ልጥፎች

ህግ አምላክ! እባከወት ይሁኑ በልከወት። "#ብሉ እዬተባለ ነው ያለና?" ከኡራኖስ የባጁት ቀዳማይ እመቤት ……

ምስል
በህግ አምላክ! እባከወት ይሁኑ በልከወት። " #ብሉ እዬተባለ ነው ያለና?" ከኡራኖስ የባጁት ቀዳማይ እመቤት …… ምን ብሉ?? ባሩድ? ጭንቅ? ጭፍለቃ? መፍረስ። መናድ? እራስን ማጣት። ብልኃት ዬሌለው ቅላት ትል ነበር እሚታዬ ጽግሽ። በተጓዙ ቁጥር ጎንደር አዲስ ከንቲባ ይጠብቀወታል። አሁን 6/7 ኛው ከንቲባ ይሆናሉ። ለምን ብለው አጤወትን ጠይቀው አያውቁንም? ከ2015 ዓም ጥምቀት ማግስት ደግሞ አዲስ ከንቲባ ተመድበዋል ከብልጽግና ወንጌል። ወይ ጠቅልለው አባጠቅላዩ በሪሙት ኮንትሮል ከንቲባ ቢሆኑ ይሻላል። ሰርክ ከንቲባ ምርጫ??????? "ህግ ተላላፊወችን ጠላሁ" እንሆ ………   ቤተ - ዬሻሸመኔ ዬእግዚአብሔር ዓውደ ምህረት በደም በጨቀዬ ፴ቀን ሳይሞላው ዬድፍረት ኃጢያት አዳመጥኩኝ። "አቤቱ የድፍረት ኃጢያትን እንዳልሠራ ባሪያህን ጠብቅ።" አሜን ንግግር አያስፈልግምፖ። #ሪባን መቁረጡ በቂ ነው። ቤተ - መቅደስ ተከርችሞ በዕለተ ሰንበት በመዲናዋ ሥርዓተ - ቅዳሴ፤ ሥርዓተ - ፍትኃት፤ ሥርዓተ - ተክሊል፤ ሥርዓተ - ቁርባን፤ ሥርዓተ - ማህሌት በጦር ኃይል ታግቶ መስቀል እዬተረሸነ፤ ለመሆኑ አዲስ አበባ ዬማን ናት አሁን? በትውስት እንደሚኖሩባትስ ያውቁ ይሆን??? ፦፦፦፦ ነገ በኤሌትሪክ እጥረት፤ በውሃ አቅርቦት፤ በቀረጥ ጫና ለሚዘጋ ዕለታዊ ነገር ያለልክ እና ያለ ደረጃ በልቁ እና ዝልግልጉ የኦነግወኦህዴድ የቀውስ ፖለቲካ ተማምኖ ካለ ችሎታም፤ ካለ ክህሎትም እንዲህ ዘው ብሎ #ከመበለሻሸት #ዝምታ በስንት ጣዕሙ። ሲሆን ሲሆን መናገር ዬማይችል ሰው አፅፎ ማንበብ። በስተቀር ከመቀስ ጋር ተዋውሎ በዝምታ እንደ ተከደኑ ይሻል ነበር። ትምህርት ቤት ዳቦ ቤት እዬሠሩ ማስመረቅ ይበቃወታል። እላፊ እባከወትን አይሂ...

