#የኢትዮጵያ ሰነደቅ ዓላማ የነፃነት ካሪክለም ነው። #ፋኖ የአማራ ህዝብ ቀይ የደም ሴል ነው። ሁለት ዕርዕሰ ጉዳይ በወጥ የወግ ገበታ አቀርባለሁ።
መነሻዬ አዘውትሮ አቤቾ (አቤ ቱኩቻው) የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ተውልን፤ ፋኖንም ለእኛ ተውልን ስለሚል በግራፊክ ለመስራት አስቤ ነበር። አመክንዮው እንዳያረጅ እንዲሁ ለመሥራት ወሰንኩ። ያ ሰፊ ጊዜን ስለሚሻ። በነገራችን ላይ መስፍኔም ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ የፋኖ ከሆነ ተፋትቸዋለሁ ሲል አንድ ቃለ ምልልስ ላይ ሰምቻለሁኝ። አመክኒዮ ቢስ ውሳኔም ነው። በዚህ መንገድ የሞገተኝ ሄዷል እና ሌላ መንገድ ካልተሰራ ተኮርኩሜ እቀመጣለሁ ዓይነት። ቀድሞም የውስጥ አልነበረም ፌክ።
የዓድዋን ዓለም ዓቀፍ መንፈስ ለመንጠቅ እስከ 2023 ሰፊ ዲስክርምኔሽን ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማው ደርሶበታል። በባዕለ ካራማራ፤ በሰማዕታት ቀናት፤ በዓድዋ በዓላት። ብዙም ተገብሮበታል። እስከ አሁን እስር ቤት የሚማቅቁ፤ ድብዛቸው የጠፋ፤ የተደበደቡ በርካቶች ናቸው። እኔ አሁንም ኢትዮጵያ በዓድዋ ትግል መንፈስ ውስጥ እንዳለች ይሰማኛል።
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ አማራን እና አማርኛ ቋንቋን፤ ብሄራዊ ቀደምት ሰንደቅ ዓላማን፤ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና ግዕዝን ማዬት አይሹም። ዕውነቱን ለመናገር ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ፓን አፍሪካኒስት አይደሉም። እሳቸው #ፓን #አረቢክ ናቸው። ይህን መስጥረው የያዙት ገመናቸው ነው። አቤ ገራገር ነው እኔ ሳዳምጠው። ነገር ተሎ አይገባውም። ይህ ደግሞ የማይገኝ ሰብዕና ነው። እሱ በቅንነት ያዬውን የሚደውሉለት ሃሳቡን ሲያስቀይሩት አድምጫለሁ። የሆነ ሆኖ ፖለቲካ ውስጥ በመደበኛ ፋንክሽነሪ ሆኖ ስላልሠራ ዕለታዊ ነገሮች ይስቡታል። ይማርኩታል። የብዙ ግድፈቶች ምንጭም ይህው ነው። ፖለቲካ ሞገድ ላይ ከሆነ እንዲህ እና እንዲያ ያደርጋል። የትውልድ ብክነቱ የመስዋዕትነት ግዝፈቱም ጦሱ ይኽው ነው። ከአንድ የዩንቨርስቲ ፕሮፌሰር አንድ የቀበሌ ሊቀመንበር ይበልጣል።
የሆነ ሆኖ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አንድም ፕሮጀክታቸው የኢትዮጵያን መንፈስ ገላጭ የሆኑ አመክንዮችን ይዞ አይነሳም። አይደለም እሳቸው ባለቤታቸው ቀዳማይ እመቤት ወሮ ዝናሽ ታያቸውም። የአባይ ድልድይ ምርቃት የለበሱት ልብስ የጀርመን ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ መንፈስ ነበረው። አካላቸው ውስጣቸው ከኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ መንፈስ የሸሸም ነው። ለዛውም ጎንደሬ? አበስኩ። ጎንደር እኮ ሲታደግባት የዕውቀት ተደሞ የኖኽ መርከብ ናት።
ዓውድዓመት በመጣ ቁጥር ዓዋጅ ነው በመንግሥታችሁ። ሽብርተኞች ተያዙ ነው። በዬጊዜው መንፈንቅለ መንግሥት ሙከራ። ታሪክ እንዲህ ያለ የተርበተበተ፦ የሚያረገርግ መንግሥት ገጥሞት አያውቅም። ግሎባሊም። 2023 የዓድዋ ድል አቤቾም ነበረ። ዘመኑን ልሳሳት እችላለሁ። ብቻ ከውቤ ጋር በባዕሉ ተገኝተዋል። ትንሽ የአቤቾ ይሻላል። የገዳን መለያ የሚለብሰው ውቤ የዓድዋ ድል ብሄራዊ ሰንደቅን እንደምን በመንፈሱ አሽቀንጥሮ እንደጣለው ታዝቤያለሁ። ፎቶውንም ይዤዋለሁ። ለእሱ ከእስር መለቀቅ ስንት ደክሜያለሁ????
