ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ሌት እና ቀን ጉዞላይ፤ ግብረ ሰላም ላይ፤ ፕሮጀክት ምርቃ ላይ ናቸው።

 ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ሌት እና ቀን ጉዞ ላይ፤ ግብረ ሰላም ላይ፤ ፕሮጀክት ምርቃ ላይ ናቸው። 

እኛን ግን ሊያሳምኑ አልቻሉም። ሳናውቃቸው አመናቸው። ስናውቃቸው ማመን ተሳነን። አንዱ የመጋቢት 24/2010 ንግግራቸው ገድል ሠርቶ ሚሊዮኖች ተቀበሏቸው። ቀጠለ ወይ ስንል ታሪክ ሆኖ ነው የቀረው። 

አስታውሳለሁ አንድ የዩንቨርስቲ ሰው ኢትዮጵያን 32 ጊዜ በንግሩ ተጠርቷል ሲሉ እጅግ ነው የገረመኝ። 30 ዓመት ዞግ ርዕዮቷ በሆነች አገር ይህን ያህል ለአገር ስያሜ ቃናዊ ዕድምታ መኖር ከድንቅ በላይ ነበር። 

ነገር ግን ቃሉ ፋንታዚ ሆኖ ታንቆ ነው የቀረው። ኬኒያን እንዲጎበኙ ልዑክ ተልኮላቸው ነበር። የኬንያ ሊቃውንት ለአብይ እንፀልይ የሚል ፕሮግራም ሠርተው ነበር። 

ኬኒያን ሲጎበኙም 21 ጊዜ የደስታ ርችት ተተኩሶላቸው ነበር። ኬኒያውያን ኢትዮጵያ መራዊት እንድትሆን ምኞት ነበራቸው። ያን ፀጋ ማኔጅ ማድረግ ተስኗቸው ለሳቸው የተሰጠውን ግርማ ሞገሥ ኬንያ ወሰደ። ስለምን ኢትዮጵያዊነትን ስለመሰጠሩ። 

ኢትዮጵያዊነትን በግልጥም በስውር ሽሽቱ ያወላልቃል። 

"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ሥርጉትሻ 2024/05/24 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።