መሪነት ስጦታ ነው። የገብያ ህግ አይገዛውም።
መሪነት ስጦታ ነው። የገብያ ህግ አይገዛውም። ቅብዓ ከገብያ ህግ ውጪ ነውና። መቀባት #ዊዝደምን መታደል ነው። ዊዝደም የሰማዩን የምድሩን የባህላዊ ህግጋትን ካለመዳፈር አህዱ ይላል። ጥንቁቅነት። የመሪነት አቅም ምንጩ #ጥሞናዊ ርግታ ነው። ጥሞናዊ ርጋታ የአምላካችን የአላኃችን ፈቃድ የጥዬቃ ጊዜ ብቻ ሳይሆን እራስን #የመገሰጪያ ጊዜም ነው። እራስን ለማረም ድፍረት እንጅ ፈሪነት አያዋጣም። መሪነት ሕይወትን የመረዳት #ፍጥነትን ፤ #ክስተቶችን በጥልቀት የማገናዘብ ብቃትን፤ የዘመኑን #ሉላዊ የፖለቲካ ባህሬን የማጤን ክህሎትን፤ ብቁ የማገናዘብ አቅም ከማድመጥ ተሰጥዖ ጋር ይጠይቃል። መሪነት ታምራታዊነት አይደለም ለገኃዱ ዓለም ዕውነታ። መሪነት በግል እና በጋራ አቅም ሰልጥኖ መፍለቅን ይጠይቃል። መሪነት ቲም ሊደርነት ነውና። ሥርጉትሻ2024/07/19