ልጥፎች

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሆደ ሰፊ አይደለም። ግልፍተኛ ነው። ግልቢያም አለበት።

 የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሆደ ሰፊ አይደለም። ግልፍተኛ ነው። ግልቢያም አለበት። ግልፍተኝነቱ ደግሞ ሥልጣን ላይ ሆኖ የዲፕሎማሲ ማህበረሰቡን እንደምን መያዝ እንደሚገባው እንኳን አያውቅም። ለዘርፋ ደም የሚያፈላ እርምጃ፤ ደም የሚያፈላ ንግግር ይደረጋል። ከዛ ፀጋ ይደፋል። ፀጋ ከተደፋ በኋላ ደግሞ ልምምጥ ይመጣል። አብሶ #ካድሬወቹ #በዲፕሎማሲ #ጉዳይ ላይ #እንዳይዘነቁሉ #በህግ #ሊታገዱ #ይገባል ። ፓን አፍሪካኒስት ኢትዮጵያ ዛሬ ያለችበትን ደረጃ የማይመጥናት ላይ ናት። በሌላ በኩል #በዘርፋ #ሙያ #ጠገብ #ኢትዮጵያውያን #በነፃነት #እንዲሠሩ #ሊፈቀድ #ይገባል ። ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ። በተለይ ማህበራዊ ሚዲያ አመጣሽ ሰብዕና ረቂቁን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ እንዲታቀቡ ሊደረግ ይገባል። ኢብን ሙሁራን ቢሆኑም። ኢትዮጵያ በትርፍ ተናጋሪወች ልትለካም አይገባም። ለዚህ ነው እኔ ኢትዮጵያ ለሁላችን ከብዳናለች የምለው። ለአገር ክብር ብርቱ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል። ተቋም አለ። ውጭ ጉዳይ ሚር። የዳበረ ልምድ ያለው። በነፃነት ይሠራ ዘንድ ይፈቀድለት። ከዞግ እሳቤ ተወጥቶ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ሥርጉትሻ2024/05/27

ስለምን???

  ስለምን??? ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ለምቾት የሚገነቧቸውን ፕሮጀክት መዋለ ንዋይ ስለምን ለዩንቨርስቲወች ድጎማ፤ ለሠራተኛ ደሞዝ መክፈል ላቃታቸው አብይ ሠራሽ ክልሎች አይመድቡም። ደቡብ ደሞዝ መክፈል ካቃተው፤ ደቡብ ዩንቨርስቲወችን መመገብ ከተሳነው ዛሬ ደቡብ ሰላም ነው ነው የሚባለው ይደፈርሳል። የማይቆም ከቁጥጥር ውጪ የሆነ አመጽም ሊነሳ ይችላል። ዳቦ ለሚጠይቁም ቀለሃ ሊታዘዝባቸው ይችላል። ችግር ደርሶ ማኔጅ ለማድረግ ከሚያቅት በእጅ ባሉ ነገሮች ቢያንስ ችግሮችን ለማስታገስ ጥረት ለምን አይደረግም። የኮሪደር፤ የጫካ፤ የሪዞልት ወዘተ እያሉ በፈንታዚ ከሚጓጓዙ። ድግሱም እንዲሁ ማዕቀብ ሊጣልበት ይገባል። የክልል አለቆችን በአጃቢነት ከማሰለፍ የፀጥታ ኃይሎች በቂ ናቸው ጉዞ ካስፈለገ። ለነገሩ ወንበሩ ባዶ ነው ብዬ የፃፍኩት 2011 መግቢያ ላይ ነበር። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ሥርጉትሻ2024/05/27

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅንነት የነጠፈበት ነው።

 የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅንነት የነጠፈበት ነው። ቅን ለሆነ ህዝብ ቅንነት የነጠፈበት ፖለቲከኛ በምን ሂሳብ ሊደማመጥ ይችላል? አይመጣጠንማ! ሥርጉትሻ2024/05/27

Zerihun and me on various Ethiopian issues ...

