ሆደ ባሻወች የእኔ አምሳዬ ናቸው።


ንኳን ወደ በቡሽ ብሎግ በሰላም ጣችሁልን።

"የቤትህ ቅናት በላኝ።"



ከማክበር በላይ ውስጤ የተለዬ ነው። ለእኔ የቤተሰብ መርዶ አይነገርም። በጥባጭ ነኝ። እንደ ድክመት ከተቆጠረ ይህ ዓይነታው ድክመቴ ነው። መጽናናት የማልችል ነኝ። ለአጽናኞቼ ሲዊዞችም፣ ጀርመኖችም ጓደኞቼ የቸገራቸው ይኽው ነው። ለዚህ ነውበኢትዮጵያ ጉዳይ እኩል የሚያዝኑት እንደ እኔው።

 

#ልነሳ

 

የአመራር ብቃት ቲም ሊደርነት ነው። እናትነት ሲታከልበት ያብባል። ይህን ያጣች አገረ ኢትዮጵያ ይህ ይርባታል። የአማራ ህዝብን እንዲህ እቅፍ አድርጎ የሚያጽናና እናት ይሻል። የአማራ ህዝብ እናት የለውም። ልጅ ግን አግኝቷል። ዶር ደሳለኝ ጫኔ።

የልጅነት እና የእናትነት ቃናው ለዬቅል ቢሆንም። እናታዊነት ለወንዶችም ይሰጣል። እናት ሆዱ ይባላሉ። ሴትም ሆኖ ጨካኝ አለ። እንደ ወሮ ዳግማዊት ሞገስ። እንደ ዶር ሂሩት ካሳ አይነት በህልፈቱ የሚሳለቅ። እንደ ወት ብርቱካን ሚዲቂሳ የጭካኔ ዬውስጥ አርበኛ። ቂመኛም። በቀለኛም።

ስስ ልብ ያላቸው ተባዕት ይሁኑ አንስት ግጥሜ ናቸው። ሆደ ባሻወች የእኔ አምሳያ ናቸው። የተለዬ ሰብዕና ነው። ለዚህ ነው አባ ቅንዬ አቶ ሠለሞን ኃይሌ ሲጠፋብኝ የት ሄዱ የምለው። አዛኝነት ከመነነ ጫካነት ምድሩ ይወርሰዋል።

ግን እንዴት አደርን በድጋሚ። አጣዬ፣ ኤፍራታ፣ ሽዋ ሮቢት እንዴት ናችሁ? ሁላችሁም።

በእህቴ አትሌት ደራርቱ ቱሉ ስፍስፍ ማለት ውስጤ ተነካ። ከሙያ አንፃር ያለው ይህን መሰል አስተዳደር ግጥሜ ነው። ሴቶች መሪነታቸውን እናታዊ ሁኔታቸውን መዋጥ አለበት።

ለረጅም ጊዜ ታግዬበት መና የቀረው ድካሜ ይህ ነው። የጨካኞች ማህበር በኢትዮጵያ ሰፈነ። ከውስጤ ነው እማዝነው።

የሆነ ሆኖ ይህን ሙያዊ መንሰፍሰፍ ብትን አፈር ላጡ የአማራ ልጆች ቢሆን ብዬ ተመኜሁኝ። አንድስ እንኳን ማግኜት አልቻልኩም።

የሆነ ሆኖ መሪነት በዚህ አርት ልቅና ልክ ይናፍቀኛል። ከሁሉም በጋራ፣ ከእያንዳንዳችን በግል።

ይህን አርት ወድጀዋለሁኝ። ይህን አያያዝ ናፍቄዋለሁኝ። በአማራ ደም ለምትታጠበው ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት እናት ቢሰጣት ብዬ ተመኜሁኝ። አማራዬ እስቲ ፀልይ። እባክህን የራስህን የቤት ሥራ ሥራ።

ሌላው በዚህ ዙሪያ ሺወችን እዬቀበርን በዚህ አጀንዳ አንጠመድ የሚሉም አሉን። እንደ እኔ ሙሉ ዘመኑን በጎምዛዛው ፖለቲካዊ ህይወት ላሳለፈ ትንፋሽ ማግኛ ነው ይህን መሰል ክስተት። ደክሞኛል።

ድካሙ ከሸፍጠኛውም ጋር ፊት ለፊት በመጋፈጥ ስለሆነ እጅግ ውስብስብ ነው። ትግሉ ከመርኽ ጣሹ ጋር ስለሚሆን ውስብስብ ነው። ፍልሚያው ከወረተኛ ታጋይ ጋር ስለሚሆን ትብትብ ነው። ግብግቡ አርቆ ስለ ትውልድ ከማሰብ አስቀድሞ ከማዬት ጋር ስለሆነ ሁልጊዜ መማገድ ነው። በዚህ ውስጥ በነፃ እዬተደከመ ምስጋና ቀርቶ በዙለገብ መሳደዱ ልክ የለውም።

ስለዚህ ይህን መሰል ክስተት ያስታግስልናል። ሰው ነን። ሃዘን ይሰብራል። ወደ ፍፃሜም ያጓጉዛል። ቢያንስ በማስተዛዘኛው ተሳትፎዋችን አትቅኑበት እያልኩ ነው።

ብዙው ዶር አብይ ወደ ሥልጣን ከመጡበት ጋር፣ ጥቂቱ በአማራ ተጋድሎ፣ በስሱ በዘመነ ቅንጅት የመጣ ሊሆን ይችላል።

ከዛ የቀደመ ጊዜ በነፃነት ጊዜ ለቆዬነው የህወሃትን እንቆቆ ዘመን ፊት ለፊት ወጥተን በጥዋቱ ለተጋፈጥነው ከባድ ነው። ሁልጊዜ ጥቁር ልብስ ስለወገን። ከቤተሰብ ምንም ሳይጎድልብን። በኑሯችንም።

ብቻ ይህ አንጀት የሚያላውስጥ የውስጥነት ሀዲድ ስቦኛል። መስጦኛል። እናም ለጋሷ ሥርጉትሻ አክብራዋለች።

እግዜአብሔር ይስጥልኝ።


 

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

19/07/2022

እንበርታ።

 

 

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።