ልጥፎች

ከኤፕሪል, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የፖለቲካል ፓርቲን የመረጠ ሰብዕ #የእኔ የሚለው የፖለቲካ ዕይታ ሊኖረው አይችልም።

ምስል
  የፖለቲካል ፓርቲን የመረጠ ሰብዕ #የእኔ የሚለው የፖለቲካ ዕይታ ሊኖረው አይችልም ።       "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     #ምዕራፍ ፲፰።       ፎቶው የፖለቲካ ድርጅት ቋሚ ሠራተኛ ሳለሁ የነበረ የሥራ መታወቂያ ካርዴ ላይ ያለ፤ እንደ ልጄ የማዬው፤ አብሮኝም የተሰደደ፤ እጅግ እምሳሳለት የፓርቲዬ የኢሰፓ ቅርሴ ነው። ፓርቲዬን ኢሠፓ እወደዋለሁኝ። በህይወቴ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ፓርቲዬ ኢሠፓ ነው።   ከኢሠፓ ጋር እስከ መጨረሻው ታግያለሁኝ። እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ለፓርቲዬ ደንብ፤ ፕሮግራም #በድንግል ነው ያለሁት። ከፓርቲዬ ኢሠፓ መራራ ስንብት በኋላ አይደለም የፖለቲካ ድርጅት፤ ማህበር እንኳን በአባልነት ተመዝግቤ፤ ተሳታፊ ሆኜ፤ መዋጮ አዋጥቼ አላውቅም። ወደፊትም ፈጽሞ አይታሰብም። ይበቃል።    እንደ ዕድል ሆኖ እኔ አገር ለመምራት ሙሉ ልቅና፤ ሙሉዑ ልዕልና፤ ሙሉ ብቃት በነበራቸው ታላላቅ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሊቀ - ሊቃውንት ነበር የመለመሉኝ። #የሠሩኝ ልበል። እነ ጓድ ገብረመድህን በርጋ፤ እነ ጓድ ወንድወሰን ኃይሉ ወዘተ…   የማይናወጽ ጽናት፤ #የማይበረግግ ሰብዕና፤ እጥፍ ዘርጋ የማይል ዕይታ፤ ገባ ወጣ የማይል የፖለቲካ አቋም ብቻ ሳይሆን አጥርቶ የመስራት ሚስጢር፤ የፖለቲካ ፓርቲ ጽንሰ ሃሳብ፤ ዲስፕሊን ተልዕኮ በተለያዩ የኮርስ፤ የሰሚናር፤ የጉባኤ ዕድሎች እንድሳተፍ በማድረግ ብቻም ሳይሆን ህይወቱ እኖረው ዘንድ በቅርብ እየተከታተሉ አዕምሮዬን አነጹት።    የትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ቢመጣ - ቢሄድ፤ ሚሊዮኖች የእኛ ቢሉት፤ ስልጣን ቢይዝ ቢለቅ ከቶውንም #አይናፍቀኝም እስከ ህይወቴ ፍፃሜ። በዛ በተደራጄ፤ ምራቁን...

#በራስ መተማመን ልክ እንደ ጥርጥር #ሲሸበሸብ። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።