ምስል

ዋ! ያቺ ዓድዋ

ምስል

ስትለጥፋ አክሰሱ ያላቸውን ታዳጊወች እያሰባችሁ ይሁን።

  እባካችሁን ለሙሉ ዕድሜ ላለነው እጅግ #የሚሰቀጥጡ ፖስተሮችን ስትለጥፋ አክሰሱ ያላቸውን ታዳጊወች እያሰባችሁ ይሁን። ፍርኃት አብሯቸው እንዲያድግ መፍቀድ ነው። ይህ ደግሞ የሥነ - ልቦና ዝበትን ያመጣል። ኃላፊነት ሊሰማን ይገባል በዬምንተጋበት ዓውድ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ሥርጉትሻ 2024/05/26

የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚታመሰው #የማንነት #ቀውስ ባለባቸው ሰወች ነው።

  የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚታመሰው #የማንነት #ቀውስ ባለባቸው ሰወች ነው። እራሱ በፖለቲካ ምልከታው የማንነት ቀውስ አለው፤ በዞግም ማንነት ቀውስ ያለባቸው አሉ። እርግጥ ለመሆን #ስስ ነገር ከኖረ። ሌላው እራስን ለመግለጽ የኮንፊደንስ ቀውስም ያለባቸው አሉ። ይህን ሁሉ ጓዝ ተሸክሞ ምኞቱን የማይመጥን ህልም ይያዝና በቃ መተራመስ፤ ማተራመስ። በኢህአዴግ ዘመን ብአዴን፦ ደህዴን፥ ኦህዴድ አንድ ሰው እንዲህ ይገላበጥ ነበር። ከብአዴን፦ ህወሃት፦ ከህወሃት ብአዴን፤ ከብአዴን ብልጽግናም አለ። ያ ሰው የፖለቲካ ተንታኝ ወይንም ጋዜጠኛ ወይንም ሞደሬተር ሆኖ ሲመጣ ከእነጓዙ ነው። ይህ ነው ህመሟ የእማማ። ሥርጉ2024/05/25 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

#መሪነት።

  #መሪነት ። ገጣሚነት ብቻውን መሪነት ሊሆን አይችልም። ፀሀፊነትም ተማላውን መሪነት ሊሆን አይችልም። ተዋናይነት ቢሆን፤ ጋዜጠኝነትም ቢሆን የመሪነት አቅምን ሊያጎናጽፍ አይችልም። ፕሮፖጋንዲስትነት፤ የፖለቲካ ሳይንስ ሙሁርነትም መሪ ሊያደርግ ብቻውን አይችልም። መፈለግም መመኜትም መብት ነው። መብቱ ብቻውን ግን የመሪነት ክህሎትን አያጎናጽፍም። ተጽዕኖ ፈጣሪነትም የመሪነት አቅምን አያጎናጽፍም። መሪነት #ቅባዐ ነው። መሪነት መክሊትም ነው። መሪነት መሰጠትም ነው። መሪነት ግልፅነት ነው። መሪነት ታማኝነት ነው። መሪነት #ቅንነት ነው። መሪነት #አወንታዊነትም ነው። መሪነት መረጋጋት ነው። መሪነት የውስጥ ሰላም #ስፍነትም ነው። መሪነት አድማጭነት ነው። መሪነት አብዝቶ መቀመጥን ይጠይቃል። መሪነት ተመክሮን ይሻል። ለመሪነት ልምድ ያስፈልጋል። መሪነት ወቅትን የሚመጥን ሐሳብ አፍላቂነትም ነው። መሪነት መታመንን ይጠይቃል። መሪነት በመንፈስ መደራጀትን ይጠይቃል። መሪነት የማደራጀት አቅምንም ይጠይቃል። መሪነት #ጥሞናን ይጠይቃል። መሪነት ሲዩት ግርማ ሞገሱ ድንግጥ ሊያደርግ ይገባል። መሪነት #አደብ ነው። አቅል የለሽ ሰብዕና ለመሪነት ግጥሙ አይደለም። መሪነት ወጥኖ ማጠናቀቅን ይጠይቃል። መሪነት ለውሳኔ አለመቸኮልን ይጠይቃል። መሪነት ሰብዓዊነትን ማስቀደምን ይጠይቃል። መሪነት ቲም ወርክም ነው። መሪነት ተተኪን ማፍራትን ይጠይቃል። መሪነት በስልጠናም ይገኛል። መሪነት ማስተዋልም ነው። መሪነት ወጥ ፍላጎትን ይጠይቃል። መሪነት የመቻል ጥበብ ነው። መሪነት ዳኝነትም ነው። ብቃት ኑሮም ተቀባይነት ላይኖሮ ይችላል። ይህን ፈቅዶ መቀበል ይገባል። መሪነት #ፍዝ ለሆኑ ሰብዕናወች አይሆንም። መሪነት ርቱዑ አንደበት ይጠይቃል፡ መሪነት ቆፍጣናነትንም ይጠይቃል። ን...

