Julay 12/2019 የዴሞክራሲ ፎርፌ

 Julay 12/2019


የዴሞክራሲ ፎርፌ

 
ግርም ከሚሉኝ ጉዳዮች "አህዳዊነት" ማስፈራሪያ መሆኑ ነው። አህዳዊነት እንፈልጋለን የሚሉ ዜጎች እኮ እንደ ዜጋ መብት ሊሰጣቸው ይገባል። ዴሞክራሲ እኮ ልትሰማው እማትፈልገውን ነገር ታግሰህ ማድመጥና በላቃ የሃሳብ ብልጫ መርታት ነው።
ሉዕላዊነትን እንዲደፈር ጦርነት አዋጁን መሪን አንቀባረህ ይዘህ፤ ስለሚዘረፈው፤ ስለሚጠፋው ንብረት ብቻ ሳይሆን መተኪያ ስሌለው የሰው ልጆች ህይወት ያለ አግባብ መቀጠፍ፤ ተስፋቸው መዘቅዘቁ፤ ስለሚዘረፈው የአገር አንጡራ ኃብት፤ አገር እንመሰርታለን አጀንዳ በፌስታ በቤተ መንግሥት ግብረ ሰላም እያዝመነመንክ ሌላው የተለዬ ሃሳብ ያለውን ወዮ! የተገባ አይደለም።
ለመሆኑ አህዳዊ መንግሥት የሚሉ ድርጅቶች አሉን? ግለሰቦችስ ቢሆኑ ቁጥራቸው ምን ያህል ነው? ይህ ተጠንቷልን? በአህዳዊ ሥርዓት ያሉ አገራት ብልጽግናቸውን ኃያልነታቸውንስ ቀንሶታል? ቀድሞ ነገር እኮ ክልል አደረጃጀቱ እኮ የቋንቋ ፌድራሊዝም ይባል እንጂ በውስጡ የአህዳዊ መንፈስ ያለበት ነው። በፌድራሊዝም ጽንሰ ሃሳብ የተሻለው የአማራ ክልል ብቻ ነው እኔ እንደሚገባኝ ከሆነ በቋንቋው ፌድራሊዚም ማለቴ ነው።
እኔ ስለምን ሃሳቦች ማስፈራሪያ "አያ ጅቦ መጣ" በኢትዮጵያ ፖለቲካ እንደ ነገሰ ግርም ይለኛል። ሌላው የሚገርመኝ ደግሞ ዴሞግራሲያዊ አካሄድ ሲባል ነው። የአንድ ቀንጣ ነፍስ ሃሳብ ለማስተናገድ አቅም የለሽ የ100 ሚሊዮንን እማ እንዴት ተብሎ ነው?
እንደ እኔ ዜጎች የተሻለ ነው የሚሉትን ሃሳብ ያቅርቡ በሃሳቡ ላይ ሙግት ይከሄድበት አስቀድሞ ሃሳቦችን ማስፈራሪያ ከማድረግ ይልቅ። መብትም ነው፤ ነጻነት ነው። ራሱ በፌድራሊዘም አንደራደርም የተገባ ቋንቋ አይደለም። መደራደርም አለመደራደርም የሚቻለው መርሁ ጉዞው አሻጋሪነቱ ለዴሞክራሲያው ሥርዓት ከሆነ የሃሳብ ማዕዶት ክፍት ሊሆን ይገባል በእኩልነት ለሁሉም።
በቀደመው ጊዜም ፌድራሊዝም በቋንቋ ታይቷል። በመለካዕ ምድራዊነትም በደርግ ጊዜ ተሞክሯል። ፌድራሊዝም በህውኃት ብቻ እንደመጣ ተደርጎ የሚነገረው ወደል ግድፈት ነው። ፌድራሊዝምን ደርግ ጀምሮት ነበር። በአሁኗ ኢትዮጵያም አህዳዊነትን ስትመለከቱት ትግራይ እኮ 27 ዓመት ሙሉ በአሃዳዊነት መንፈስ ነው የዘለቀችው። የቀረው ቃሉ ብቻ ነው እንጂ ድርጊቱ እንደዛ አህዳዊ ነው።
ዴሞክራሲ ቃሉን አፋችን ስለለመደው ብቻ ሳይሆን ተፈጥሮውን በሚገባ ማጥናት ይገባል። እኔ እስከ አሁኑ ቀን ድረስ አንድም ድርጅት ተፎካካሪ፣ ተቃዋሚ፤ ተቀናቃኝ፤ ተደማሪ የሆነ አህዳዊ ሲል አልሰማሁም። ግን እንደ ትልቅ የፖለቲካ ማስፈራሪያ ሆኖ ወዲህ እና ወዲያ ሃሳቡ ጅዋጅዊት ሲሰራበት አያለሁኝ።
ይህን የሚደግፉ እንኳን ቢኖሩ ሃሳባቸው ፍላጎታቸው ሊደመጥ ይገባል። እንዲሸማቀቁ፤ እንዲፈሩ፤ እንዲሰጉ ዘመቻ ሊካሄድባቸው አያገባም፤ አቅሙ ከኖረው የኢትዮጵያ መንግሥት፤ አቅሉ ከኖረው የኢትዮጵያ መንግሥት ይህን ሃሳብ የሚያቀንቅኑትም ዜጎቼ ልጆቼ ናቸው ሊል ይገባል።
ኦሮሙማ እኮ ወጥ ማህበረሰብ ለመፍጠር ነው እኔ እስከገባኝ ድረስ። ጨፍላቂ ነው ለእኔ። ምክንያቱም ከ80 በላይ የተለያዩ የመህብረስብ ህብር ላለባት አገር የአንድ ማህበረሰብን ፍላጎት ተከተሉ ጭነት ነው ለእኔ። ሊያስፈራ የሚገባውስ ይሄ ነው፤ አህዳዊ የሚሉ ከኖሮ ... እስካሁን እኔ ስሜቱን የሚቀነቅኑ ታታሪዎችን አልሰማሁም፤ አላዬሁምም።
ግን አንድ ጥያቄ ለውዴቼ ሰጥቼ ልሰናበት? የአብይወለማ ሥርዕዎ መንግስት አቅል፤ አደብ፤ መቻል አለውን? አለውም ካልን ሆነ የለውም ካልን እስኪ ተጨባጭ ቁምነገሮች እያነሳን እንሟገትበት? በቅርንጫፎቹ ላይ ሳይሆን በሥርዕወ ግሱ ላይ።
መሸቢያ ሰንበት።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።