ድካሜ ኢትዮጵያን ከነተፈጥሮዋ መስጥሯል በሚል ብሂል ነበር እንደዛ የተጋሁት። ኢትዮጵያን ማግለል ምርቃት ስለሚያስነሳ ፈጣሪ ይከውነዋል። የእኔ ጉዳይ አይደለም ይሄ። በህይወት ኑሬ ግን ይህን መሰል ጉዳይ ማዬቴ ዛሬ ዛሬ ብክነቴን አቅጄ እንድከውን አድርጎኛል። ድምፃችን ይሰማወች ከእነ ሚዲያቸው ድብዛቸው የለም እነ ቲም ሳዲቅ።
ወጡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የበደለው የለም። ያጠፋው የለም። በማርክሲስቶች ግን በጥርስ የተያዘ፦ የተዋጉት እዬተዋጉትም ነው። በተለይ የዞግ ማርክሲስቶች። አቤቾ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ውስጥ ትልልፍ የለውም። ግን እሱ ስፍስፍ ለሚልለት ለአብይዝም አስተዳደር ለፒኮኮ አሳቻ መንፈስ ግን ለእርድ እንዲቀርብ አንፈቅድም። ወዳጆቹ እንቀጥላለን የልዕልና በልቅና #ብራንዳችን አድርገን። ውቤ ግን ለፌክ የሚለጣጥፈውን ቢተው? የበለጠበትን ድፍርስ አሳቻ መንፈስ ጋር ይቀጥል። መብቱም ነው። ለቀኑ ቀን ሲሰጠው ስኬት ይገኛል። ዕድሜ ለኬኒያ ካቢኔ አድምቆታል። ለዚህም ፕሬዚዳንቱ በግርማ ሞገስ እዬገሰገሱ የሚገኙት። ክውን ያሉ። ጠፈፍ ያሉ። በአንደበታቸው በጀስቸራቸው ሳይቀር የታረውሙ ርቱዕ።
2) "ፋኖ ሥያሜውን ተውልን" አቤቾሻ ነው ይህን የሚለው። ኧረ ባክህ?? እንዲያውም የፋኖን ንቅናቄን "ፋኖ ተብዬው፤ ጽንፈኛው" ሲል ነው የባጀው። እኔ ማህፀኔ እንደ ዱባ ይቀረደዳል አንዳንድ ዕርዕሶቹን ሳይ። የሆነ ሆኖ እኔ በፋኖ ጉዳይ ለጠሚር አብይ እንኳን 2010 ግንቦት 05 ጽፌላቸው ነበር። የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎም እራሴን ወክዬ የተጋሁበት ጉዳይ ነው። የአሁኑ ዝምታዬ ትግሉን እንዳልጎዳ ብቻ ነው። እሰበው አቤ እኔ አማራ ሁለት የገዘፈ መከራ ተደቅኖበታል ብዬ ነው እማምነው። 1) የማንነት 2) የህልውና።
የሆነ ሆኖ ፋኖ ለአማራ ህዝብ #ቀይ #የደም #ሴሉ ነው። ሴሉን አውጥቶ ለማህበረ ኦነግ፤ ለማህበረ ፒኮክ ይሸልም የተገባ አይደለም። የቀራንዮ ውሳኔም ነው። እኔ ብዙ ፓርቲወች ይጠይቁኛል አብሬያቸው እንድሠራ። እምመልስላቸው እራሴን አፍርሼ እላቸዋለሁ? ለዚህም ነው በራሴ አሻራ ውስጥ ስክን ያሉ ተግባራትን በጥሪዬ ልክ እምከውነው። ፋኖ እራሱን አፍርሶ #ኦዳወገዳ#አንበሳነቴ ቀርቶ ፒኮክ ይሁን ቢል " ካለ አባቱ ዶሮ ባጓቱ" ይሆናል። አትሰበው አቤ። አይሆንም። አይደረገምም። ፋኖን ኃያል መንፈሱን እና ዲስፕሊኑን ለማህበረ ኦነግ የሚስገብር፤፦ለሞጋሳ ጥምቀት ስጦታ የሚሰጥ እብድ የአማራ እናት አትፈጥርም። አንተ ከፈለግ ግን አቤዋ ፋኖ መሆን ትችላለህ። ከልካይ የለህም። በዜግነት ሥጦታ ማንም መብት የለውምና።
