ግሥ የሌለው መሪነት አልቦሽነት።
ግሥ የሌለው መሪነት አልቦሽነት። "ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ።" ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ #ማሰሪያ #አንቀጽ የላቸውም። የድርጊቱ መነሻም መዳረሻውም ከኦዲዬንሱ ውጪ ነው። አሁን አሁን ሳስበው መሪነት ጽንሰ ሃሳቡ የገባቸው አይመስለኝም። በሌላ በኩል #የመሪነት #ስሜቱንም የተረዱት አይመስለኝም። በተጨማሪነት የመሪነት #መነሻውን ያወቁትም አይመስለኝይ። ይህም ብቻ አይደለም #የመሪነት #ቅደም ተከተሉንም የተረዱት አይመስለኝም። እርግጥ እሳቸው ያቀዱትን እዬከወኑ መሆኑን አያለሁኝ። ያ ማለት ግን የአገር መሪነቱን ሚና እዬተወጡ ነው ማለት አይደለም። መሪነት ለእሳቸው 365 ቀን መናገር፤ ለሳቸው ደስ የሚላቸውን ፕሮጀክት የድሎት አቅዶ መፈፀም፤ አስደሳች እና አዝናኝ የሆኑ ጉዳዮችን ነጥሎ ትኩረት መስጠት መሪነት መስሏቸዋል። በፍፁም የመሪነትን #ስሜቱን አልተረዱትም። በፍፁም። መጓዝ፤ ንግግር ማድረግ፤ ድንገተኛ ክንውኖች ላይ አቅምን ማፍሰስ መሪነት መስሏቸዋል። የሠፈር መሪ አይደሉም። የዓለም የሰላም አባት የሚመራውን አገር ቀጠናውን በሰላም ማስተዳደር የተሳነው፤ እወክለዋለሁ በሚለው ኦሮምያ ክልል እንኳን ከህዝቡ ጋር የተቆራረጠ። ከበሻሻ በስተቀር በዬትኛውም ሁኔታ የወጡበት ማህበረሰብ ውክላዊ ፖለቲካዊ ሂደት አብሰንት የሆኑ። የሚገርመኝ እሳቸው ከተደሰቱ፤ እሳቸው ከደለቁ ከ110 ሚሊዮን ህዝብ በላይ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ስሜቱ ምን ይሁን ምን ጉዳያቸው አይደለም። እረፍት አልባ የሚታትሩት ለራሳቸው ፍስኃ ስለመሆኑ ነው እኔ እማስተውለው። ህዝቡ ሲከፋው አይከፋም። ሲያዝን አያዝኑም። ሲራብ አይራቡም። ሲያለቅስ አያለቅሱም። ለእኔ የቤተ መንግሥቱ #ሃውልት ወይንም ማስዋቢያ ዲኮሬሽን ሆነው ነው የሚታዩኝ። ኦሮሞ ጠቅላይ ሚር ሆነ።...