የእብዬ ሆዴ እትብት እቴጌ ጎንደር፣
እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሰላም መጣችሁልን።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
«አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ።»
"ከማመስገን ጋር በፀሎት እዬፀናችሁ ትጉ"(ቆላስያስ ፬ ቁጥር ፪)
የእብዬ ሆዴ እትብት እቴጌ ጎንደር፣
ሁሉን ቻይ፣ ሁሉን አስተናጋጅ ማንጠግቦሽ ጎንደር፣ የአውንታዊ ልዕልት ሙሉእመቤት ጎንደር፣
የቤተ በሞቴ አውድዓመት ዘውዷ የእኛዋ ጎንደር፣
የብልሉኝ የአብርኃሙ እልፍኝ እቴጌ ጎንደር፣
የኑልኝ ንግሥት ውቢት ጎንደር፣
እናት ሆዱ ባለፀዳል ጎንደር፣
እርህርህት ለራህብ ደራሿ አራሿ ጎንደር፣
የአብሮነት ማርዳ ድሪ፣ ድኮት ጌጣአለም ጎንደር፣
የመቻቻል ሥህነ ህይወት ጎንደር
የበረከት ሙላት ጎንደር፣
ለችግር ፈጣኗ አጽናኞዋ ጎንደር
የሥር ዓተመንግሥ መቅድም ፍቅርተ ጎንደር
የዶግማ የቀኖና ቀመራዊት ጎንደር፣
የባህል አውራ ሁሉ ያለሽ ጎንደር፣
የታሪክ እጬጌ አንባሳደሯ ጎንደር፣
ለምለሚቱ ብሩህ ብርኃናማዋ ጎንደር
የአሳርም ቤተኛ ጎንደር፣
አመድ አፋሿ ልዕልት ጎንደር
የጥሞና ወላጅ እናት ጎንደር፣
የምህላ ብጡል ጎንደር፣
የትጋት ወተቷ ጎንደር፣
ቤተ ሊቀ ሊቃውንታት ጎንደር፣
የደግ ሰው ህብር ጎንደር፣
የእንግድነት ወግ እማታውቂ አላማጇ ጎንደር፣
የአርቆ ማሰብ ህሊና ጎንደር፣
የማስተዋል ጥሪት ጎንደር፣
የአርምሞ ዬጥበብ ሟተት ጎንደር፣
የድዋ ቀንዲል እናት ዓለም ጎንደር
ስለ ሁሉም ለሁሉም ዘወትር ትርታዋ ፀሎት እናት ሆዱ ጎንደር።
ኑሪልኝ ናፍቆቴ ……
ክበሪልኝ እትብቴ ……
ፀጋሽ ይድረኝ እመቤቴ ………
ሁኝል የመልካምነት አውደዓመት።
ጽኒልኝ በማተብሽ ……
ኩሪልኝ በትህትናሽ ……
አብቤልኝ በረድኤትሽ ……
ውስጤ የውስጤ ቀለቤቴ
የቃል ማሰሪያ የጽናቴ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
19/07/2022
ለጠሎት ትጉ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