ምስል
  #በራስ መተማመን ልክ እንደ ጥርጥር #ሲሸበሸብ ።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።     #ምዕራፍ ፲፰።   በራስ መተማመን ሲከሽፍ የድንቢጥ ይሁን የቅምጫጭሪት፤ የቅምጫጭሪት ይሁን የጉንዳን፤ የውሃ እናት ይሁን የአውጭኝ፤ የአውጭኝ ይሁን የእንጉቻችሪት፤ የንጉቻችሪት ይሁን የጃርት፤ የጃርት ይሁን የእስስት ሥም መሆን የተሳነው ከቤታችን መጥቶ ይውተረተራል። ሰውን ለመተቸት ይሁን ለመሞገት መጀመሪያ ሰዋዊ የሆነ #ሥም ይደፈር። የእራሥ የሆነ ዓለማዊ ይሁን የክርስትና ሥም ይቅር ቢያንስ የውሻ ሥም፤ የጥጃ ሥም፤ የአንበሳ ሥም፤ የፈረስ ሥም፤ የበቅሎ ሥም እኮ አለ።   በዚህ አማራጭ መጠቀም የተሳነው ያረገረገ ነፍስ መጥቶ እዚህ ገለባውን ሊያራግፍ፤ ቀጨሬ መጨሬውን ሊደርብ ይሞካክራል። ደግሜ ልንገረው እኔ በሰው ላይ ግፍ የማያደርሱ ሰብዕናወች ሁሉ የህሊናዬ #ዘውዶች ናቸው።    አቶ ሙስጠፌ መሐመድን በሚመለከት የተለየ አክብሮት ነው ያለኝ።   1) ህወሃታዊ ተግባርን ይጠየፋሉ። 2) በክልላቸው በማንነቱ ተለይቶ በግፍ የሚፈናቀል፤ በዕብሪት የሚገደል፤ ሰርክ #መስቃ የሚሰማ ነዋሪ የለም። ስለሆነም ሰዋዊ የሆነ ተፈጥሯቸው ይመስጠኛል። በአደባባይ እመሰክርላቸዋለሁኝ።    ዕውቅናም ልሰጠውም እፈልጋለሁኝ። አይደለም በሌላ ክልል፤ በአማራ ክልል እኮ የአማራ ልጅ መኖር አልቻለም። መሥራት አልቻለም። መማር አልቻለም። ወጥቶ በሰላም መግባት አልቻለም፤ አይደለም "ክልሉ የአንተ ብቻ ነው" ተብሎ በተሰጠ ሌላ ክልል የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ፤ ቅኒት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት እንደ ሃይማኖት መከበር ቀርቶባቸው መኖር በተፈቀደላቸው።   ምስራቅ አርሲ እኮ በየዕለቱ የቅ...

ለአንድ የፖለቲካ ድርጅት የፍላጎት #ቅደም ተከተል ያስፈልገዋል። መሻቱ ከዘመኑ ግሎባል የፖለቲካ #ባህሬ ጋር በእጅጉ ሊጣጣም ያስፈልጋል።

ምስል
  ለአንድ የፖለቲካ ድርጅት የፍላጎት #ቅደም ተከተል ያስፈልገዋል። መሻቱ ከዘመኑ ግሎባል የፖለቲካ #ባህሬ ጋር በእጅጉ ሊጣጣም ያስፈልጋል።   "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"   #ምዕራፍ ፲፰።         ፍላጎት ገደብ የለውም። የግል ፍላጎት፤ የማህበራዊ ፍላጎት፤ የቡድን ፍላጎት፤ የቤተሰብ ፍላጎት ይኖራል። ተፈጥሯዊም ነው። የፖለቲካ ድርጅት የሰወች የዓላማ እና የግብ ውህድ #ተቋም ነው። ይህ ተቋም ብሄራዊ ብቻ ሳይሆን አህጉራዊ፤ ሉላዊ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት ሊኖርበት መቻሉን በፍላጎቶቹ ውስጥ ማካተት ይኖርበታል።   በሌላ በኩል ዘመን ሰጥ አሉታዊም ይሁን አወንታዊም ሁነት በአንድ የዘመን #ማዕቀፍ ውስጥ ይኖራል። የኢራኑን ጦርነት ማዬት እንችላለን። ኮቢድንም እንዲሁ ለናሙና ማቅረብ እንችላለን።   በተለይ እንደኛ ያለ በኢኮኖሚ ዕድገታቸው ኋላቀር ተርታ የምትገኝ አገር ብሄራዊ፤ አህጉራዊ እና ዓለም ዓቀፋዊ ሁነቶች፤ ዘመን ሰጥ አሉታዊ እና አወንታዊ ገጠመኞችን በቅጡ ማስተዳደር እንዲችል የፍላጎት ቅደም ተከተል #ተመጥኖ ሊኖረው ያስፈልጋል።   ይህ የሚያስፈልገው ለገዢው የፖለቲካ ፓርቲ ብቻ ሳይሆን የእውነት ለሆኑት ተፎካካሪ ይሁን ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችም ፍላጎትን መጥኖ በአቅም ልክ መሰናዳት ያስፈልጋል። ለዚህም የፍላጎት ቅደም ተከተልም አውጥቶ በዛ ልክ ለመራመድ አቅዶ መነሳት የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ዝንቅንቅ ያለ፤ ያልጠራ ሁነት ነው እየተመለከትኩ ያለሁት።   የቱ ይቅደም? ከምን ላይ ይጀመር? ከቀላሉ ነው የሚጀመረው። ከከባዱ ላይ ከመነሳት በፊት። ስኬት ዕድል ቀንቶ መዳረሻው ቢያምርም እንኳን በሳል እና አስተዋይ ብቁ #ማህንዲስ ያስፈልገዋል። አቅጣጫ ...

