መካሰሱ ለሁለቱ መንግሥታት አይጠቅምም። አደብ ገዝቶ በጭብጦች ላይ ቅናዊ ውይይት አድርጎ ትውልድን ከዘላቂ ስጋት አላቆ የውስጥ ሰላምን የሚያረጋግጥ ብልህ አመራር ይጠይቃል። ወጣትነት መንፈስ የሚፈታተነው ግብግብ ኪሳራ ያሳፍሳል። የሥርጉትሻ ዕይታ። 19.03.2025 ------------------------------------------------------------ «ኤርትራ በትግራይ ክልል በተፈጠረው ቀውስ "ምንም ሚና" የለኝም አለች» BBC https://www.bbc.com/amharic/articles/c17q2zr00k5o የፎቶው ባለመብት, Yemane G. Meskel/X ከ 7 ሰአት በፊት «የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልህ፤ አስመራ በህወሓት እና በትግራይ ክልል "ጊዜያዊ አስተዳደር እየተካሄደ ባለው ግጭት" ውስጥ "ምንም አይነት ሚና" እንደሌላት ተናገሩ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ "የጎረቤቶቿን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እንድታከብር" ግፊት እንዲደረግባት ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ጥያቄ አቅርበዋል። ኦስማን ይህንን የተናገሩት ማክሰኞ፣መጋቢት 9/2017 ዓ.ም. መቀመጫቸውን አስመራ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት በሰጡት ማብራሪያ እንደሆነ የሀገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ አስታውቀዋል። ማክሰኞ ጠዋት በኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ማብራሪያ የተሰጣቸው የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት፤ "አምባሳደሮች" እና "የዲፕሎማቲክ ኮር አባላት" እንዲሁም በሀገሪቱ "እውቅና የተሰጣቸው የተባበሩት መንግስትታት ድርጅት ተቋማት አመራሮች" መሆናቸውን የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገልጸ...