሚታዩት ሁሉ እዬታፈኑ የት እንደደረሱ አይታወቅም። አፋኙ የዶር አብይ ማፍያ ነው። ቤተሰብ ሪፖርት አያደርግም።
የት ሊገባ። በዚህ የታፈነ አዬር ውስጥ ተሁኖ ስለዴሞክራሲ ቅልጣንም ቅብጠትም ነው። መኖርን ለማኖር እንትጋ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
16/07/2022
ርትህን ከእዮር።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።