ኢትዮጵያ ከፋት። እኔም።

 

ኢትዮጵያ ከፋት። እኔም።

 
እኛም ውስጣችን እዬገደልነው ነውና ነፍስ ይማር።
ግን ኢትዮጵያ ትፀልይ ወይንስ ታልቅስ? ዛሬ ጥዋት ዕንባዋን ለመታደግ በተጠራ የዲሲ ህሊናዊነት ስምምነት አልተደረሰም። አዳጠው። እኔ ሳስበው አንድ ሰው ከሁለት የመተርተር ያህል ነው።
ለዚህ ትግል ዕድሜ ዘመናቸውን የሰጡ፣ የተሰው፣ ወጣትነታቸውን የገበሩ፣ አካላቸውን ያጡ፣ የመከኑ፣ ጫካ ለጫካ የተንከራተቱ፣ በእስር ቤት ለተገላቱ፣ ተሰደው ወላጆቻቸው ሳያገኙ በሞት የተነጠቁ ስንቱ ይነሳ ዛሬን ሳናግረው ሆድ ባሰኝ።
የዕውነት ሆድ ባሰኝ፣ የሚሆን መስሎኝ የምችለውን አድርጌ፣ አልሆን ሲል በራሴ መንገድ ሰብሰብ ብዬ ብታገልስ ብዬ የወሰንኩት ውሳኔ ፅድቅ ነበር። እርግጥ በወቅቱ የዘመቱብኝ፣ ያዘመቱብኝ ሰዎች ሆኑ ያልተረዱኝ ወገኖቼ ዛሬ የሚነግራቸው ዕውነት አለ። ካዳመጡት። እነዛኑ ናቸው አሁንም ለዕንባ ድምፅ እንዳይኮን የሚያነኩሩት።
የዲሲውን ስብሰባ ሂደት ከኢትዮ 360 አዳመጥኩት። ህወሃት በአንድ መትረዬስ ሳትለይ ቢያገኛቸው የማይለቃቸው፣ ወይንም ካቴና የማያማርጥላቸው ወገኖች በኢትዮጵያዊነት ጥሪ ላይ እንዲህ ዛሬ ተባደግ ሲሆኑ ማዬት፣ በተለይም ትውልዱ አሳዘነኝ። ብክነቱ።
ኢትዮጵያ ከአብይዝም በላይ ወይንስ በታች? ይህን መመለስ የቻለ መንገዱ አይጠፋበትም።
ኢትዮጵያስ መጨረሻዋ ምን ይሆን? እኔ እንደማስበው የሰው ልጅ እንደ በግ ቆዳው ተገፎ፣ ተቃጥሎ፣ ብትን የቀብር አፈር ከማጣት በላይ ምን ይምጣ? ይህን ከኢትዮ 360 አዳምጫለሁኝ።
የአቶ ዬሖንስ ወልዴ የሉሲ ትቤት መሥራች ዕንባ የፈሰሰው ለትውልዱ ነው የመሬት የማጣት ጥሞና ነበረው። ይህን የውስጥ አለማድርግ ማን ይባል? ምንስ ይባል?
አብሮ መሥራት ካልተቻለ የግልን ኃላፊነት ብቻም ሆኖ መወጣት ይገባል። ጊዜ ዕውነትን ያፈልቃልና። የትናንት ላይበቃ ከአላማችን ጫፋ ሳንደርስ እንዲህ ያልቦካ ምርጊት መሆን ማዘን ቃሉ አይገልፀውም። ታመናል።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ፈጣሪ ሆይ! መንገድ ጠፍቶናልና ምራን እባክህን?



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።