ስለምን???

 ስለምን??? ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ለምቾት የሚገነቧቸውን ፕሮጀክት መዋለ ንዋይ ስለምን ለዩንቨርስቲወች ድጎማ፤ ለሠራተኛ ደሞዝ መክፈል ላቃታቸው አብይ ሠራሽ ክልሎች አይመድቡም። ደቡብ ደሞዝ መክፈል ካቃተው፤ ደቡብ ዩንቨርስቲወችን መመገብ ከተሳነው ዛሬ ደቡብ ሰላም ነው ነው የሚባለው ይደፈርሳል። የማይቆም ከቁጥጥር ውጪ የሆነ አመጽም ሊነሳ ይችላል። ዳቦ ለሚጠይቁም ቀለሃ ሊታዘዝባቸው ይችላል። ችግር ደርሶ ማኔጅ ለማድረግ ከሚያቅት በእጅ ባሉ ነገሮች ቢያንስ ችግሮችን ለማስታገስ ጥረት ለምን አይደረግም። የኮሪደር፤ የጫካ፤ የሪዞልት ወዘተ እያሉ በፈንታዚ ከሚጓጓዙ። ድግሱም እንዲሁ ማዕቀብ ሊጣልበት ይገባል። የክልል አለቆችን በአጃቢነት ከማሰለፍ የፀጥታ ኃይሎች በቂ ናቸው ጉዞ ካስፈለገ። ለነገሩ ወንበሩ ባዶ ነው ብዬ የፃፍኩት 2011 መግቢያ ላይ ነበር። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ሥርጉትሻ2024/05/27

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅንነት የነጠፈበት ነው።

  የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅንነት የነጠፈበት ነው። ቅን ለሆነ ህዝብ ቅንነት የነጠፈበት ፖለቲከኛ በምን ሂሳብ ሊደማመጥ ይችላል? አይመጣጠንማ! ሥርጉትሻ2024/05/27

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሆደ ሰፊ አይደለም። ግልፍተኛ ነው። ግልቢያም አለበት።

  የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሆደ ሰፊ አይደለም። ግልፍተኛ ነው። ግልቢያም አለበት። ግልፍተኝነቱ ደግሞ ሥልጣን ላይ ሆኖ የዲፕሎማሲ ማህበረሰቡን እንደምን መያዝ እንደሚገባው እንኳን አያውቅም። ለዘርፋ ደም የሚያፈላ እርምጃ፤ ደም የሚያፈላ ንግግር ይደረጋል። ከዛ ፀጋ ይደፋል። ፀጋ ከተደፋ በኋላ ደግሞ ልምምጥ ይመጣል። አብሶ #ካድሬወቹ #በዲፕሎማሲ #ጉዳይ ላይ #እንዳይዘነቁሉ #በህግ #ሊታገዱ #ይገባል ። ፓን አፍሪካኒስት ኢትዮጵያ ዛሬ ያለችበትን ደረጃ የማይመጥናት ላይ ናት። በሌላ በኩል #በዘርፋ #ሙያ #ጠገብ #ኢትዮጵያውያን #በነፃነት #እንዲሠሩ #ሊፈቀድ #ይገባል ። ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ። በተለይ ማህበራዊ ሚዲያ አመጣሽ ሰብዕና ረቂቁን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ እንዲታቀቡ ሊደረግ ይገባል። ኢብን ሙሁራን ቢሆኑም። ኢትዮጵያ በትርፍ ተናጋሪወች ልትለካም አይገባም። ለዚህ ነው እኔ ኢትዮጵያ ለሁላችን ከብዳናለች የምለው። ለአገር ክብር ብርቱ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል። ተቋም አለ። ውጭ ጉዳይ ሚር። የዳበረ ልምድ ያለው። በነፃነት ይሠራ ዘንድ ይፈቀድለት። ከዞግ እሳቤ ተወጥቶ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ሥርጉትሻ2024/05/2

Liyu and me on various issues ...