አዬህ አቤዋ አስተዋይ ፖለቲከኛ ጠፍቶ እንጂ የአማራ ህዝብ በርብርቦሽ ይህን ያህል ሙሉ 50 ዓመት በስውርም በግልጥም መገለል ባልተካሄደበት ነበር። ፍፁም ገር፤ የኮፒ ራይት የማይጠይቅ ለጋስ እና ሥልጣኔ የገባው ህዝብ ነው የአማራ ህዝብ። በራስ የመተማመን አቅሙም ዝቅም ከፍም የማይል ምጥን። እና አማራዬ ፋኖነትን በኢትዮጵያ ግንባታ ላይ መንፈሱ እንዲጠቅም ሲያደርግ ያለስስት ነበር።
እኔ የገበሬ አደራጅ ነበርኩ። እኔ የማህበረሰብ አደራጅ ነበርኩ። እምነግርህ በስማ በለው አይደለም። ዳገት ቁልቁለቱን፤ በጋ ክረምቱን ዳጡን ተጋፍጬ ተግቼያለሁ። ካሴናው ጎጃም እናትዋ ጎጃም ጣማቸውን ቀምሰህ ይሆናል። ፋኖነት ለአማራ ህዝብ ጣዕሙ ለዛው ጣዝማ ነው በተፈጥሮው። እኔ እምነግረህ የፋኖን ተፈጥሮ #መንፈሱን ነው።
አሁን ፋኖ የፖለቲካ ድርጅት ይፍጠር፦ፋኖ በአንድ እዝ ይማከል ሲሉ ይገርመኛል። ለዛውም እንዳልቦካ ምርጊት በጥድፊያ እኮ ነው። ኢትዮጵያ በማርኪሲዝም ተመርታ የመጣው ዓይነት ውድቀት ምን አልባትም የፋኖን መንፈስ እስከወዲኛው የሚያከስም ግድፈት እንዳይፈፀም እሰጋለሁ።
የሚገርመኝ ዬአቅሙ መነሻ ፋኖ ሆኖ ፋኖ የሚለው አሰባሳቢ አሻራ ሥሙ እንዲዘለል ተደርጎ ቀጭጮ የቀረ ክስተትም አስተውያለሁ። ካለተፈጥሮ መሪነት፤ ካለልኩ እጀ ጠባብ ይሆናል። ሁሉም በልክህ ልክ ሲሆን ነው የሚያምረው። የፖለቲካ አመሠራረት ይሁን የሠራዊት አመራር በቅጂ ቅጂ አይሆንም። አንዱ በወደቀበት ቢሞከር ያው መሃንነትን መጉረስ ነው።
ፋኖ ገበሬው እራሱን መርቶ በይተብኃል ያቆዬው ልዩ አሻራ ነው ለአማራ። ዲስፕሊኑም ባልተፃፈ ህግ በፈርኃ አላህ እና በፈርኃ እግዚአብሄር ይመራል። ቅኑ አማራ የመኖርን ዘይቤ ተጠቦበት ሰልጥኖ ያሰለጠነባቸውን ትውፊቱ ወጉ ባህል እና ልማዱን በልግሥና ለኢትዮጵያ ከሰጠው አንዱ ፋኖነት ነው። ፋኖነትን አማራ ቢተው ያለ ቀይ የደም ሴሉ መኖሩ ያበቃል።
በውነቱ የአማራ ተባት ትጥቁን ከፈታ ሚስትም አያገኝ። መሳቂያ መሳለቂያ ነው የሚሆነው። ይህን የሚፈቅድ ቆፍጣና አማራ ደግሞ አይኖርም። የጠቅላይ ሚኒስተርህ ጉዞ ደራሽ እና ብልጥነት ያዘለበው ነው። ያ ደግሞ እርቃንን ያስቀራል። አማራ ትጥቅ አይፈታም። እኔን ከብዕሬ መለዬት ይቻላልን? ያለ አቅም መውተርተር ነው።
የበጋ ስንዴ ምን መሰለህ አቤ? ጤፍን እንዲቀናቀን ነው። በጤፍም ቀንተዋል ዶር አብይ። አሁን ደግሞ የሽሮ ካንፓኒ ኦሮምያ ላይ መታሰቡን ሰምቻለሁ? ሽሮ ጎንደር፤ ትግራይ እና ኤርትራ ጠላ ጎጃም ድፎ ሽዋ ወዘተ ፤፤፤
ስንክሳር በቁቤ ተጽፏል። ሚስጢሩ ያለው ግን ከግዕዝ ነው። ጀርመን በርሊን ፍሪ ዩንቨርስቲ፤ ሀንቡርግ ዩንበርስቲ እና ሃይደልበርግ ዩንቨርስቲ ስለምን ግዕዝ ሙያ ሆነ? ሚስጢር ስለሆነ ነው። ስውሩ አስምሌሽን፤ ዲስክርምኔሽን፤ ወረራ እና መሥፋፋት የአብይዝም መለያ ነው። እና ለዚህ አካል ብሄራዊ ሰንደቃችን ሆነ ፋኖነታችን ፈቅደን አንሰጥም። በነገራችን ላይ ባልደራስን ፓን አፍሪካኒስት ሁን እያልኩ ሳያዳምጥ ዛሬ ፋኖ በራሱ ብቃት #ፓን አፍሪካኒስት ሆኗል። ይህ የሰው አይደለም። የፈጣሪ ጥበብ ነው። አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ፋኖን "ጽንፈኛ ወይንም ፋኖ ተብዬው ወይንም ጃውሳ" #ተኖ የቀረ ምኞት ነው። #ፋኖነት #ፓን #አፍሪካኒስትነትም ነው።
