#በራስ መተማመን ልክ እንደ ጥርጥር #ሲሸበሸብ። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።

#ምዕራፍ ፲፰።
በራስ መተማመን ሲከሽፍ የድንቢጥ ይሁን የቅምጫጭሪት፤ የቅምጫጭሪት ይሁን የጉንዳን፤ የውሃ እናት ይሁን የአውጭኝ፤ የአውጭኝ ይሁን የእንጉቻችሪት፤ የንጉቻችሪት ይሁን የጃርት፤ የጃርት ይሁን የእስስት ሥም መሆን የተሳነው ከቤታችን መጥቶ ይውተረተራል።
ሰውን ለመተቸት ይሁን ለመሞገት መጀመሪያ ሰዋዊ የሆነ #ሥም ይደፈር። የእራሥ የሆነ ዓለማዊ ይሁን የክርስትና ሥም ይቅር ቢያንስ የውሻ ሥም፤ የጥጃ ሥም፤ የአንበሳ ሥም፤ የፈረስ ሥም፤ የበቅሎ ሥም እኮ አለ።
በዚህ አማራጭ መጠቀም የተሳነው ያረገረገ ነፍስ መጥቶ እዚህ ገለባውን ሊያራግፍ፤ ቀጨሬ መጨሬውን ሊደርብ ይሞካክራል። ደግሜ ልንገረው እኔ በሰው ላይ ግፍ የማያደርሱ ሰብዕናወች ሁሉ የህሊናዬ #ዘውዶች ናቸው።
አቶ ሙስጠፌ መሐመድን በሚመለከት የተለየ አክብሮት ነው ያለኝ።
1) ህወሃታዊ ተግባርን ይጠየፋሉ።
2) በክልላቸው በማንነቱ ተለይቶ በግፍ የሚፈናቀል፤ በዕብሪት የሚገደል፤ ሰርክ #መስቃ የሚሰማ ነዋሪ የለም። ስለሆነም ሰዋዊ የሆነ ተፈጥሯቸው ይመስጠኛል። በአደባባይ እመሰክርላቸዋለሁኝ።
ዕውቅናም ልሰጠውም እፈልጋለሁኝ። አይደለም በሌላ ክልል፤ በአማራ ክልል እኮ የአማራ ልጅ መኖር አልቻለም። መሥራት አልቻለም። መማር አልቻለም። ወጥቶ በሰላም መግባት አልቻለም፤ አይደለም "ክልሉ የአንተ ብቻ ነው" ተብሎ በተሰጠ ሌላ ክልል የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ፤ ቅኒት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት እንደ ሃይማኖት መከበር ቀርቶባቸው መኖር በተፈቀደላቸው።
ምስራቅ አርሲ እኮ በየዕለቱ የቅድስት ተዋህዶ አማንያን በጅምላም፤ በተናጠልም ሰማዕትነታቸው የሰርክ ሆኗል። ምስራቅ አርሲን እኔ ሰርቸበታለሁኝ። ደግ ህዝብ ነው። ጭካኔው #ፖለቲካዊ ነው።
ይህ እንዳይሆን የታገሉ፤ ያሳኩ የመስተዳድር መሪወች ሊመሰገኑ ይገባል። አስፈላጊ ሲሆን ምስክርነት ሲያስፈልግም እመሰክራለሁኝ። ሌላው የሚገርመኝ ህሊናዬ የእኔ ክፋ - ደጉን፤ ዕውነት - ሃሰቱን፤ ጭካኔ - እርህርህናውን አንዘርዝሬ እንድለይበት ነው።
ህሊናዬን አላከራየሁትም። የጅምላ ጭብጨባ፤ ውዳሴ ከንቱ ናፍቆኝ አያውቅም። በጋሜዬ አንቱታውን፤ ክብሩን ሞገሱን ሥልጣኑንም ኑሬበታለሁ። ያላዬሁት፤ ያላጣጣምኩት የኑሮ መስመር የለም። አልነበረምም።
ስለዚህም የውዳሴ ቦንዳ ናፋቂ አይደለሁም። ስለዚህም #እንቅጭ እንቅጩ ይነገራል። ይፃፋል። ይሞገታል። መመስገን የሚገባውም ይመሰገናል።
በማናቸውም ጊዜ፤ በማናቸውም ሁኔታ፤ የየትኛውም ግለሰብ፤ የየትኛውም አካል ይሁን ተቋም #ፈቃድ አያስፈልገኝም። አስፈልጎኝም አያውቁም። ቅምጫጭሪት ካልተሆነ በዕውነተኛ የታወቀ ሥም ይሁን የብዕር ሥም #ኑ እና ሞግቱኝ። #አቅሙ ከተገኜ።
