አንሰበርም አንሰበርም!

ንኳን ወደ ከበቡሽ ልሳነወርቅ ሚዲያ ላም መጡልኝ።

 

#ንሰበርም አንሰበርም!

"የቤትህ ቅናት በላኝ።"


 

ከቤቴ ከእኔ ጋር የዘለቁ ቅን መስካሪወች አሉ። ቀበርናት ስትሉ የሚንፎለፈለው አቅም በዚህ በሦስት ዓመት ፌስቡክ ላይ ተከሰተና ድንግርግራችሁ ወጣ። ስታሳዝኑ።

እንደ እኛ ዝልኝ ሁኑልኝ የገማ መንገድ ነው። እዛው ተጨፋፈቁበት።

ወይ ቀልድ። ማህበረ ኦነግን የትናንቱ ውሎዬ ምን አፈራገጣቸው? እኔ ኦኮ በሙሉ አቅሜ ሠርቼ አላውቅም። ምን እንደ ሠራችሁ እናንተም ታውቁታላችሁ፣ የላይኛውም ያውቃል። ገዳ ለእኔ ሥርዓት ሊያስተምረኝ? ለመሆኑ እንደ እኔ አክብሮ የሚሞግት አለን?

ከእኔ ፔጅ ላይ የታዳሚዬ ስድብ፣ግልምጫ፣ ውርጅብኝ ገጥሞት ያውቃልን? ምክንያት እኔ እምሠራው ለትውልድ ነው። ለትውልድ ስሰራ አክሰሱ ላላቸው ልጆችም ተጠንቅቄ ነው።

አንተ እና አንቺ እያሉ የሚዘልፋትን ሚዲያወች አላዳምጣቸውም። ከቤታቸውም አልገባም። ስድብ ዕውቀት ስላልሆነ፣ ዘለፋ ልቅና ስላልሆነ።

እነሱም ወደው አይመስለኝም ከልክ ያለፈው ጭካኔ ስለ አንገሸገሻቸው ይሆናል። ስለዚህ በዝምታ ሁኜ የራሴን የሚዲያ አክሰስ ግን በራሴ ልክ አክብሬ አስከብሬ እሰራለሁኝ።

ከእኔ ፔጅ አንተ ብዬ የሞገትኩት፣ አንቺ ብዬ የሞገትኩት የለም። እንኳንስ ባለስልጣናት የቤቴን ታዳሚወች እራሱ በጓዳ መጥተው አንቺ፣ አንተ በይን ካላሉኝ በስተቀር እርስወ ነው እምለው።

ለእኔ ሲል ስዩም ወሮ፣ ወት አይደለሁም ስላሉ በሥማቸው ጽፌያለሁኝ። ያውም ሲኤንኤን ኢትዮጵያን ተዳፈረ ብዬ ወግኜ። ለዛውም አሞኝ ሳለ ነበር የፃፍኩት። አገሬን አትንኩ ብዬ። ውክልናው የኢትዮጵያ አንደበት ነበር እና።

የተፈቀዱ ቃላት፣ ግን የማይመቹ ሲሆኑ እንኳን ቀይሩት ብዬ አሳስባለሁኝ። አሻም ካለ በፍቅር መራራ ስንብት ይሆናል። ፎቶ ላይ ኤክስ የተደረገበት ፔጄ ላይ አይገኝም።

አንድ ጊዜ በዶር አብይ አህመድ አሊ ፎቶ ላይ ፍዬል ሽንት እዬሸናችበት አገኜሁኝ። የማከብረው ወንድሜ ነበር። ተሰነባበትን።

ሌላ ጊዜ ወሮ አዳነች አበቤን "ቅሪንዲዳ" ብላ የፃፈችን እህቴን፣ ተይ ይህ አይፈቀድም። ለጥቁርነቱ ከሆነ ሁላችንም ነን። እረፊ አልኳት። እሷም እምቀርባት ነበረች። አሰናበትኳት።

ሌላው "ጋላ" የሚሉትም አንድ ማህበረሰብ በዚህ አትጥሩኝ ካለ ሊከበርለት ይገባል። ገላጩም በቀደመው መጠሪያ መጠቀሙ ባያስኮንነውም።

ሌላው ቀርቶ እኔ "ሴተኛ አዳሪ" የሚለውን፣ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚጠራውን አልጠቀምበትም። ፆታቸውን መተዳደሪያ ያደረጉ ብዬ በትርጉም አቃንቼ ነው እምጠቀመው።

ይህን ያነሳሁት በምክንያት ነው። ፌስቡክ ስጀምር መራገጫ ነበር። እረቂቅ ነው። አይጨበጥም፣ አይዳሰስም። እንጂ ብዙ ሰርቸበት አሁን ፔጁ በተለይ የእኛ ቤት ምንም የትርፍ ንግግር መደብር አይደለም።

ምክንያቱም ስድብ ድል ስላልሆነ። ስድብ መሸነፍ ነው ብዬ በአውዲዮም፣ በፁሁፍም ሠርቻለሁኝ።

ግን ለተገቢው የጭካኔ ተግባር አክብሮ የሚሞግት ቦንብ ቃል፣ ቦንብ ሥንኝ፣ ቦንቦ ሐረግ እጠቀማለሁኝ። ያራደው ግድፈቱን ማረም ነው። ጥሞና ወስዶ እራሱን መርመር ነው።

ሌላው አፍ ያለው ሁሉ ማይክ እንደሚይዘው አይደለም ፀጋዬ። ይህን ዓለም በተለያዬ ጊዜ መስክሮታል። ዩኒክ ነው። ተዝረክርኮም አይቀርብም። ዓይንህ ጥርስህ ተብሎ ታርሞ፣ ታርቆ፣ የድምፅ ምቱ ተውቦ ነው የሚቀርበው።

