ልጥፎች

የቃሉ ጌታ አሜኑ እንዲህ ነው!

ምስል
እልልታው በስልክ ናፈቀኝ! ከሥርጉተ ሥላሴ 09.07.2018 (ከጭምቷ ሲዊዚና።) „እንሆ ይህን ሁሉ ዓይኔ አዬች፤" ጆሮዬም ሰምታ አስተዋለች።“ (መዝሙር ምእራፍ ፲፫ ቁጥር ፩) ·         አ ዲስ ዜና ለቅኖች … ይሄውና የእኛ የአሮን በትር በዬሄደበት ሁሉ ለምለም ነው። በዚህች ቅጽፈት የሰልክ አገልግሎት የኤርትራ እና የኢትዮጵያ መጀመሩን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አበሠረ። ቃል ብቻውን ምንም አይሠራም ሲሉ የነበሩት ሁሉ እንጥሽት ውሃቸው ፍስስ ይላል አሁን። ኢትዮጵያ ውስጥ ከብርሃን የቀደሙ ተግባራት በታምራዊ ምትሃት በሚመሰል አኳሆን እዬተከወነ ነው። ተመስገን የዚህ ዘመን ታዳሚ ፈጣሪዬ ስላደረከኝ። አሹልከህም ሪሞርኬው ስላለደረከኝ።  ውዶቼ ቅኖቹ ... እንዴት በሞባይል እና በቤት ስልክ እንደሚገባ ደግሞ ምርኩዙን ተከትሎ የበለጠ ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል … ·       ም ርኩዝ።   https://www.youtube.com/watch?v=1kXNrttrCSA Ethiopia: [ ሰበር ዜና ] ከኢትዮጵያ ኤርትራ በቀጥታ ስልክ መደወል ተፈቀደ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ዓራት ዓይማናው መንገዳችን ነው! ቅኖቹ የኔውቹ ኑሩልኝ። ማለፊያ ጊዜ። 

ሽኝት በቅኔ እትብታዊነት ነባቢታዊነት!

ምስል
የእናት እና የልጅ መለያዬትን ያህል የነበረው ተመስጧዊ ሽኝት በጥሞና! ሃሌ ሉያ። "ነፍሴ ሆይ እግዚአብሄርን አመስግኚ።" (መዝሙር ምዕራፍ ፩፵፭ ቊጥር ፩) ከሥርጉተ ሥላሴ 09.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) ·        መነ ሻ። https://www.youtube.com/watch?v=8sbjgAy5t1s&feature=share „Ethiopia: የጠ / ሚ አብይ የደመቀ የሽኝት ፕሮግራም ከአስመራ“ ድመቀቱ አይደለም እኔን የመሰጠኝ፤ መለዬት እንዲህ መፈራቱ። ሽብርቅ ለሆኑ ዲኳዊ ጉዳዮች እንብዛም ነኝ። አብሶ ይህ የሚሊዮኖች የነፍስ ጉዳይ ነው። ስለዚህ ጥሞናም፤ ተመሰጦም ያስፈልገዋል። እንዲያውም አቅም ያላቸው ይህን ስመጥር ቅኒያዊ ትልም በጸሎት ቢደግፉት ጥሩ ነው። እንዲያውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና የኤርትራው የወል የ7 ቀን የሱባኤ ሁኔታ ቢኖራቸው፤ እስልምናም፤ ካቶሊክም፤ ፕሮቴስታንም በወል ይህን የሰላም ጥረት በጸሎት፤ በሰጊድ፤ በሱባኤ፤ በድዋ አጥር ቅጥር ቢሆኑለት ምኞቴ ነው። ቢያንስ በግል ሁላችንም ማድረግ እንችላልን። የባከነው የትውልድ ዘመን ማክተም አለበት። ይበቃናል። ለእኔ የመንፈሴ ጉዳይ መለያየቱ እንዲህ ጭንቅ መሆኑ ነው። እያንዳንዷ ሰከንድ የፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ መንፈስ ዕዝነ ህሊናቸው ከኢትዮጵያ አዬር መንገድ ላይ ተተክሎ ነበር በተመስጦ እና በጥሞና። ያ ነው እኔን መንፈሴን ሁለመናዬን የገዛው። ቅንነት ነጥሮ የወጣበት፤ ንጽህና እና አሳቢነት ፈልቆ የታዬበት ድንቅ ገጠመኝ። ያዝልቀው እንጂ አያያዙ የእናት እና የልጅ ያህል የጠራ የፍቅር ጥሪኝ አለበት። ተመስገን! ·    ...