#መመረቅ። ከሃመር ተዋህዶ ዬተገኜ ነው እማሆይ ዜና ማርያም

ምስል
#መመረቅ ። ከሃመር ተዋህዶ ዬተገኜ ነው እማሆይ ዜና ማርያም    ============= በመንፈሳዊ ትምህርት የቅኔ መምህርነት አስመስክረዋል፣ አቋቋም ተምረዋል፣ በረካታ የቤተክርስቲያን ትምህርቶችን ተምረዋል። ከልጅነት እስከምንኩስና በርካታ የችግር ጊዜዎችን አልፈዋል። እማሆይ ዜና ማርያም በዲማ ጊዮርጊስ ቅኔ ተምረዋል፣ በባህርዳር የአብነት ትምህርት ቤት አቋቋም ተምረዋል። በዘመናዊ ትምህርት የመጀመርያ ድግሪ ተምረው ተመርቀዋል፣ በዚህ አመት በ2014 ደግሞ በከፍተኛ ማዕርግ የማስተር ድግሪያቸውን ይዘዋል። በአሁኑ ሰዓት በቅድስት ሰላሴ መንፈሳዊ ዩኒበርስቲ በማስተማር ላይ ይገኛሉ። እማሆይ ዜናማርያም በልጅነታቸው ከሰንበት ትምህርት ቤት የጀመራቸው የእግዚአብሔር ቃልና ለእግዚአብሔር ራስን የመስጠት ፍቅር እንዲሁም በእግዚአብሔር ቃል የመጠራት ጥበብ በሴትነታቸው የደረሰባቸውን ባህላዊና ቤተሰባዊ ጫና በትዕግስትና በእግዚአብሔር ጥበብ በማለፍ ለዚህ ክብር የበቁ እናት ናቸው። በታላቁ ገዳም በደብረ ሊባኖስ የምንኩስናን ተቀብለው የመንፈሳዊ ህይወት ሰባኪ ሆነው ቀጥለዋል። እማሆይ ዜናማርያም ለሴቶች የሚከብድ የሚመስለውን ህይወት ኖረው አሳይተዋል እየኖሩትም ነው። የዕማሆይ ፅናታቸውና እምነታቸው ገራሚ ነው። በወጣትነታቸው የገቡበትን መንፈሳዊ ህይወትና ውጣ ውረድ አልፈው ዛሬ ደግሞ ለዚህ ክብር በቅተዋል። በሁለት የተሳለ ሰይፍ የመሆን ምስጢርን አሳይተዋል። እግዚአብሔር አምላክ እናታችን በዕድሜ በፀጋ ይጠብቅልን https://t.me/Hamerzetewahido  

የተርገበገበ ዬተግለበለበ አይደለም ለህልውና ተጋድሎ ለሽሮ ወጥም አይሆንም። በልካችን እንደ ልካችን አንጓዝ።

ምስል
የተርገበገበ ዬተግለበለበ አይደለም ለህልውና ተጋድሎ ለሽሮ ወጥም አይሆንም። በልካችን እንደ ልካችን አንጓዝ። እንዴት አደርን? ደህና ናችሁን እነ ማህበረ ክብር? ለቅኖች ላም እረኛ ምን አለን ለሚያዳምጡ ብቻ የተኮለመ። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"     1) አዲስ ገቦች እያክለፈለፋት ነው ሁለመናውን። አልጠግብ አሉ መቃወሙን። ከላይ ከላይ ሁለመናውን ያጫጭኑታል። በአግራሞት እዬተከታተልኩት ነው። ምልሰታቸው መልካም ቢሆንም ጥድፊያው ግን አሻሮ ያደርጋል። መሪ ነንም ባዮች ናቸው። ነባሩም ከእነሱ ጋር ግልቢያ ይዟል። አዝናለሁኝ። ስክነት አልቦሽ ትግል ዬክስረት ካንፓኒ ነው። ርጋት ያስፈልጋል። ጠቅላይ ሚር አብይን አታውቋቸውም በዬሰከንዱ ምን ያህል የምንሳሳለትን እንደሚያጋዩ። ዓለምም እራሱ ገና አላወቃቸውም። እንዲህ ዓይነት መሪወች በጥንቃቄ ሊያዙ ይገባል። እንኳንስ መጣንብህ፤ ደረስንብህ ቀርቶ #በዝምተ #ለመገደል እንኳን አይፈቅዱም። ሳትደርሱባቸው ደረሱብኝ፤ መጡብኝ ተደራጁብኝ ብለው ሲያጭዱም ሲያምሱም ድፍን አምስት ዓመት ሞላ። ቢያንስ #ዘመነ #ፍዳን ተረድቶ ከችግሩ ጋር የቆዬው አደብ ገዝቶ በስክነት መራመድ ሲገባው ከአዲስ ገቦች ጋር ግልቢያው አልገባኝ አለ። ዛሬ ረቂቁ መከራ እሬሳ ይሸሸጋል። አሁን የድላቸው መከብከቢያ እስከመሆን ደርሷል። በማይዘልቅ ማህበርተኝነት በአልሰከነ ፍላጎት ስንት ነገር፤ ስንት የላቀ መንፈስ #አነጠፍን #አንጠፈጠፍን ። ቢያንስ 12993 ዬቅኔው ጎጃም ዬአማራ ተማሪወች የተስፋ እንቅፋትን እንደምን ለናሙና ወስደን ተግ ማለት፤ አደብ መግዛት ዬሚያሳጣንን መስመር መቅጣት ይሳነናል። ስህተት እንደምን መምህር መሆን ያቅተዋል? አቅምን ማኔጅ ማድረግ እንደምን ያቅታል? ቲም ዘኔ ቀጥሎ አሰልጥኖ ቢሆን በኮፒ ራይት ባያተራምሱት ...