ከልጅነት እስከ ዕውቀት ከማምንበት፤ ከማራምደው ሃሳብ ፈቅ የሚያደርገኝ ቢኖር ፈጣሪዬ ብቻ ነው። የራሴ አለቃ እኔው ነኝ። ይህ ፔጅ የፋንታዚ ዳንኪራ የሚመታበት የድልቂያ ወይንም የኳኳቴ ቤት አይደለም።
ቤቱ የራሱ አዛዥ እራሱ ነው። ቤቱ የራሱ እንደ ራሴ እራሱ ነው። ቤቱ የራሱ አለቃ እራሱ ነው። አዛዥ ናዛዥ አይፈቀድለትም። ቁሮ ወይንም ለጠፍ ሃሳብ አያስተናግድም።
ቤቱ የእራሱ ቋሚ አሻራ በልኩ ለልኩ ያለው ነው። ድልቄያ፤ ሆታ ካስፈለገ ወደ የሚገኙበት መሄድ ነው ከልካይ የለም። እዚህ ፔጅ የማያረገርግ፤ የሰከነ፤ በልምድ የፋፋ፤ በተመክሮ የለማ ሃሳብ በራስ መንገድ እና ዕምነት ይለፍ ይሰጠዋል።
ይህ ቤት የትኛውም የፖለቲካ ድርጅት #የማይመራው እራሱን ችሎ የቆመ ዕልፍኝ ነው። ዕልፍኙ የእኔ የሚለው ቋሚ አሻራ ያለው ፔጅ ነው። ስለሆነም አውሎ በተነሳ ጊዜ ሁሉ መበርገግ አይታሰብም። ፈጽሞ።
ቤቱ ዕድሜ ለዓጤ ፌስቡክ እንጂ በፈራኃ እግዚአብሄር፤ በአደኩበት የይሉኝታ ማርዳ፤ በሲዊዝ፤ በዓለም ሥራ ላይ ባለው የህወሃትም ቢሆን የአገሬም ህገ - መንግሥት #ባላምንበትም፤ በሃይማኖቴ ዶግማ ቀኖና አደብ በገዛ ማስተዋል ይመራል።
እንደ ቦይ ውሃ ያሻው በአሻው ወቅት ሊዘውረው ፈጽሞ አይችልም። አይቻልምም። ሥርጉትሻን ለደቂቃ ከመዳፌ አስገባኋት ብሎ ሊፎክር የሚችል አንድ ነፍስ የለም። ሊኖርም አይችልም። መግቢያ ቀዳዳም የለም።
ክውን፤ ክርክም፤ ቁጥብ፤ ምራቁን የዋጠ ሃሳብ ስክን ብሎ፤ በስሎ ተፈጥሯዊ ቃናው #በጎንደርኛ ለዛ እና ወግ ተከሽኖ ሃሳብ ይቀርብበታል። ሊመሰገን የሚገባው ይመሰገናል። ሊወቀስ የሚገባው ይሞገታል፤ ግን ተከብሮ።
ህሊና ሲከራይ የአንጨት ይሁን የአፍር ሥም ይዞ እኔን ለመሞገት ማሰቡ እራሱ ይገርማል። መጀመሪያ ፍርሃቱ፤ መራዱ፤ በራስ መተማመኑ በተፈጠረበት ልክ ይስተካከል። ከዛ ከስድብ፤ ከዘለፋ፤ ከእላፊ ንግግር በስተቀር አቅሙ ከኖረ እኔን መሞገት ይፈቀዳል።
በውነቴ ብነግራችሁ #ፈሪ ሰብዕና ግጥሜ አይደለም። በተለይ በራስ የመተማመን አቅሙ #የተሸበሸበ ሥሙን ለመግለጽ የሚርበተበት ለተፈጥሯዊ ግንኙነት ዕድ ነው። ለትውልድም ኪሳራ።
ያ የዛለ፤ በራሱ መቆም የተሳነው ላንቁሷዊ ሰብዕና እራሱን #ሰርዞ የለሁም ብሎ፤ እድሜ ልኩን ሲሽሎኮለክ፤ አዩኝ አላዩኝ ብሎ ሲደክክ ዕድሜው ያልፋል። መሃከነ።
ማህበረ ቅንነት እንዴት አረፈዳችሁ? እንደምንስ ዋላችሁ። ኑሩልኝ።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
31/03/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ዕውነት ወጌሻም ይሁን ጋራጅ አስፈልጎት አያውቅም።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