እመነኝ አትበለው።

 

እመነኝ አትበለው።

 
ማስረጃም አታቅርብ። ማገዶም አትፍጅ። እጬጌው ሂደት ለዕውነት የደነገልክ፣ ለመርህ ዘብ የቆምክ ፅናት መሆንህን ለቀኑ ቀን የሰጠው ዕለት ያውጃል እና። ይልቅ እራሱን ነፃ ላላውጣው ነፍስ እዘንለት።
በቀናት ውስጥ አመክንያዊ ሂደቶች ማንዘርዘሪያ አላቸው። አንተ በተፈጠርክበት መክሊት ስለመሆኑ ለባለ ህሊናማ ዓይናማወች ይገልጣል። ስለዚህ እመነኝ ብለህ እሰጣ ገባ አትግባ። አቅም አታባክን።
አንተ አንተን መሆን ካልተሳነው በመክሊትህ ልክ ዋጋህን ሳትለጥጥ ወይንም ሳታጎብጥ ወይንም ሳትቀረቅር ወይንም ሳታጣብቅ በተፈጠርክበት ምርቃት ውስጥ መሆንህን ምግባርህ ይገልፀዋል። ያብራራዋል። ይኽው ነው።
በራስህ ውስጥ ካለህ አንድ ነገር ግን አትርሳ። ቅንነትህን፣ ግልፅነትህን፣ ዕውነት ፈላጊነትህን፣ መርኽ፣ አክባሪነትህን፣ እርህርህናህን፣ ትጋትህን፣ ድካምህን የሚመርቅ ፈጣሪ እንዳለህ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ለቀኑ ቀን የሰጠው ዕለት የችግር ቋጠሮ ይፈታል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።