ነፃነት ለአብያዊ መንፈስ!

ለአገር እንባ የነበርክ መፈወሻ!

ቅዱስ አባቴ ሆይ! የት ሄደ የብጹዕነተዎት አምላክ?
ከቶ ከመንበሩ የለምን?! 

"ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ"
 ትቢተ ሐጌ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፭

ከሥርጉተ©ሥላሴ 18.08.2018 
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።



ነፍስ ሲጨንቃት ስለ አገር ስታነባ
ማቆሚያ አጥቶ ሆዴ ሲባባ
የነፃነት ልዩ አባባ
ፍሬ አፍርቶ ከልብ ሲገባ
ነፍስ ተገዘቶ ሁሉን አግባባ።

ያ የነበረ ግን አሁን የሌለ
የሰማይ ያህል የራቀን 
ወስጣችን ገብቶ በሰናይ የነኘን
እሱ ነበር ሥጦታ
የመንፈስ ቅኔ ጌታ
የመሆን አዝማራ የሁለመና ገበታ።

ሳናስበው ብቅ ብሎ ነፍሳችን ገዝቶ
ወጣ ገባውን አስማምቶ በህሊና ለምቶ
ስለህሊና ለህሊና ቃል አስምቶ
ቃል ገብቶ የውል አባት ያ ሁነኛ
የዋቢነት ባላ የእኛ።

የሁሉን ጓዳ ደባብሶ ለፍስሃ ተግቶ
ጉድፍ ጠርጎ፤ ጎናጣውን ሊያቃና አቃንቶ
ቅንነት ሊዋውል አስልቶ
እድሜ ሙሉ ተሰናድቶ
ነበር እሱማ ስለሁሉም ተግቶ።

የለም አሁን ከቅርባችን
ያ አውራው ንብ ደርባችን
መንበራችን …
እንደናፈቀነው
እንደ አጓጓን
እንደሳሳነው
የባተለው፤ ያ ሳተና ብረቱ
የሰጠን ለኛ ሳይሰት ስልቱ
ጥሩነቱን ሳንጠግበው ሳንሰናበተው
በክፉዎች ወጥመድ የተበላው
ደጉ አብይ ከቶ የት ነው ያለው?

ያ ቅን ደካሚ አገር አለኝ ብሎ ሲማስን
ሲወድቅ ሲነሳ  
እናቱን ከእንቅልፏ  ሊያስነሳ
አያታክቴ አንደ ባከነ ላይወሳ ላይነሳ
ነገ ቀድሞት እንዲህ ሊረሳ?
እንዴትስ ይረሳ? ስለምንስ ይረሳ?

ለእኛ የሆንክ የአብርሃም በግ
አንተ ንጹህ የሆንክ ደግ።
ያ ባተሌ ብላቴና
የተግባር ምስክር ገናና
የቸርነት አባወራ
የደግነት የአብ ሥራ!
አስራቂ የልጅ አዋቂ
የፈግግታ መሰረት አንጸባራቂ
የቀን ከሌት ዳማቅ አብሪ
የተስፋ ጥገት ብርቱ መሪ!

ዋ! አብይነት የውስጥነት ጎመራ
የብቃት ብራ
የትህትናህ ልዩ ሥራ
ትናራለህ ከነፍሳችን ስታበራ።

ለኢትዮጵያ እናቶች ብርቱ ልሳን ለዶር አብይ አህመድ ይሁንልኝ።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።

 



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።