ዬቸርነት ዜና ስለ ግዕዝ እና አማርኛ ቋንቋ ከአቶ መኮነን ያሬድ ሰይፋ። አገር ቤት ውጊያ ውጭ አገር ንግሥና።

ዬቸርነት ዜና ስለ ግዕዝ እና አማርኛ ቋንቋ ከአቶ መኮነን ያሬድ ሰይፋ። አገር ቤት ውጊያ ውጭ አገር ንግሥና። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።" ጥንታዊው የግዕዝ ቋንቋ በታላቁ ሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ። "እ.ኤ.አ. 2016 ጀምሮ ጥንታዊውን የግዕዝ ቋንቋን እንዲሁም የአማርኛ ቋንቋንም ጭምር በታላቁ ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ በታላቅ ክብር እና ሞገስ እንደ አንድ የውጭ ሃገር ቋንቋ ለዩኒቨርስቲው ተማሪዎች እያስተማርን ነው። ክብርና ምስጋና ለልዑል እግዚአብሔር ይሁን። እናት ዓለም ኢትዮጵያ ዕፁብ ድንቅ ሀገር ከአንቺ በመፈጠሬ እና የአባቶቼ ልጅ በመሆኔ ደስታዬ እጥፍ ድርብ ነው። አንቺ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ጡትሽን ጠብቼ በማደጌ ምንኛ ዕድለኛ ነኝ እንዲሁም ይኽን ጥንታዊ የግዕዝ ቋንቋን እስከአሁን ድረስ ተንከባክበሽ እና ጠብቀሽ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ስለ አደረግሽልን የላቀ አስተዋጽዖ ሁሉ ምሥጋና ይግባሻል። በዚህ ምድር ሲኖሩ ዘመኑን የዋጁ ወደር ለማይገኝላቸው ቀደምት ጀግኖች አበው አባቶቻችን ከፍ ያለ የከበረ ምሥጋና ይድረሳቸውና ብራና ፍቀው ቀለም ቀምመው የራሳችን የሆነ ፊደላት ቀርጸው በጽሁፍና በዜማ ለእኛ አስተላልፏልን። ምን ያደርጋል ታዲያ ተረቱ "ከሞኝ ደጅ ሞፈር ይቆራጣል" ይሉ ዘንድ ሆነብንና ነገሮች ሁሉ የተገላቢጦሽ ነጮቹ የእኛ የሆነውን ታሪክ ሁሉ ለማወቅ የማይቆፍሩት ነገር የለም እኛ ደግሞ የነሱን።" መጪው ዘመን የግዕዝ ቋንቋ ትንሣኤ ይሆናል!!! እግዚአብሔር ሀገረ ኢትዮጵያን ይባርክ!!!  