ስንት ሽርክትክት፣ ስንት ግርድፍድፍ የተሸከመ ኦነጋዊ የሚዲያ አታሞ በኢትዮጵያ ባጀት የሚያላግጥበትን ጥሰት ያስተካክለው። በዛ ውስጥ ያሉ አክብሬ እማዳምጣቸውን የሚዲያ ሰወችን አይመለከትም።

ሌላው የእኔ የፌስቡክ ጓደኛ፣ ፎሎወር ሆኖ ያልተፈቀደልን ፆታዊ ነገር ከለጠፈም ይሁን ቪዳዮ ላይ ካገኜሁኝ ሥሙን ይዥ አሰናብተዋለሁኝ። ንግግርም የለም። ምንጊዜም የዘለቀ መከፋት ከኖረኝ አልናገርም። በዝምታ ማሰናበት ነው።

አዬ እስኪ ይታይ ዩቱብ ቻናሉ ሁሉ? ለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድን በሙሉ ታይትላቸው የሚጠራው የትኛው ሚዲያ ነው? ህሊና ይኑር።

ሌላው በኢትዮጵያ አንጡራ ሃብት የሚዘባነው ሚዲያ ሁሉ

እስኪ በምልሰት ልጆቻችን ሲታገቱ የነበረውን ዝክትልትል ትቃኙት ዘንድ አንድ ምስል ላቅርብ።

ስንት አክሮባት በሰዓታት ሚዲያው የሚሠራውን ትቼ። ሲላጥ፣ ሲፈገፈግ፣ሲጋጋጥ፣ ሲገጣጠብ፣ ሲለባበጥ የሚውለውን ትቼ።

በሙሉው መረጃው ከእጄ አለ። ሞጋች ስለሆንኩኝ። ሁሉንም ቀድቼ፣ ዘግቤ እይዛለሁኝ።

ይህን የምጽፈው ትናንት የአንሰበርም ንቅናቄ በድምፅም፣ በፁሁፍም ሠርቼ ነበር። በጣም በትጋት። በጥራትም። በጠበጣቸው። እና ሲወራጩ አመሹ። በምንም ነገር እኔን መክሰስ አይቻልም። በምንም።

ተጠንቅቄ ነው እምሠራው። ጋዜጠኝነቱ ግማሽ እድሜዬን ወስዶታል። ትውልድ ከማይተካቸው አዛውንት አውራ ግንድ ጋዜጠኞች ጋርም ሠርቻለሁኝ። የእነሱ ልጅ ነኝ። ሥልጠናውም አልቀረብኝም። በመጋዝን ከሦስት ዓመት በላይ በተግባር ሰልጥኛለሁኝ እዚህ ሲዊዝ። በራዲዮ ጋዜጠኝነትም የሲዊዝ ሰርትፍኬት አለኝ።

6ቱም መፃህፍቶቼ 6 ጊዝ በሲዊዝ የኢንተግሬሽን ብሔራዊ የላይብራሪ ጉባኤ ላይ መግለጫ ተሰጥቶባቸው እዛው ላይ ተሽጠዋል። ብዙወቹ የአማርኛ ቋንቋ ዲፓርትመንት የከፈቱት በእኔ ነው። አሁን ሲደክመኝ ነው የቀረው።

8ኛው መፀሐፌ ታርሞ ተቀምጧል። በሚዲያ በቆዬሁባቸው ወቅቶች ግጥሞች፣ ትረካወች፣ መጣጥፎች ቢጠራቀሙ ዓመታቱን ሙሉ ህትም ይሆኑ ነበር።

የማይደንቀኝም ለዚህ ነው። ክብር በሚባለው ሁሉ ገና በጋሜ እና ቁንጮዬ ጀምሮ አልፌበታለሁኝ። ብርቄ አይደለም። ጎርፍ አምጥቶ ደለል የሠራብኝ አይደለሁም።

ምን እንዳለኝ፣ ምን እንደምችል፣ ምን እንደሚፈቀድልኝ ጠንቅቄ አውቃለሁኝ። ምን ደግሞ እንደማይፈቀድልኝም። ዓለም ዓቀፍ ጉባኤን ጨምሮ ብዙ በጣም ብዙ ቁምነገሮችን መኖሬ አገናኝቶኛል።

ለምን እወቀሳለሁኝ? ብቸኛዋ ሴት 15 ዓመት የራዲዮ ዝግጅት ያላት፣ ተጠማኝ ያልሆነች፣ ኪሳችሁን የማታስቸግር እኮ ናት ሥርጉተ።

ወቀሳ ለእኔ? ቢላ ቤት፣ ሙገሳ፣ ከንቱ ውዳሴ፣ ዶላር ጎርሼ ስላልሆነ፣ የዬትኛውም ድርጅት አባልም፣ አካልም ስላልሆንኩኝ፣ በራሴ ወጪ፣ በራሴ ጊዜ፣ በራሴ ዕድሜ ነው እያባከንኩ በነፃ እምሳተፈው።

ያልተመቸው ወደ ተመቸው መብት ነው። እኔን ግን ከአቋሜ ንቅንቅ የሚያደርገኝ የትኛውም የአናርኪዝም ጉዞ የለም። አይኖርምም።

"የሚሉሽን ብትሰሚ ……" ምን አለና ነው ልብ ሞልቶ የሚያናግር? ዝልግልግ። ሚሊዮን ፍቅር ተደፍቶ ቂም፣ በቀል፣ ጥላቻ በዬሰከንዱ እዬተመረተ።

እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

Winterthur Schweiz. 

22/07/2022

#አንሰበርም!

#አንሰበርም!

#አንሰበርም!

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።