ጠባቂው። መልካምነት እንደ ጊዜ ብቻ አይደለም። በመሄድ ውስጥ ቀድሞ ይጠብቃል። ምርቃት፤ ሽልማት ይሆናል። የመልካምነት ተፃራሪው ግን ይመነጥራል።

 

ጠባቂው።
"የሰው ልጅ መንገድ ያዘጋጃል፤
እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።"
(ምሳሌ፲፮ ቁጥር ፱)
 

 
 
ማህበረ ክብር ውድ ቤተሰቦቼ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ? አይዞን። የሰው ልጅ የተሰጠውን ጊዜ ለመልካምነት እና ለደግነት ሊያውለው ይገባል። ደቂቃወች ይናገራሉ፤ ያናግራሉ። ደቂቃወች አልፈው ሊጠብቁም /// ላይጠብቁም ይችላሉ። ከጥሪት አንፃር። መልካምነት ለእኔ ጥሪት፤ ትውፊት እና ትውልድ አበርካች ፀጋ ነው።
 
መልካምነት እንደ ጊዜ ብቻ አይደለም። በመሄድ ውስጥ ቀድሞ ይጠብቃል። ምርቃት፤ ሽልማት ይሆናል። የመልካምነት ተፃራሪው ግን ይመነጥራል። 
 
ስለዚህ አወንታዊ ሰብዕናወችን ማቅረብ፤ አሉታዊ ሰብዕናወችን ማራቅ ጤንነትን ለማንነት መቀለብ ነው። ምርቃት blessing. ክፋነትን ላለማድመጥ ከአሉታዊ ሰብዕናወች መራቅ የመወሰንን አቅም ይወስናል። 
 
በተለይም ኃላፊነትን እና ተጠያቂነትን በቤተሰብ፤ በማህበራዊ ግንኙነት፤ በአገራዊ፤ በአህጉራዊ ሆነ በተፈቀደላቸው ልክ በግሎባሉም ሁነት የድርሻቸውን የተወጡ፤ በህይወቱ ውስጥ የኖሩ ሰብዕናወች መዋዕለ መንፈሳዊ ግብረ ሰላማቸው ለአወንታዊ ሰብዕናወች ብቻ ሊሆን ይገባል። ጊዚያቸውን ቆጥበው ማኔጅ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
 
ጊዜን፤ ገንዘብን፤ ጉልበትን፤ ቅዱሳዊ የምክር አገልግሎት ሁሉ በርካሽ ለሚቀልቡ ቅኖች፤ የመልካምነት ጥገትነታቸው ከሚበቅልበት ማሳ ላይ ማተኮር ብልህነት ነው። በሌላ በኩል ይህን ማድረግ ለራስ የጤንነት ሰብዕናም ዘብ መቆም ነው። አሉታዊ ሰብዕናወች የሚያውቁት እራሳቸውን ብቻ ስለሆነ ይጎዳሉ። ያደቃሉ። ቢድኑ መድከም ጥሩ ነው። የማይድን ጉድጓድ ሰብዕና ከሆነ ግን ለራስ ጤንነት ማሰብም ይገባል።
 
ከመልካም ሰወች ጋር መሆን በረከት ነው። ጤና ነው። ሰናይ ነው። ትምህርት ቤትም ነው። ጊዜውን መሻማትም ያስፈልጋል። የተቃኑ ቅኖች ሁልጊዜም እሸት ናቸው። አይነጥፋም። ከፈጣሪ በታች መልካምነት ጠባቂም ነው። ቀድሞ ይጠብቃል። ቀድሞ ይንከባከባል። ቀድሞ አጥር ከለላ ይሆናል።
 
ከእኛ ከሌሊቱ 10.00 ሰዓት ነው። የብዕራ አውሊያ እንዲህም ያደርጋል እንደማለት። የአባቶቻችን አምላክ መልካሞችን አበራክቶ፤ አወንታዊነትን ያፋፋልን ዘንድ ፈቃዱ ይሁን። አሜን። ቅድስት እናት አገር ኢትዮጵያን እና የዕንባ ዋናተኞችን ይጠብቅልን። አሜን።
 
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
20/07/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።