ይድረስ ለቀዳማዊት እመቤት ለወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው

ምስል
ይድረስ ለቀዳማዊት እመቤት ለወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው አዲስ አበባ። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።" ጉዳዩ፦ ይቅርብኝን አምጦ ስለመውለድ።     ለቁርጥ ውሳኔ ሂደትን መጀመር የወቅቱ ጥያቄ ይመስለኛል። ጊዜን መሻማት፤ ጊዜን መቅደም ብልህነት ነው። ብልህነቱ ህክምናው እራስን ከማዳን ይጀምራል። ራስን ማዳን ቀዳማይ ዬሰው ልጅ ዬተፈጥሮ ግዴታ ነው። ይህን ግዴታ በራስ ላይ ሲጭኑት ውሳኔ ይሻል። ውሳኔው ሊኮሰኩስ ይችላል። ግን አትራፊነቱ መራራን ገጠመኝን ከመቋቋም ይነሳል። ኮስኳሳ ውሳኔ #ላምነት ወይንም #ከፈይ ዬመሆን ዕድሉ በጊዜ መጠቀም ሲቻል ብቻ ይሆናል። ወርቅ ከቀለጠ ይፈሳል ጊዜም ካመለጠ ፀፀትን ያፀድቃል። ጊዜ ሲሰጥ ፈቃደ እግዚአብሔርን አጠይቆ ነው። እናም ይህ ጊዜ ሁለቱ የዓራት ኪሎ የቤተ መንግሥት በጋብቻ የተሳሰሩ ጥንዶች በአኃቲ ልቦና መክረው የሚደርሱበት ውሳኔ እራስን፤ ህዝብን፤ ትውልድን፤ ታሪክን የማዳን ታላቅ ተልዕኮ አለው ብዬ በጽኑ አምናለሁኝ። የከፋን አደጋ ለመቅደም ማስተዋልን ማስተዋል። #ዬተከበሩ ቀዳማዊት እመቤት ወሮ ዝናሽ ታያቸው ሆይ! ዛሬ የተሰጠን ለዛሬ ብቻ ነው። በዛሬ ውስጥ ያለው ነገ እኛ የምንሠራው ብቻ ሳይሆን የፈጣሪ ፈቃድም ነው። ዬኢትዮጵያ ዛሬ ጣር ላይ ነው ያለው አካላቶቿ ሁሉ። በሞተ ዛሬ ነገን ማግኜት ደግሞ ጋዳ ነው። አይቻልም። መሸቀዳደም ያስፈልጋል። እሽቅድድሙ ለፍውሰት፤ ለድህነት ነው። ተጎድቶም ቢሆን ፍውሰት እና ድህነት ከተገኜ የመንፈስ ትርፍም ነው። አብሮ ያልተፈጠረን፤ ነገ በእዮር ጥሪ ተትቶ ለሚሄድበት ዬድንኳን ቤት ለከፋ ነገሮች ስለምን ተምሳሌት ይኮናል? እግዚአብሄር እስከ ፈቀደ ድረስ ኢትዮጵያን ያህል የሚስጢር አገር #አካልተአምሳል ሆናችሁ መርታችኋል። ብዙ ጊዚያችሁ በፍሰኃ፤ በሰናይ አሳልፋችኋል። ክብ...

