ነፃነት ለአብይ እና ለቤተሰቡ!
ዛሬም ዝምታ ነፃነት ለዶር አብይ አህመድ!
„ኤርምያሰ ወደ ጉድጓድ ቤት ወደ ጓዳዎቹ ገባ፤ ኤርምያስ በዚያ ቀን ከተቀመጠ በኋዋላ ንጉሡ ሴዴቅያስ ልክ አስመጣው፤ ንጉሡም በቤቱ፤ በውን ከእግዚአብሄር ዘንድ የሆነ ቃል አለን ብሎ በቆይታ ጠዬቀው።“
ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፯ ከቁጥር ፲፮ እስከ ፲፯
ከሥርጉተ© ሥላሴ 18.08.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? አሁንም ድህረ ገፆችን ጎበኘሁኝ ምንም ነገር የለም ዝምታ ሰፍኖበታል፤ እንዲያውም ሌላ የማጠናከሪያ ጹሁፍ ባ ኢንግሊዘኛ አነበብኩኝ። በዝምታ እንድንዘልቅ ያን የሚያጠናከር ነው። አሁን አጀንዳችን ሊሆን የሚገባው ዶር አብይ አህመድ ሆነው ሳለ እኛ በአርቲ ቡርቲው ስንፋለጥ እንገኛለን።
እርግጥ ዛሬ የተሻለ ህልም አይቻለሁኝ። ነገር ግን እኛም ከተኛን ቀጣይ ነው ጨለማው። የአሜሪካ ኢንባሲ በኢትዮጵያ ቃላ አቀባይ የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት ሲገኝ የአጠቃቀሙ ሁኔታ ነበር የገለጸው፤ አቶ አህመድ ሽኔ ደግሞ ለውጡ ሊቀለበስ አይችልም የሚል መግለጫ ሰጥተዋል። ይህ ሁሉ አድበስብሶ ለማለፍ ነው።
ዶር አብይ አህመድ እገታ ላይ ናቸው። እባካችሁ መላ ፈልጉ። እባካችሁን ለነፃናታቸው ታገሉ፤ እባካችሁ እንቅልፍ አንተኛ ኢትዮጵያ በታሪኳ ይህን መሰል ዕድል አግኝታ አታውቅም። በዚህ የሚከፉ፤ የሚጨነቁ፤ በዚህ የሚጠበቡ ቅኖች ናቸው።
ትናንትም ቅኖች ነን አብረን ከጎናቸው የቆምነው። ዛሬም ማድረግ ያለብን ይሄውን ነው።
ቢያንስ ወያኔ ሃርነትን ያህል ጠላት አስቀምጠን ይህ ሁሉ ቀን ከሰው እንዳልተፈጠረ ያ ሩህሩህ ፍጡር እንዴት ዝም ይባላል? እባካችሁ እንድረስለት።
ነፃነት ነፃነት ነፃነት ነፃነት ለዶር አብይ አህመድ። እባካችሁ ሌላ አጀንዳ አይሁን አጀንዳችን ነው። እዛ የሄዱትም እኮ ሊቀቀሉ ነው። የደገፈው ሁሉ ጭንቅ እዬመጣበት ነው። ህዝብን ማዳን ጭምር ነው።
ዶር ደብረጽዮን ገብረሚኬኤል ሰሞኑን የሰጠው „ጉልበት ሳይኖር ተራራ እወጣለሁ ማለት፤ መነሻውን ያለወቀ መድረሻውን አያውቅም፤“
ሌላው ቅድስት ተዋህዶ ጥቃቴን አልተቋቋመልኝም መንግሥት ብላ መግለጫ እንድታወጣ የተደረገበት ምክንያትም ያው ዶር አብይ አህመድ በሙሉ ሥልጣን ያለ አድርገው ቸልልተኛ አስደርጎ ለማቅረብ ነው።
ይሄን መገመት እንዴት ያቀታል። ወስጣችሁ እንዴት አርፎ ይተኛል። እስኪሞት ድረስ ነው የሚጠበቀው፤ ወይም በእልህ ልጆቹን ወይንም ባለቤቱን እስኪያጣ ነውን። የቁም እስረኛ ነው አብይ አህመድ።
ነፃነት ነፃነት ነፃነት ነፃነት ለአብይ አህመድ!
ነፃነት ለአብይ እና ለቤተሰቡ!
የኔዎቹ እባካችሁ ልብ ይኑረን።
ቸር ወሬ ያሰማን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