ዝምታዬ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ በር ስሌለው ማህበራዊ መሠረቱን ያጣው ሁሉ ስለሚተምበት አለቃነቱንም ስለሚያውጅ እህትህ ፀጥ ረጭ ብዬ በአደብ እዬተከታተልኩ ነው። መንፈሱ የፋኖ ንፁህ ነው። የዝናብ ውሃ። የዝናብ ውሃ ጠበል ነው። እኔ አቁቼ እጠጣለሁኝ። እኔም #ብዕረኛ ፋኖ ነኝ። ግን አለቃ የለኝም። የራሴው እንደራሴው እኔው ነኝ።
የፋኖ መንፈሱ ልበ ሙሉነት በራሱ የሚተማመን አምላኩን የሚከብር ኢትዮጵያ የታተመችበት ነው። ከሰላም አገር በሰላም እና በፍፁም የረጋ ስክነታዊ ተደሞ አለንለት ለፋኖሻ #ጽዑም መንፈስ። እና ፋኖሻን ዘንጠል ዘንጠል ስታደርግ ፀጎራችን የሚቆም፦ ዓይናችን ጉርሽጥ የሚመስል አናብስቶችም እንዳለን እወቅ እሺ አቶ ወንድም አቤቾ።
ክብረቶቼ አቤቾን ለምን ታዳምጫለሽ አትበሉኝ። አንደኛ ህግ ተላላፊ አይደለም። ሁለተኛ የመንግሥቱን መሻት ይነግረናል። ለሙግት ያግዛል። ሌላው እኔ ጥንቁቅ ስለሆንኩ ከዛም ከዛም ስለማል ጠቅለል ያለ ቁጭትም፤ ማቃለልም፤ ትችትም እማገኜው ከአቤዋ ነው። እምፈልጋቸውን ብቻ ለይቼ አዳምጣለሁ። ስለአዳመጥኩም ነው እምሞግተው።
አቤቾ ከምለጥፍልህ ፎቶወች ኢትዮጵያ መኖሯን አስተውልበት። ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ኢትዮጵያ ማጓጓዣቸው ናት። እኔ ኢትዮጵያዊነታቸውንም ይወዱታል፦ ያምኑባትልም ብዬ አላስብም።። ኦነግነታቸውን ገልጠው ቢናገሩም እኔ አይደንቀኝም። ዕድሉን በኢትዮጵያዊነት ኃላፊነቱን ግን ኢትዮጵያን በሚቀናቀን፤ በሚበቀል መልኩ መሆኑ ነው የሚያሳዝነን። ደግሞም ኮንፌዥን እና ኮንቢንስ ያሉትም ለዚህ ነው። እኔ እማምነው ከመስከረም 5/2011 ዓም ጀምሮ አዲስ አበባ ለኦሮምያ ተሰጥታለች ብዬ ነው ስጽፍ የኖርኩት። አሁን የሆነ ቢሆን አልደነግጥም ገዳ እና ወረራ፤፦ገዳ እና መስፋፋት ገዳ እና አስምሌሽን ተፈጥሮው ስለሆነ። ገዳን አዘመኑት ጠቅላዩ። መራራ ነው ከርቤ። ዕውነቱ ግን ይህነው። ለኦነግ ኢትዮጵያ አትጥመውም። ኦነግም ኢትዮጵያን አይመጥናትም። በምን አቅሙ? ምን አለውና????
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
በተረፈ ቸር እንደር። ቸር እንሁን። ቅን እናስብ። መሽቶ ሲነጋ ስለማዬታችን ብለን ቅንነት ይምራን። እንድንመረቅ።
#የግርጌ ማስታወሻ።
የዶር አብይ ደጋፊ ሚዲያወች ሁሉን ታብጠለጥላላችሁ። የሁሉም ሚዲያ ቤተኛ የሆነውን አቶ ገለታው ዘለቀንስ ለምን፣ ስለምን አትሞግቱም አንተን አቤቾን ጨምሮ። አቤ ፎቶወችን እያቸው ያወያዩኃል። ሁሉንም እያቸው የፓርኮችን ትቼ ነው።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23/05/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