ቢፈሩሽ የተገባ ነው። ሊቀ ትጉኃን ነሽና።

 

ቢፈሩሽ የተገባ ነው። ሊቀ ትጉኃን ነሽና። 
 
ለማቀርበው ዕውነት ሙግት ያለው ይምጣልኝ። በፍቅር እንወያያለን።
ብርቱዋ ካቴና የድል አጥቢያ አርበኛ የቤተመንግሥት ሁነኛ የሆነበት ገጠመኝ በቅጡ ሊሞገት ይገባልና።
"እግዚአብሄርን የሚፈራ ትዕዛዙንም 
 
እጅግ የሚወድ ሰው፤ ምስጉን ነው።"
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፲፩ ቁ ፩)
 

 
 
ውዴ እንዴት አለሽልኝ? የእኔ ብርቱ ሙሉ ፲፫ ዓመት ለምታምኝባቸው የዕውነት ማህለቆች ፊት ለፊት ተጋፈጥሽ። አቅመ ቢሶች ይፈረሻል። ይገባል ሊፈሩሽ ይገባል።
 
ሁሉም አለሽ እና። እናት ነሽ። ሚስት ነሽ። እህት ነሽ። መምህር ነሽ። ሞጋች ነሽ። ልጅም ነሽ። የብዕር ጠብታ ጥሪም መሪም ነሽ። አቅምሽ በአቅምሽ የተከሰተበት መስክ አቅመ ቢሶችን አስበረገጋቸው።
 
እናም አካልሽን ማገታቸው የብቃትሽን ልክ ማዕቀብ ሊጥሉበት አይችሉም። መቼውንም። አንቺ እራስሽ ተቋም ነሽና። አንቺ እራስሽ የትውልድ አብነት ነሽና።
 
የእኔ ብርቱ ትጋትሽ በብቃት፤ ትትርናሽ በምሳሌነት፤ ድፍረትሽ በዕውነት ፋፍቶ መከራ እንድትቀበይ ሆኗል። ግን "ከመከራ ጀርባ ታላቅ ክብር አለ" ይላል ወንጌል። ክብር ነሽ። ከብረሻልም። ፀፀት የለብሽም። 
 
መምህርነትሽ ከተጎዳው ጎን፤ ከዕንባ ዋነተኛ ጎን መቆምሽም ቢሆን የዛሬ አይደለም። እኔ ለተጨማሪ ተሳትፎ ከፀጋዬ ድህረ ገጽ እና ከፀጋዬ ራዲዮ በተጨማሪነት የደጉ ዘሃበሻ፤ የደጉ ሳተናው ድህረ ገጽ ቋሚ አምደኛ ከሆንኩበት ጊዜ ከ2013ጀምሮ ነው እማውቅሽ። ወደ ፲፫ ዓመት አውቅሻለሁ። ብርቱ ነሽ። ጠንካራ ነሽ። አንድ ጊዜ ኢሜል ሁሉ ልኬልሽ ነበር። ግርም ብለሽኝ። ዬእኔ ውድ አይዞሽ። 
 
አንቺ በታገልሽበት ዘመን ከካቢኔው ውስጥ አንድ ሰው ብቻ በትግል ከነበሩት በስተቀር፤ በአገዛዙ ዬዬትኛውም መስክ በጣትየሚቆጠሩ ጥቂት ሰወች ሲታገሉ የቆዩ ሊኖሩይችላሉ።
 
ግን ብዙው ከጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ጀምሮ አብዛኛው የድል አጥቢያ አርበኛ ነው። በዘመነ ህወሃት በካድሬነት ሲያገለግሉ የነበሩ ናቸው። አንቺ ግን ቀደምት ነሽ። ብዕርሽ ለረጅም ጊዜ ሞግታ ለሌሎች መኖር ለአንቺ እግር ብረት መሆኑን ሳይ እቆስላለሁ።
የእኔ ውድ ትውልዳዊ ድርሻሽን የተወጣሽ የብቃት አርያነሽ። አይዞሽ። ያልፋል። ለምታደርጊው መልካምነት ግን ዝቅ ብዬ አመሰግንሻለሁ የብዕር እና የብራና ትንታጓ ሊቀ - ትጉኃን።
 
ውዴ መስኪ #የድል #አጥቢያ #አርበኛ #አይደለሽም። ዛሬ የመጣሽ አይደለሽም። ጎርፍ አምጥቶ ደለል የሰራብሽ የወቅት ታጋይ አይደለሽም።
ስለመቆምም ስለ በረደውም ትግሉ ወጣ ገባ እያልሽ ዬተቆራረጠ ትግል አላደረግሽም። እኔ እራሴ በብዕርሽ ሞጋችነት የማውቅሽ ፲፫ (13)ዓመቴ ነው።
 
ስለዚህ በህይወት እስካለሁ ድረስ በሙሉ ልቤ ስለ ብርታት እና ጥንካሬሽ ቀደምትነት እመሰክራለሁ። አንቺ #ዕንቁ ነሽ። ለእኔም #ሞጋቿ #አልማዜም ነሽ። ኑሪልኝ የእኔ ብርቱ።
 
ክብሮቼ ደህና ዋሉልኝ፤ ቸር አምሹልኝ፤ በሰላም እደሩልኝ። ዕውነትን አልሙልኝ። አሜን። ይደልወ ከዕውነት ነፍስ ጋር ያዋድደን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። 
 
ሥርጉተሥላሴ
SerguteSelassie
21/07/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።