#አዛውንቱ ጋዜጠኛ ይፈቱ።

 

#አዛውንቱ ጋዜጠኛ ይፈቱ።
ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
"ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።"
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)
 

 
አዛውንቱ ጋዜጠኛ የአንጀት በሽተኛ ናቸው። ያገኙትን አይመገቡም። ለአንጀት በሽተኛ እንኳንስ እስር ቤት ቤት ውስጥ ብዙ አስቸጋሪ ነገሮች አሉበት።
አቶ ታዲዮስ ታንቱ ደፋር ተናጋሪ እና ሞጋች ናቸው። ታሪክን አልክድም ባይ ናቸው። የበደሉ ሠወች በተግባራቸው ይቀጡም ባይ ናቸው። ይህ መብት ነው።
እሞግታለሁ የሚል ሊሞግታቸው ይችላል። በዚህ ዕድሜ አስሮ መበቀል ግፍ ነው። እሳቸው የአገር አሻራ ናቸው። አሻራቸው የኢትዮጵውያን የነፃ ህዝብነት ምስክር ናቸው። ነፃ ህዝብ ነፃነቱን በድፍረት መጠቀም አለበት የሚል አመለካከት ያለባቸው ይመስለኛል።
ይህን በማድረጋቸው ብቻ ይህን ያክል መከራ በዬዘመኑ ሊከፍሉ አይገባቸውም። አሁነኛ ሰወች ስንት ሹመት ሽልማት ምስጋና ሲታደላቸው እናያለን። ይህም ቀርቶ ሰላማዊ ኑሯቸው ለምን ይታወካል።
መንግሥት ወላጅ ማለት ነበር የአንድ ሰው ባህሬን መቻል እንደምን ይሳነዋል የኦዳ ገዳ ኦህዴድ መራሹ የአዳማ ሥርዕወ መንግሥት ነኝ እስካለ ድርስ።
ግፍ ነው እኒህን አዛውንት እንዲህ አሥሮ ማሰቃዬት። የአንጀት በሽተኛ መሆናቸው እራሱ ምን ያህል ይህ ሥርዓት ጨካኝ እንደሆነ ያመሳክራል።
እናት ብዙ ዥንጉርጉር ልጆች አሏት። ሁሉንም እንደባህሬያቸው ትይዛለች። ይህን ማድረግ የሚችል መሪ ኢትዮጵያ መቼ ይሆን የሚኖራት። የኦሮምያ የሽግግር መንግሥት መሠረትን ያሉ ኦነጎች በክብር ተቀምጠው በሃሳብ የሞገተ ነፍስ እንደምን ይታሠራል?
ግን ኢትዮጵያ የማን ናት?
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
16/07/2021
ፍትህ ለአቶ ታዲዮስ ታንቱ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።