ማስተዋላቸውን #ላላፈሰሱ #ማህበረ #አብይዝሞች።
አብይዝም ሆኖ ማስተዋል እንዴት የምትሉ ወገኖቼ ትኖራላችሁ። አወንታዊ፤ ቅን፤ የበዛ ትዕግሥት ያላቸው ሆነው አሁንምጊዜ ይሰጣቸው የሚሉ ወገኖች አሉን።
በተለይ ሳይለንት ማጆሪቲው ማስተዋሉ የበዛ ነው። ውስጡን ሲያገኝ ሆ ብሎ ይነሳል። ዕይታዬ እነሱንም ይጨምራልና ነው። በመደዳ፤ በጅምላ ሁሉንም መኮነን አያስፈልግም። የሚደግፋ ግን ሰብዕናቸው ጠፈፍ ያሉ ወገኖች አሉን። ይህን በስክነት የፖለቲካ አረዳድ ሂደት የሚገኝ ብሂል ነው።
ከልባቸው ኢትዮጵያኒዝምን የተቀበሉ የኦህዲድ ኦነግ ደጋፊወች ዝም ብለው በትውልድ ግንባታ ላይ የሚሠሩ ሚዲያወችን ይዩ። በተገኜው የብልጭልጭ አታሞ ከሚፍለቀለቁ።
የጥበብ ዓውዱን ለማስፋት ሁሉም የመንግሥት ሚዲያወች በተለያዬ ሁኔታ ይሠራሉ። ግን ስቴጁን ተመልከቱት። የብርሃን አርት የሚጠቀሙትንም እዩት።
ኢትዮጵያ #ሳይለንት #ዲስክርምኔሽን፤ #ሳይለንት #ኔግሌሽን እዬተፈፀመባት ስለመሆኑ ማስረጃ ታገኛላችሁ። የመድረክ ቅንብሩ፤ የቲሙ አልባሳት ሁሉ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ትውር እንዳይልበት ተጠንቶ ነው የሚዘጋጀው። ቅንጥብጣቢ ጉዳዮች ሳይቀሩ ከኢትዮጵያ መንፈስ ይርቃሉ። የተወዳዳሪወች የፕሮፋይል ፎቶ ሰንደቁን ካከበረ ሃይለኛ ዱላ ያርፍበታል።
ለነገሩ የሚዲያው መሪወች #የኢንሳ ሰወችም ናቸው። ማለትየዶር አብይ የንሰኃ ልጆች ናቸው። ዓላማው ዳብል ተግባር ሚዲያው ይከወን ዘንድ ታስቦ የሚከወን ነው።
ተወዳዳሪወች በዚህምፈተና ውስጥ ናቸው። ምክንያቱም ሲያሸንፋ ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸው ለሥርዓቱ ኢንቤስት ያደርጉ ዘንድ ውስጣቸው የዘለቀ ጥናት ይከወንበታል። ልክእንደ አንድ ኦብጀክት። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል ቅንነት ጎደል ነው። ለዛውም የኦነግ መንፈስማ መደበኛ ጠላታቸው ኢትዮጵያ ናት። ይህ አጠቃላዩን ሲስተሙን እንጂ አልፎ አልፎ ኢትዮጵያን የማይገፋ በመንፈሳቸው አመራሮች ሊኖሩ ይችላሉ።።
የሆነ ሆኖ ሰላይ የሚዲያ አለቃ መኖር ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዊነት ቢሆን በበጄ። አይደለም! #ኢትዮጵያን #ለመፋቅ፤ #ለመፈቅፈቅም ነው። ለነገሩ ለጥበብ ዓውድ ሰላይነት ነፃነትን ስለሚቀማ ብዙ አደጋ ያስከትላል። ስጋት ፍርሃት ለጥበብ ዲዲቲ ነው።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
25/05/2024
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