#ነንነን #አንሰበርም! #አንበገርምም!
እንኳን ወደ ከበቡሽ ልሳነወርቅ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
አታስቡት አንሰበርም
አንበገርም!
ግብርነታችን ይታወቃል
ዬጽንሳችን ስለእናታችን ነው የቃል!
ግብራች የሆነ ስለልባም
ተግባራችን ህብራዊ አጓጊ ደማም!
ህብራዊነታችን ሳቢ ሊቀ - ትጉኃን
በመቻችል ውስጥ የፀደቀ ስኩን።
የምህረት ሰብላማ - ዓውድዓመት
የይቅርታ ቤተ ሐሴት።
የጽናት ሰናይ ተምሳሌት
የመሆን ፍስኃ ትሁት።
የፈተናችን መበራከቱ ጓሉ
የሚስጥርነታችን በላቂያነት ስለቃሉ።
የመኖር ጥበባችን ኪዳን የፍቅር ሰላሚዊት
የአብሮነት ክናድ ክስተታችን ትፍስህት።
ባለ ብዙ ተስጥዖ፣ ግን ~~~~~#የቀስታ
ያላጣን፣ ያልቸገረን ~~~~ ግን - በዝግታ።
የይሉኝታ ፍልስፍና ያለን
ያላጣን፣ ያልነሳን ከቀደምቶቹ ቤተኝነትን።
ዬዕጣ ውጪጭ የማያሰዬኜን
ለመኖር የፈቀድን በልካችን።
#የማንገፋው - $የማይገፋን
#የማይገፋ ማንነት ያለን።
አወን ነንነን
እርግጥም ኢትዮጵያዊ አማሮች ነን።
እስተወዲያኛው የማንሰበር ሁነኛ
ሰበርነው ፍጡረ ፈጣሪን የማንል፣ ያልሰከርን ደራሽ በረኛ።
ትምክህት - ያላበጀን
በአላህ የተፈጠርን።
በእግዚአብሄር የተመረቅን
እንድናከብር ክቡር ሰውን።
ነንነን! ነንነን!
ትናንትም ዛሬም
ነገም ከነገ ወዲያም ከዚያም በስቲያ
ኢትዮጵያዊ አማሮች ነን።
ለተፈጥሮ ተፈጥሯዊ ክብር ያለን
ስለሰው ልጅ የሚጨንቀን፣ የሚጠበን።
የማንሰበር
ሌላውን የማናውክ ግን ማገር።
22/07/2022
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
19.01
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