የህወሃት #የቀውስ ተስፋ የመከነበት #ሐዋርያ የሱማሌ ክልል።

ምስል
  የህወሃት #የቀውስ ተስፋ የመከነበት #ሐዋርያ የሱማሌ ክልል።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።       #ምዕራፍ ፲፰።   በአቶ አብዲ ዒሌ ዘመን እንደ ጋንቤላ ክልል፤ የህወሃት ሙሉ መፈንጫ የነበረው የሱማሌ ክልል አቶ ሙስጠፌ መሐመድ የክልሉ መስተዳድር ፕሬዚዳንት ከሆኑበት ወቅት ጀምሮ የህወሃት የተደራጄ የቀውስ በቀል፤ የህወሃት ህልም አይሆኑ ሆኖ ከመከነበት ክልል ሐዋርያው የሆነው የሱማሌ ክልል ሲሆን። ሁለተኛው #ሲዳማ እራሱን ችሎ ክልል ከሆነበት ጊዜ ጀምሮም የህወሃት ተስፋ ወደ መቃብር ተልኳል።   አብሶ የሱማሌ ክልል የአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ቅድስት ተዋህዶም አሳሯን ያዬበት ጊዜ ነበረ። ገና በሽግግሩ ወቅት መቀጣጫ የሆነችው ቅኒት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ነበረች የነደደችው፤ የከሰለችውም። ከህወሃት መንበር ለቀቃ በፊትም ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪወች ሰፊ የሆነ #የፖለቲካ መፈናቀል ደርሶባቸዋል።    በአሁኑ ጊዜ የሱማሌ ክልል መሪ አካላት በወጣት ሊቃናት የተመራ በመሆኑ፤ የክልሉ ቲም ወርክም #ጤነኛ ነው። ህወሃት የአማራ ክልልን፤ ቤንሻንጉል ጉምዝን፤ ሌሎች ቦታወች ላይ የቀውስ መፈተኛ ማሳ የማድረግ አቅሟ በአይበገሬው የሱማሌ ክልል ብቁ፤ ንቁ ትንታግ አመራር መክሸፍ ችሏል።   ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ 100% የተሳካላቸው ምደባ ይህ ነው። ይህን በጥዋቱም ጽፌበታለሁኝ። ታላቅ ስኬት ነው። የሱማሌ ክልል ከጎረቤት አገራት ጋርም ደንበረኛ በመሆኑ ብዙ አውሎችን፤ የወጀብ ቡፌወችን የተቋቋመ ጠንካራ ክልል ነው።   የህወሃት የታቀደ ቀውስ ድል በድል የሆነው #አማራ ክልል ላይ ነው። እርግጥ ነው የጠገዴ...