ቅርሻ!
ቅርሻ!
„አባቶቻችሁ ወዴት ናቸው? ነብያትስ ለዘላለም በሕይውት ይኖራሉን?“
ትንቢተ ዛካርያስ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፬
ከሥርጉተ©ሥላሴ 18.08.2018
ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።
የውሸት ቀዳዳ ዋሻ
ሁልጊዜ በግምሻ
የፖለቲካ ነጋዴው የዘመኑ የመዘላባድ ቅምሻ
ምንግዜም እየሸቀጡ ለማምሻ
የቀዳዳ ቅርሻ!
ሁልጊዜ ማበሻ፤ የነዳላ አስሳ
የጦስ ልምሻ!
የተልባ ስፍር መስፈሪያው ፍርሻ
አንዱን ሲያሸልክ ሲነፍስ ለመቆስቆሻ
የወጀብ ስፍር የቀመኞች ድርሻ
ያፍ ወለምታ የማይነጥፍ ዓመት ድገሙን መቆራቆሻ
ቆሻሻ!
የጭድ ክምር ድንኳን ጥቅርሻ
የጎደሎ ቀን እጣ የፍስሽ አለሎ መዋቀሻ
በሌለበት የአልሁ ባይ መደቆሻ።
ያልተወለደ አንጀት የጭካኔ ማርከሻ፤
የዕብለት አንቱታዊ ማፈሰሻ
የምናምንቴው አርቲ ቡርቲ ማሳሻ።
የማያባራ የሞላጮች ትናጋ መቀየሻ
ክምር የድርቆሽ የባዶ ሜዳው አያልቅ ጥቃሻ
የለመደበት የናዳ ፍርሻ!
- · ሥጦታ ዘመን ተዘመን በውሸት ድርድር ለተከመሩ ገበርዲን እስተከራበቱ ይሁንልኝ። 18.20
ውሸታሞች የሚያልቁበትን ቀን ፈጣሪ ያምጣልን!
አሜን ይሁንልን! ይደረግልን!
የኔዎቹ ልባሞቹ ቅኖቹ ኑሩልኝ!
ማለፊያ ጊዜ!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