ይሕ ሕዝብ፡-< በፀጋዬ ራዲዮም በንባብ ይቀርባል።

 

ለመሰናበቻ ከአቶ ጋሻው አባተ ያገኜሁት ነው የእኔም የ፲፭ ዓመት የትጋቴ መስክ የብላቴው የማር መንፈሱ ነውና። 
በፀጋዬ ራዲዮም በንባብ ይቀርባል። 
 

 
 
"ይህን ሕዝብ በቅጡ ካላስተዳደራችሁት የዋዛ አይምሰላችሁ …
ይህ ህዝብ አፄ ቴዎድሮስን ወልዶ የበላ፤ የአፄ ዮሐንስን አንገት ያስቆረጠ፤ በእምዬ ምንሊክ ሐውልት ላይ ቁማር የሚጫወት፤ አባባ ጃንሆይን (ሥዩመ-እግዚአብሔር) አንግሶ ያዋረደ፤ ቆራጡን መሪ ጓድ መንግሥቱ ኃይለማሪያምን አንቆራጦ ያባረረ (በቁሙ አስቀምጦ ቲያትር የሚያሳይ)፤.
 
መሪዎቹን የሚፈራ- መሪዎቹን የሚጠላ
መሪዎቹ የሚፈሩት-መሪዎቹ የማይወዱት
ሠምና ወርቅ የሆነ ሕዝብ ነው፡፡
 
ይሕ ሕዝብ፡-
 
ፍቅሩንም ጥላቻውንም በሆዱ የሚፈጅ ምሥጢረ ሥላሴ የሆነ ሕዝብ ነው፡፡
ይሕ ሕዝብ፡- 
 
ንጉሡ ጥለውት ጠፍተው (ተሰደው) ለራሡ የጎበዝ አለቃ በመፍጠር ፋሺሽቶችን ተዋግቶ አገሩን ነፃ ያወጣ፤ መንግሥቱም (ኃይለማሪያም)ወደ ዚምባቡዬ ሪፈር በተባለ ጊዜ ራሱን በራሱ ያስተዳደረ ጨዋና ንጉሡ ከሥደት ሲመለሱ አልጋውን ያስረከበ የዋህ ሕዝብ ነበር (አይገርምም?)፡፡
 
ይሕ ሕዝብ፡-
 
በራሡ ቋንቋ ፍቅሩን አስከመቃብር የጻፈ፤ ሼክስፒርን ፈቶ የመግጠም ፀጋ (ዬ) የተሠጠው ሕዝብም ነው፡፡
ይሕ ሕዝብ፡-
 
በቅዱስ ያሬድ በኩል ከሠማየ ሠማያት የመልአክትን ዝማሬ ሰምቶ ዜማ የሠራ ዜመኛ ሕዝብ ነው፡፡
ይሕ ሕዝብ፡-
 
ጦርነትን በባዶ እጁ እንዳሸነፈ ሁሉ ኦሎምፒክንም በባዶ እግሩ ድል ያደረገ ጉደኛ ሕዝብ ነው፡፡ (ሮም ሁለቴ ጉድ ሆነች እንዳሉት የአውሮፓ ወሬኞች…)
 
ይሕ ሕዝብ፡-
 
የዓባይን ልጅ ውሀ ጠማው ተረቱን እያደሰ ሱዳንን አልፎ ግብፅን እስከ ሲናይ በርሀ ውሃ የሚያጠጣ ሳይተርፈው የሚቸር ውሃ የሚያደርግ ሕዝብ ነው፡፡
 
ይሕ ሕዝብ፡-
ሌላው የአፍሪካ ሕዝብ የቀኝ ግዛት እባጩ ንፍፊት ሳይፈነዳለት አብዮት ያፈነዳና እውነተኛው መንገድ የእኔ ብቻ ነው ብሎ ባላብ አደርና በወዛደር በእናቸንፋለንና በእናሸንፋለን ጎራ ለይቶ አንድ ጥይትና ወጣት እስኪቀር ድረስ የሚጫረስ ግራ የገባው-ግራ -ዘመም ሕዝብ ነበር (ው)።
ይሕ ሕዝብ፡-
ከእናቱ ልጅ ይልቅ በመጽሐፍ ለሚያውቃቸው አብዮተኞች በማድላት ወንድሙን የሚገድል፤ አገር ለመገንጠልና ለማስገገንጠል እስ-በሱ የተጫረሰ ጉደኛ ሕዝብ ነው፡፡ ሲገርም!!! የሆነው ሆኖ…
ይሕ ሕዝብ፡-
መሪዎቹን የሚፈራ- መሪዎቹን የሚጠላ
መሪዎቹ የሚፈሩት-መሪዎቹ የማይወዱት ፡፡
ሠምና ወርቅ የሆነ ሕዝብ ነው፡፡
ፍቅሩንም ጥላቻውንም በሆዱ የሚፈጅ ምሥጢረ ሥላሴ የሆነ ሕዝብ ስለሆነ በቅጡ አስተዳድሩት።
ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
@Book For All"

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።