ለምን ይሆን ማህበረ አብይዝም እዬተበሳጩ ያሉት? ምን ተፈጠረ?
እንኳን ወደ ከበቡሽ ልሳነወርቅ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ።
· ለምን ይሆን ማህበረ አብይዝም እዬተበሳጩ ያሉት?
· ምን ተፈጠረ?
በሰው ልጅ የሚደርሰውን ነገር ሁሉ ማሰብ ይገባል። ከመራራው ጀምሮ።
መሰበር አለ። አካል መጉደል አለ። አዕምሮ መሳት አለ። ማበድ አለ። ዝንጉ መሆን አለ። ማበድ አለ። መሞት አለ። ሥልጣንን ማጣት አለ። ሰው ሰው ነውና። እኔ ለማንም ክፋ አልመኝም።
ማንም ሰው ዕድሜ ሰጥቶት ስህተቱን የሚያርምበት፣ የሚፀፀትበት፣ ንሰኃ የሚገባበት፣ የጥሞና ጊዜ ይስጠው ፈጣሪ ነው የምለው።
በሌላ በኩል በፖለቲካ ትግል ውስጥ መውደቅም፣ መነሳትም ይኖራል። መሞገትም ይኖራል። ግን ይሙት በቃ ለህሊናዬ አልመኘውም። ፈፅሞ።
በጣም ደንጋጣ ነኝ። አልቃሻ ነኝ። ቀድሞ ነገር እኮ ሰው እኔን ደፍሮ የቤተሰብ መርዶ አይነግረኝም።
ጭካኔ አብሮ አልተፈጠረም። የሚለመድ ነው። ሰውነት ሲክድ ጭካኔ ይወርሳል።
ጨካኞች ማስተዋል ይስጣቸው። አሜን።
አረማውያን የሚማሩበት ጊዜም ይስጣቸው። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
22/07/2022
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