"ኒው ዮርክ ባቡር ጣቢያ ውስጥ አንዲት ሴት በእሣት ተቃጥላ መገደሏ ተሰማ" BBC እኔ የሚያስፈራኝ ይህ ነው።
እኔ የሚያስፈራኝ ይህ ነው። ክፋ ሃሳብን ያነገቡ ሰብእናወች ዓለማችን የጥፋት እና የመከራ በማድረግ ፈሪ ትውልድ ይሻሉ። የጭካኔው ዓይነት ይዘገንናል። ይህን ጭካኔ የሚገታ ወይንም የሚመክት ተቋም አለማችን ምን አላት? የሚያስፈራኝም ይሄ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/c23vezjzgzdo "ኒው ዮርክ ባቡር ጣቢያ ውስጥ አንዲት ሴት በእሣት ተቃጥላ መገደሏ ተሰማ" 23 ታህሳስ 2024, 07:49 EAT "በኒው ዮርክ አንዲት ሴት ባቡር ጣቢያ ውስጥ በእሣት ተቃጥላ መገደሏን ተከትሎ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ታውቋል። የፖሊስ ኮሚሽነር ጄሲካ ቲስክ እሑድ ዕለት የተፈፀመውን ጥቃት "አንድ ሰው ሌላ ሰው ላይ ከሚፈፅማቸው እጅግ ዘግናኝ ወንጀለኞች መካከል አንዱ" ሲሉ ገልፀውታል። ኮሚሽነሯ እንደገለፁት የተገደለችው ግለሰብ 'ስቴሺነሪ ኤፍ' ከተባለው ጣቢያ ወደ ብሩክሊን እያቀናች ሳለ ነው አንድ ሰው መጥቶ በእሣት መለኮሻ (ላይተር) ልብሷን ያቀጣጠለው። ግለሰቧ እዚያው ባቡር ጣቢያ ውስጥ ስትሞት ተጠርጣሪው በተማሪዎች ጥቆማ መሠረት ሌላ ባቡር ሲሳፈር በቁጥጥር ሥር ውሏል። ፖሊስ እንዳለው ስሟ ያልተጠቀሰው ሴት እሑድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ጥዋት 1፡30 ገደማ ነው ባቡር ስትሳፈር አንድ ሰው የተጠጋት። ከጥቃቱ በፊት በሁለቱ መካከል ምንም ዓይነት ንግግር አልነበረም ያለው ፖሊስ ሁለቱ ሰዎች ይተዋወቃሉ ብሎ እንደማያምን አስታውቋል። በባቡር ጣቢያ ያሉ የፖሊስ መኮንኖች እሣቱን ለማጥፋት ሲረባረቡ ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠረው ግለሰብ ከሥፍራው ሮጦ ማምለጡ ተሰምቷል። "በባቡር ጣቢያው በላይኛው ክፍል ላይ የነበሩት ፖሊሶች በሽታ እና በጭስ አማካይነት እሣት መነ...