"ጎንደር… ………Tesema Dereje
"ጎንደር… ………
የዩኩኖ አምላክ የዘር ሀረግ… …የአምደ ፅዮን አጥንት ፍላጭ ፣ የዘረ ያቆብ የሰይፍ በትር ፣የልብነ ድንግል የልጅ ልጅ… የሲሲኒዮስ የአብራክ ክፋይ ፣… ፋሲል …የጠረበሽ የንጉሰ ነገስታት ዙፋን… ዘንፋላዋ ጎንደርርርርርርርር… ……
አንዴ… ፋሲል ግንቡ ላይ ፣ አንዴ ቁስቋም አቀበቱ ላይ ፣ አንዴ ፋሲል መዋኛዋ ላይ ፣ አንዴ አባጄሌ ላይ ፣ አንዴ ደብረ ብርሃን ስላሴ ላይ… አንዴ ጎሃ ተራራው ላይ …ብልጭ ድርግም እያልሽ የምታስደነግጭኝ… ጎንደርርርርር
ቃሃ ወንዙ ላይ ፣ ሽንታ ወንዙ ላይ፣ መገጭ ወንዝ ላይ ፣ አንገረብ ወንዙ ላይ… አንዴ ብቅ አንዴ ጥልቅ… እያልሽ… የምታቁለጨልጪኝ… ጎንደርርርርርርር
ደብረ ታቦር ደጀንሽ… ደረቱን የሰጠልሽ ፣ ጋይንት መከታ ጋሻሽ… ስለ አንቺ የማያመው፣ እስቴ …እርስትና ውርስሽ… ወልቃይት ማተብሽ ፣ አርማጭሆ… የጠላትሽን ግንባር መፈርከሻ የጥይት እርሳስሽ ፣ ጠገዴ መጎልጎያ ጓንዴሽ፣ ወገራ …አጅሬ ጃኖራ …ደም መላሽሽ ፣ ሰሜን ጃናሞራ የንጉስ አሞራሽ… ከፍ ብሎ እየበረረ ዘወትር የሚጠብቅሽ ፣ አለፋ ጣቁሳ… ነጭ ጤፍ የሚሰፍርልሽ ፣ በነጭ በጥቁር አዝሙድ የሚያጥንሽ …ጭልጋ ገለድባ ፣ ጨው ድባ ጫን ድባ… ጥለት መላያዎችሽ ፣ ደንቢያ ወተት እና እርጎሽ… …ጎንደርርርርርርር
ቋራ መተማ… ቴዎድርስሽ… ጎንደርርርርርርርር
ወረታ ፣አዲስ ዘመን… ፎገራ ፣ እብናት በለሳ… ሰርክ የሚዳብሱሽ ፣ ጣና …መስታውትሽ… ጎንደርርርርርር
የገብርየ ማተብ ፣ የትዋበች… ውብ ቃልኪዳን፣ የምንትዋብ… ውብ አዳራሽ…የአዲያምሰገድ ታላቅ ዙፋን ፣ የበካፋ ቅኔ… ገንደርርርርርር
ደመቀ …በፍልሚያ አብሪ ጥይት አቅልቶ ያደመቀሽ… ጎቤ የተሰዋልሽ… ……ልባሟ ፣ኩሩዋ …ጎንደርርርርርርር
መሰረተ ሀገር…ጎንደርርርርርርርር!!!"
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