በእብለት ተበጥቶ!
ማህበረ ናዳ በወናው ማሳ ቀርንቶ!
„ቁጣዬ በእረኞች ላይ ነድዷአል፤ አውራ ፍዬሎችንም እቀታለሁ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሄርም የይሁዳን
ቤት ጎብኝቷል፤ በሰልፍም ውስጥ እንዳለ እንደ ክብሩ ፈረስ ያደርጋቸዋል።“
ትንቢተ ዘካርያስ ምዕራፍ ፲ ከቊጥር ፫ እስከ ፬
ከሥርጉተ© ሥላሴ 18.08.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
ምን አለው እና የብትክ ቀረርቶ¡
የሰባራ ሰንጣራ የሞገድ ሠርግ ቀበቶ።
የስርዝ ድልዝ ቋቶ
በወናው ማሳ ቀርንቶ።
የሥም እንካ ስላንትያ ድርጎ
የወንፊት ግድፍት ብልጎ።
የጡዘት እርቃን ተባዝቶ
ዓመት እስከ ዓመት ተዋርጭቶ።
ተፈራግጦ ሲነሳ ደንግጦ
ተላልልጦ ተገምጦ አይዋ ልጦ!
በደመምን ተውጦ
በትካዜ ጎርብጦ
ያ እፉኝት ሰላቢው ወረንጦ።
በድጥ ማጥ ተፈናጦ
በፈንጣጣ ተንጣጥቶ
በምንም ቀርቶ!
በጎርምጥ እባጭ ተሰልቆ
መውጫያ ሲያጣ ተደብቆ
በፍርስቱ ናዳ ለቆ።
የእፉኝት ጢንዝዝ ተቋንጥቶ
አለሁ ይላል ተዝካሩ ላይ ሞቶ።
ይሄው ታዬ በእብለት ሙሽርነት ተበጥቶ
የውርዴው ኪሳራ አቦካቶ
በዬለም ተቦክቶ ታካቶ።
ሰላም የማይሰጥ እንቶ ፈንቶ
በግጭት ህውከት ተዳምቶ
ቀበቶውማ መች መክቶ?
ቀረ ፈሶ አንብቶ ...
የእብለት ሳይበር ጎርንቶ።
- · ሥጦታ ለማህበረ ቅጥፈት። 19.04 ደቂቃ።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