መቼነው ወደ እኛ የምትመጪው እትጌ ትግራይ?

ምስል
ይብላኝልሽ ትግራይ። „አቤቱ በአንተ ታመኛለሁና ጠብቀኝ።“ (መዝመሩ ዳዊት ምዕራፍ ፲፭ ቁጥር ፩ ) ከሥርጉተ  ©  ሥላሴ  09.07.2018 (ከጭምቷ ሲወዘርላንድ) ·         መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=6yww4Az7IdY&t=0s&list=LLNUkM6s0cFeCBEsZNkZIp0g&index=4 Must Watch !!! Amazing Story on JTV Min Addis ·         ጠ ብታ አሁን እርሰ ጉዳይ ትግራይ ስትሆን የሚከፋችሁ ልትኖሩ ትችላላችሁ፤ ግን የግድ ነው። እኔም ፈልጌው፤ ወድጄው አይደለም። ለነገሩ እነሱም  በአንድም በሌላም የትግራይ ህዝብ ማለት የኛ ድርጅት ማለት ነው ይላሉ። አመክንዮውም የወያኔ ሃርነት ትግራይ መሠረቱም የትግራይ ልጆች ነው። ያገዟቸው፤ ያበረታቶቸው እርሱ ህዝቡ ነው። ስንቅና ትጥቅ የሆናቸው እነሱው ናቸው። ሌሎች ተፎካካሪ ነን ባዮችም በትግራይ ሥም የተደራጁትም ያው የትግራይ ልጆች ናቸው።  ስለዚህ ከዚህ ዕውነት ውጪ ሊሆን አይቻልም። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ብለህ ከትግራይ ውጪ ሰማይ ላይ የተነሳፈፈ መንፈስ ነው ማለት አይቻልም። እኔ እንዲያውም አጋጣሚው ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ጀምሮ ትግራይን የመርሳት ሁኔታ ይፈጠራል ስል ጭራሽ የተባባሩት ድምጽ ሆነው ነው ያረፉት ተፎካካሪ ነን የሚሉትም መደመሩ ከጭካኔ እና ከአረመኔያዊነት ጋር ሆኗል። ያም መብት ስለሆነ ምንም ባልልም ትግራይን አታንሱ ስለሚለው ግን መነሻውም መድረሻውም መናህሪያውም ይሄው መሬት ስለሆነ ...

አጋጣሚሰጥ ስሜት ምንድን ነው?