ምስል

Zerihun and me on various Ethiopian issues ተክሌሻ የምሞግተው ሲጠፋ ደግሞ የሚናፍቀኝ ሰው ነው፨

ምስል

ለልጄ ውዱን ስጦታ ተቀበልኩኝ! #ድንቅ ልጆች #eshetumelese #እሸቱ መለሰ #ማን እንደ ሀገር

ምስል

ጠቅላይ ሚር አብይ እና ቅንነት #ህምም #እምም?

 ጠቅላይ ሚር አብይ እና ቅንነት #ህምም #እምም ? ቅንነት እኮ አዛኝነት፦ አጽናኝነት፤ አይዟችሁባይነት፦ ታጋሽነት፤ አወንታዊነት፤ ታማኝነት፤ ደግነት፤ አሳታፊነት፤ አድማጭነት፤ እራስን ገሳጭነት፤ ህዝብ አክባሪነት፤ ህዝብ ወዳጅነት፤ ወዘተ ነው። እና እሳቸው እና ቅንነት አብረው ኑረው የሚያውቁ አይመስለኝም። ክፋት ክፋነት ጭካኔ በሚመራት ኢትዮጵያ ቅንነትን እንደ መንገድ ማቅረብ የማይመጥን አቅርቦት ነው። ዕውነት ለመናገር የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅንነትን መጥኖት አያውቅም። የላችሁም። ወና። ውዶቼ ቸር ዋሉልኝ። አሜን። ሥርጉትሻ 2024/05/23

#የኢትዮጵያ ሰነደቅ ዓላማ የነፃነት ካሪክለም ነው። #ፋኖ የአማራ ህዝብ ቀይ የደም ሴል ነው። ሁለት ዕርዕሰ ጉዳይ በወጥ የወግ ገበታ አቀርባለሁ።

ምስል
  #የኢትዮጵያ ሰነደቅ ዓላማ የነፃነት ካሪክለም ነው። #ፋኖ የአማራ ህዝብ ቀይ የደም ሴል ነው። ሁለት ዕርዕሰ ጉዳይ በወጥ የወግ ገበታ አቀርባለሁ። መነሻዬ አዘውትሮ አቤቾ (አቤ ቱኩቻው) የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ተውልን፤ ፋኖንም ለእኛ ተውልን ስለሚል በግራፊክ ለመስራት አስቤ ነበር። አመክንዮው እንዳያረጅ እንዲሁ ለመሥራት ወሰንኩ። ያ ሰፊ ጊዜን ስለሚሻ። በነገራችን ላይ መስፍኔም ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ የፋኖ ከሆነ ተፋትቸዋለሁ ሲል አንድ ቃለ ምልልስ ላይ ሰምቻለሁኝ። አመክኒዮ ቢስ ውሳኔም ነው። በዚህ መንገድ የሞገተኝ ሄዷል እና ሌላ መንገድ ካልተሰራ ተኮርኩሜ እቀመጣለሁ ዓይነት። ቀድሞም የውስጥ አልነበረም ፌክ። 1) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ተፈጥሮ የማንም የፖለቲካ ድርጅት፤ የዬትኛውም ሰብዕና #የግል #ንብረቱ አይደለም። ስትፈቅዱት በግርማ ሞገስ ውስጥን ያፀድቃል። ስትታገለው ሚስጢሩ እዬናደ ያሰናብተኃል። ወይንም ከእሳት የገባ ፕላስቲክ ያደርግኃል። ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማው የከበረ የልዕልና ልቅና #የነፃነት #ካሪክለም #ነው ። ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ መንግሥት እንደ ጠላት የሚታዬው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን አስቀይረዋታል። አሻም ያሉ ዓውዳመታት በማስጨነቅ፦ በቀውስ መንፈሳቸውን አርሰዋል። የዓድዋ በዓል ማክበሪያ ቦታ የሠሩት ለዚህ ነው። ለዛውም #ዜሮ ብለው ሰይመው። ይህ ዲስክርምኔሽንም ክህደትም ነው። እንዴት ዓድዋ ድሉ #ዜሮ የሚል ሥያሜ ይሰጠዋል???? ባለቤት አልቦሽ አገር መጥኔ ላንች ኢትዮጵያ። የዓድዋን ዓለም ዓቀፍ መንፈስ ለመንጠቅ እስከ 2023 ሰፊ ዲስክርምኔሽን ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማው ደርሶበታል። በባዕለ ካራማራ፤ በሰማዕታት ቀናት፤ በዓድዋ በዓላት። ብዙም ተገብሮበታል...

