የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ መዳረሻችን ለፖለቲካ ሥልጣንም ይሁን።

 

ንኳን ወደ በቡሽ ብሎግ በሰላም ጣችሁልን።

 


የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ መዳረሻችን ለፖለቲካ ሥልጣንም ይሁን።

 

"የቤትህ ቅናት በላኝ።"

 

የአማራ ልጅ ከአንጋችነት እና ከአጃቢነት ይውጣ። በፍጥነት። የትግል አቅጣጫችን እንደዚህ ጭምልቅልቅ የሚሉበትን ዝልግልግ እብቅ አመራር ታግሎ ወደ የቀደመ ሥርዓታችን ገብተን ማስተካከል ግድ ይለናል።

ለህግም፣ ለስርዓትም ሊሆን የማይችል የእንሰሳዊ ሥርዓታቸውን ለራሳቸው ይጎናፀፋት። እኛን ግን መምራት አይችልም። ፈፅሞ።

 

በቃ! የምንለው ዝርክርኩን ሥርዓት ነው። ዝርክርኩን ሥርዓት በቃን! ሥንል እኛ አቅሙ አለንና ገብተን መሥራት እንደምንችልም ህሊናችን በሁሉም መስክ ማሰናዳት ይኖርብናል።

ከስውሩም፣ ከግልፁም ኦነጋዊ ቅራቅቦን ቅልቅል የጠራ መስመር፣ የለዬለት የኃይል አሰለፍ መፍጠር ግድ ይለናል። እምንታገለው #ለጠቅላይ ሚኒስተርነት ቦታ ሊሆን ይገባል። እምንታገለው ለመሠረትናት ለአዲስ አበባ ከንቲባነት ሊሆን ይገባል። የግድ ድርጅት አያስፈልግም።

የዬትኛውም ድርጅት አባልም አካልም ያልሆነ እራሱን ለሚመጥነው ቦታ ማሰናዳት ይገባዋል። ድርጅቶች ብቻ እንዳይመስላችሁ መንፈሳቸውም ምርኮኛ ይሆናል።

ስለዚህ ጎደሎ እና እንከን እያስታመሙ፣ በሰባራ ሰንጣራ ጊዜ ማባከን አይገባም። አቅማችን ቆጥበን በሥርዓት ማኔጅ ማድረግ ግድ ይላል። የእኛን ለእኛ። 

ዜግነት ምድረበዳ ላይ ሆኖ ስለእሱ ብንጮህ ዋጋ የለውም። እሱን ለማስከበር ከራስ ጉዳይ መነሳት ግድ ይለናል። አደናቃፊወችም የእርጎ ዝንብ አትሁኑበት ለአማራ ህዝብ ተስፋ። አቅም አብጁ። ትግል የመና ሥጦታ አይደለም። የሥራ ውጤት ነው።

ከእንግዲህ በአማራ አቅም ተንጠላጥሎ ማገዶነት በቃ ሊባል ይገባል። የአማራ ልጅ ለዬትኛውም የኃላፊነት ቦታ የምትመጥን በአካልም በመንፈስም ተሰናዳ።

ከእንግዲህ ከማህበረ ህወሃት፣ ከማህበረ ኦነግ የምንጠብቀው የሥልጣን ፍርፋሪ ሊኖር አይገባም። የአማራ ልጅ 60 ዓመት ሙሉ የተቀለደብህ ይበቃል።

በአቅማችን ልክ ኢትዮጵያ እምትፈልገን ከሆነ ቦታውን መያዝ ይኖርብናል። ዶር ተሾመ ነው የሚባሉት የቀድሞው ፕሬዚዳንት? የኢጋዱ ፀሐፊ ገዳይ ዶር ወርቅነህ ገበዬሁ ፀሐፊ፣ የኬኒያን ብሄራዊ ምርጫ ለመታዘብ ዶር ተሾመ፣ ለአህጉራዊው፣ ለብሄራዊው፣ ለዓለም ዓቀፋዊው ውክልና ለሁሉም ኦነግ።

አማራ እዬታደነ ይረሸናል፣ ይታሰራል፣ ይገደላል። እኛ ደክመን በተገኜ ስልጣን የኦነግ ፈንጠዝያ። ቢችሉበት በሆነ። ሙርቅርቅ። ፍርክርክ።

ልብ ግዙ አማራውያን! ከእንግዲህ ተጋድሏችን ወደ አባቶቻችን የክብር፣ የልዕልና፣ የልቅና መዳረሻ ጉዞው ወደ ቤተ -:መንግሥት። አሟሟቂነት ይቁም! ለዚህ የተበቃው የአባቶቻችን የዊዝደም ጥሪት ነው።

ማን ባበጃት አገር ማን አሳዳጅ፣ ማን ተሳዳጅ ይሆናል። ይፋዊ ጆኖሳይድ የሚካሄድብን ህዝቦች ስለሆን ብዙ አማራጮች አሉን።

ቅድስት ተዋህዶስ ትሰሚያልሽ? ፍርፋሪ ከሜጫ፣ ቅርጥምጣሚ ከእሬቻ፣ እንጥፍጣፊ ከኦዳ? ሚሊዮን ነሽ የሰማይ እና የምድር ድልድይ። አንችም ለፖለቲካ ሥልጣን ታገይ።

ልጆችሽን እያሳረድሽ፣ ቤተ መቅደስሽን እያስደረመሽ ዝምታሽን ቅደጅው። በቃ ብለሽ ከእኛ ጋር ተነሽ። መጠጊያሽ በከፋሽ ጊዜ ጥግሽ ያው አማራዬ አይደለምን? ማን ደረሰልሽ? ተወረሻል። እሰቢበት።

 

አጃቢነት ይቁም!

የሰው ቤት ማደራጀት ይቁም!

አደራጅቶ ማስረከብም ይቁም!

ለራስ ድል ብቻ እንትጋ።

አቅማችን ለአቅማችን ብቻ።

 

ይህን ስል እኛነትን የዋጡ በቁጥር ያነሱ ግን አደጋ ከፊት ለፊት የሚጠብቃቸውን የእኛወችን ሁልጊዜም ፅንሳችን ሊሆኑ ይገባል።

 

የሸሸነውን የፖለቲካ ሥልጣን፣ አቅም ኃይል፣ የኢኮኖሚ አቅማችን ሙሉ ለሙሉ ሥራ ላይ ካስገባነው የሚሊዮኖችን ትንፋሽ ፈዋሽ እንሆናለን።

 

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

19/07/2022

አማራነቴ ፍካልኝ የእኔ አድዮ አብብልኝ!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።