ምስል
አጋጣሚሰጥ ስሜት። „ከቸር ሰው ጋር ቸር ሁነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤ ከንጹህ ጋር ንጹህ ሆነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማ ጋር ጠማማ ሁነህ ትገኛለህ።“ (መዝሙር  ምዕራፍ ፲፯ ከቁጥር ፳፭ እስከ ቁጥር ፳፮) ከሥርጉተ © ሥላሴ 09.07.2018  (ከገዳማዋቷ ሲዊዝሻ።) ስሜት የሰውነት ቋንቋ ነው። ስሜት የመንፈስ መርከብ ነው። ስሜት የነፍስ ተልዕኮ ነው። ስሜት ረቂቅ ነው። ስሜትን የሚተረጉሙ ሁነቶች የመኖራቸውን ያህል የስሜትን ትክክለኛ ገጸ ባህሪ ሊገልጹ የማይችሉ ሁነቶችም ይገጥማሉ። ሥም የለሽ ስሜቶች እንደ ማለት። ይህን እኔ ያወቅኩት የኤርትራ ልዑክ አዲስ አባባ ሲገባ የተሰማኝን አዎንታዊ ስሜት መልኩ፤ ቁመናው፤ ይዘቱ፤ አፈጣጠሩ፤ ሂደቱ፤ አቅጣጫው በፍጹም ሁኔታ ስሜቴን ማወቅ ከቻልኩበት ዘመን ጀምሮ አዲስ እና የተለዬ ነበር። ለዚህን ያህል ዘመን ይህን መሰል ሥም የለሽ ስሜት እንዳለኝ አለማወቄ ብቻ ሳይሆን ሌላም አጋጣሚ ቢፈጠር እንዲሁ በተቀማጭንት ያሉ ሌሎች የስሜት ዓይነቶችም ሊኖሩ እንደሚችሉ አሁን አዲስ ምናባዊ መስመር ያበጀሁላቸው ይመስለኛል። የታወቁ ስሜቶች በስዕል፤ በምልክት፤ በጹሁፍ፤ በትይንት፤ በምልክት፤ በደወል፤ በንግግር ሲገለጡ ኖረዋል። እኔ ወደዛ መግባት ብዙም አልፈልግም።  ለእኔ ሳብ ያደረገኝ ይህ የማላውቀው ስሜትን የመግለጫ ቋንቋ ማጣቴ ብቻ ሳይሆን ተደብቆ የመቆዬቱ ሚስጢርም ነው። ሚሰጢሩን ፍልፍዬ ማግኘትን በቀጣይነት እሻለሁኝ። የኤርትራን ሰው በማዬቴ እንዳልል ሲዊዝ ራስ እግሩ ኤርትራዊ ነው። በዛ ላይ ከኢትዮጵያዊው ሰው የሚለይበት ምንም ነገር የለም። የልሳናችን የድምጽ አወጣጥ ቅላፄያችን ብቻ ነው ልዩነት ለሚለው ተቀራራቢ ነገ...

ራያዊት ትርሲት!

ምስል
ዓይነት የወጣላት ዓመት!   „አቤቱ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል?    በተቀደሰውም ተራራ ማን ይኖራል? „በቅንነት የሚሄድ፣ ጽድቅንም የሚያደርግ፣“ በልቡም ዕውነትን የሚናገር። (መዝሙር ምዕራፍ ፲፬ ከቁጥር ፩ እስከ ፪) ከሥርጉተ©ሥላሴ( ከድንቋ ሲዊዝዬ)                ማሾውም በጣዝማ ማር ጮሪት በፍቅር               የቅኔ ማህሌት የጥዋት ጠሐይ በር።               ፏፏቴው ወርቦ ጸጥ ብሎ ታዳሚው               እልልታ በዓይነት በውስጠት ገረመው።               እሩቁ ህልማችን ፍጥነትን ተክህኖ               ናፍቆትን ቀደስ ተግቶ በተደሞ።               ህሊናው በማሳው ጸደይን አፍርቶ               የጥንት የጥዋቱ ትውፊቱ ጎምርቶ።               ወይ ሞገስ አስገዶም አንተ ሁነኛችን፤               ወይ አብረሃም ደቦጭ አንተ ጠበቃችን፤               ነፍስ ረክታ ዋ...

የቅኔ ማህበርተኝነት እልልታ!