ኢትዮጵያ ፓን አፍሪካኒስት ናት። ኬኒያ ሚስጢሩን አላፈሰሰም።

ምስል
      ኢትዮጵያ ፓን አፍሪካኒስት ናት። ጎረቤት አገር ኬኒያም ኢትዮጵያን መሰጠረ። ኬኒያ ሚስጢሩን አላፈሰሰም። በሚስጢሩ ውስጥ ተደላደለ። እንሆ በመባረክ ግሥጋሴውን ቀጠለ። ተመስገን። "የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)

"ጎንደር… ………Tesema Dereje

ምስል
  Tesema Dereje   · "ጎንደር… ……… የዩኩኖ አምላክ የዘር ሀረግ… …የአምደ ፅዮን አጥንት ፍላጭ ፣ የዘረ ያቆብ የሰይፍ በትር ፣የልብነ ድንግል የልጅ ልጅ… የሲሲኒዮስ የአብራክ ክፋይ ፣… ፋሲል …የጠረበሽ የንጉሰ ነገስታት ዙፋን… ዘንፋላዋ ጎንደርርርርርርርር… …… አንዴ… ፋሲል ግንቡ ላይ ፣ አንዴ ቁስቋም አቀበቱ ላይ ፣ አንዴ ፋሲል መዋኛዋ ላይ ፣ አንዴ አባጄሌ ላይ ፣ አንዴ ደብረ ብርሃን ስላሴ ላይ… አንዴ ጎሃ ተራራው ላይ …ብልጭ ድርግም እያልሽ የምታስደነግጭኝ… ጎንደርርርርር ቃሃ ወንዙ ላይ ፣ ሽንታ ወንዙ ላይ፣ መገጭ ወንዝ ላይ ፣ አንገረብ ወንዙ ላይ… አንዴ ብቅ አንዴ ጥልቅ… እያልሽ… የምታቁለጨልጪኝ… ጎንደርርርርርርር ደብረ ታቦር ደጀንሽ… ደረቱን የሰጠልሽ ፣ ጋይንት መከታ ጋሻሽ… ስለ አንቺ የማያመው፣ እስቴ …እርስትና ውርስሽ… ወልቃይት ማተብሽ ፣ አርማጭሆ… የጠላትሽን ግንባር መፈርከሻ የጥይት እርሳስሽ ፣ ጠገዴ መጎልጎያ ጓንዴሽ፣ ወገራ …አጅሬ ጃኖራ …ደም መላሽሽ ፣ ሰሜን ጃናሞራ የንጉስ አሞራሽ… ከፍ ብሎ እየበረረ ዘወትር የሚጠብቅሽ ፣ አለፋ ጣቁሳ… ነጭ ጤፍ የሚሰፍርልሽ ፣ በነጭ በጥቁር አዝሙድ የሚያጥንሽ …ጭልጋ ገለድባ ፣ ጨው ድባ ጫን ድባ… ጥለት መላያዎችሽ ፣ ደንቢያ ወተት እና እርጎሽ… …ጎንደርርርርርርር ቋራ መተማ… ቴዎድርስሽ… ጎንደርርርርርርርር ወረታ ፣አዲስ ዘመን… ፎገራ ፣ እብናት በለሳ… ሰርክ የሚዳብሱሽ ፣ ጣና …መስታውትሽ… ጎንደርርርርርር የገብርየ ማተብ ፣ የትዋበች… ውብ ቃልኪዳን፣ የምንትዋብ… ውብ አዳራሽ…የአዲያምሰገድ ታላቅ ዙፋን ፣ የበካፋ ቅኔ… ገንደርርርርርር ደመቀ …በፍልሚያ አብሪ ጥይት አቅልቶ ያደመቀሽ… ጎቤ የተሰዋልሽ… ……ልባሟ ፣ኩሩዋ …ጎንደርርርርርርር መሰረተ...

"ህልማቸው ሞቷል።" (ጄኒራሉ)

  "ህልማቸው ሞቷል።" (ጄኒራሉ) #የነፃነት #ህልም #መውቲ #አይደለም ። #የነፃነት #ህልም #ሄኖካዊ #ነውና ። ክብረቶቼ ደህና እደሩ። ሥርጉትሻ 2024/05/24