ምስል
አሥመራ አና ሎሬቱ! ከሥርጉተ  © ሥላሴ  08.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዝሻ።) „ጥቂት መከራ ተቀብለው በብዙ ክብር ይዘጋጃሉ።“ (መጽሐፈ ጥብብ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፭) መነሻ፤ https://www.youtube.com/watch?v=2mmNokvPc5U&t=24s Ethiopia:  የዶ / ር   አብይ   ታሪካዊ   ንግግር   በኤርትራ   ምድር  !! ( ፕሬዝደንት   ኢሳያስን   ሳቅ   በሳቅ   ያደረገው   ንግግር ) ዛሬ ኤርትራ አሥመራ ላይ የሆነውን ሁሉ እልልታ ሳይ ታቦቴ የቅኔው ልዑል ብላቴ ጌታ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን ስንኞቹ እንደምን የውስጥ አና የቀደሙ ነበሩ?የሚለውን በምለሰት ቃኘሁት።    ባለቅኔው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በትግረኛ የተናገሩት ስለ አስመራ ከተማ የዓለም ቅርስነት፤ ንጽህና፤ ታሪካዊነት ላይ ሰፊ አትኩሮተ ዕድምታ ነበረው። የቅኔ ማህበርተኝነታቸውንም እስኪ ከታቦቴ ሥንኝ ጋር ቃኙት ቅኖቹ። ያው እኔ እምጽፈው ለቅኖች ብቻ ነው። ጎድጓዶች አይጥማቸዋም ቅኝቱ ...  አሥመራ። ምነው ሁሉ እንዳንቺ አሥመራ እንደ ከተሞች መዲና አቀያዬሱ ቢጠራ ፤ የአውራ ጎዳናሽ ጠለላ፤ ሁሉን በአክናፍ እዬጠራ አሥር ሰዓት ላይ ሲደራ ለመንገደኛሽ መዝናኛ ሲያጠላ ሲያብብ ሲያፈራ፤ ምነው ሁሉ እንደ አንቺ አሥመራ አደባባይ ሲያነጥፉ አድባራት መስኪዱን ካቴድራሉን በዬረድፉ ገብያውን በየመልኩ እንዳውታር እያሰለፉ በወግ አዬደረደሩ በሥምረት እያሰመሩ በውበት እያደባሩ እያሳመሩ ቢያደሩ፤ በዬክፍሉ በዬበሩ፣ በዬ...

ኮራ ኮራ ብላ ለቀጣዩ ራሺያ ደግሞ በቀዩ የበይ ተመልካች...

ምስል
ኮራዝያን ኮራ ያለ ቡድን ነው ለካንስ ዋው! ለዋንጫም እድሉ ሰፊ ነው። „በጎ ነገር ከጥንት ጀምሮ ለበጎ ሰዎች ተፈጠረች  እንደዚሁ ክፉ ነገርም ለኃጢያተኞች ተፈጠረች።“ (ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፳፭) ከሥርጉተ ሥላሴ 08.07.2018  (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) ዜና ስፖርት ። ትናንት እንደግዳ ስለነበረብኝ ቁጭ ብሎ የማደር ያህል ነበር። እናም በዛለ ሰውነቴ ነበር ዛሬ የፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂን ሳቅ ትንሽ ረፋድ ላይ የጫርኩት እና የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክትም የላኩት። ከዛ በኋዋላ የተለመደው ተግባር ተከውኖ በቂ እረፍት ወሰድኩኝ። የትናንቱ ምሽት ዕንቅልፍ በፍቅር ተወራረደ። ከዛም ትናንት ከእንግዳዬ ጋር በጨረፍታ ብቻ የተመለከትኩት ያለዬሁት የራሺያ እና የኮራዚን የቅዳሜ ምሽት የኳስ ጉግስ በጥሞና ተመለከትኩኝ። የፊፋ የ2018 የእግር ኳስ ማራኪ ጨዋታ የመጀመሪያው የራሺያ እና የግብጽ ነበር። የፋይናል የሚመስል ፉክክር ነበር የተከወነው። ዘንድሮ ዕድሜ ለአብይ መንፈስ እንጂ ሙሉውን ስላልተከታተልኩኝ ኮራ ይህን ያህል ጥንካሬ እንደአላቸው ስላላዬኋዋችው አለውቅኩም ነበር። እርግጥ ነው በ2016 አውሮፓ የፊፋ ዋንጫ ውድድር ላይ ሲወድቁ ቅር ብሎኝ ነበር። ዛሬ ሳያቸው ግን ካለፈውም የሚገርም ብቃት አይቻለሁኝ። ቀጣዩ ተጋጣሚያቸው እንግሊዝ ነው። ያለምንም ጥያቄ ይረቱታል። ዋንጫውን ለመወስደም ቀጣይ ብቁ አቅም አላቸው። ለዋንጫ ወይ ከፈረንሳይ ወይ ከቤሌጄም ጋር ይገጥማሉ። የትናንቱ ጨዋታ እጅግ ማራኪ ነበር በጣም ማራኪ። ኪኖ ነበር።  የአስልጣኛቸው እርጋታ እና ስክነት ትውልድ ይገነባል። የኮከቦች ኮከብ ተጨዋቻቸው 10 ቁጥሩ ነው። ኮከብነቱ እኔ በ አውሮፓ ሊግ ሁልጊዜ...