ስምንት መምህራን በአዲስ አበባ በድጋሚ ታሠሩ። ዬጉጂ ተጋድሎ ጠንክሮ ቀጥሏል።

ምስል
ስምንት መምህራን በአዲስ አበባ በድጋሚ ታሠሩ። ዬጉጂ ተጋድሎ ጠንክሮ ቀጥሏል። አጭር መረጃ። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"     እንዴት አደርን? ስክነትንውጠን ወይንስ ብስጭትን አርግዘን የምንታገለው ከቬርሙዳ ትርያንግል ጋር በመሆኑ ስክነት፤ ዬሚጣደፋትን እዬገራን፤ አዲስ ገቦችን ሰከን በሉ በማለት መስመራችን ጠብቀን መታገል ይኖርብናል። ከእንዲህ ስለ ክፋው ሥርዓት ቁመና ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልግም ቂምን፤ በቀልን፤ አግላይነትን የተጠዬፈ ትግል በስክነት። #ጉጂ እና ተጋድሎው። በቅድሚያ በጨካኞች ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቼ ሰማዕትነትን ፈጣሪ ይስጥልኝ። ቤተሰቦቻቸውንም ፈጣሪ ያጽናናልኝ። አሜን። ጉጂ እና ቦረና የሚያውቁት ጉጂ እና ቦረነታቸውን ከፍ ሲል ደግሞ ኢትዮጵያዊነታቸውን ነው። በድርቁ እንዲያልቁ ዬተፈረደባቸውም የማህበረ ሌንጮ አጥፊ ፖለቲካን ስለማይቀበሉ ነው። #ሚስጢሩ ይህ ነው። መሠረታቸውን ለመበወዝ ፕሮጀክት ተሰርቶበታል። ድፍጠጣ። ይህ በዚህ እንደ አለ ዬብአዴን እና የኦህዴድ ዬወልዮሽ ጉባኤ በአዲስ አበባ እዬተካሄደ እነ አጅሬ አዲስ የከተማ አደረጃጀት እና ዕውቅና የሰጠ ውሳኔ አሳልፈው ነበር። ብዙም የሚዲያ ሽፋን አላገኜም ነበር። በዚህ መሃል ጉጂ በቃን ንቅናቄ ጀመረ። ንቅናቄው በእኔ ዕይታ ሳቢያ አይደለም። ምክንያታዊ ነው። ምክንያታዊ ንቅናቄ ለስኬት ቅርብ ነው። ፖለቲካው ሲመዘን። አሁን የሚሰማው የገዳ አባቶች ደግሞ መሃል እንደገቡ ተደምጧል። የልጆቻቸውን ጥያቄ ያስማርካሉ ወይንስ ለድል ያበቃሉ? ጥያቄው ይህ ነው። ሌላው ግን የዶር ለማ መገርሳ የከተማ ፖለቲካ ፕሮጀክት አካል ነው ሂደቱ። ጨምተን ለምንከታተለው። #መምህራን እና ዘመነ ገዳወኦዳ። ከገዳ ወረራ፤ ከገዳ መስፋፋት፤ ከገዳ አስምሌሽን፤ ከገዳ ዲስክርምኔሽን ጋር ተያይዞ ለአንድ...

ዬመዳፍ አጤ ዬጉራጌ ማህበረሰብ የህልውና መከራ እንደ አለበት ሊያውቅ ይገባል።

ዬመዳፍ አጤ ዬጉራጌ ማህበረሰብ የህልውና መከራ እንደ አለበት ሊያውቅ ይገባል። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።" ቀደምቱ፤ ጭምቱ፤ ሥራ፤ የማህበራዊ ኑሮ አንበሉ፤ ኢኮኖሚስቱ የጉራጌ ማህበረሰብ የህልውና ተጋድሎ ማድረግ ይገባዋል ዬሚል ጽኑ እምነት ላይ ደርሻለሁ። የህልውና ተጋድሎ ያለባቸው ማህበረሰባት፤ አመክንዮወች ተዳብለው ሳይሆን እራሳቸውን ችለው ትግል ፈጥረው፤ ተቋም ሆነው መታገል ይኖርባቸዋል። የዘመኑ ዬፖለቲካ ባህሬ ቁመና ዬገዳ ወረራ፤ ዬገዳ አስምሌሽን፤ የገዳ መስፋፋት እና ዬገዳ ዲስክርምኔሽን መሆኑን ጨዋው፤ ጭምቱ ወገናችን ተርድቶ ሰላማዊ ተቋም የሲቢክሳ ሳይሆን ዬፖለቲካ ፈጥሮ መታገልን አህዱ ሊለው ይገባል። እራሱ ጉጂ እና ቦረናኦሮሞ መነሻ ዋርካ ሆነው ችግራቸው የህልውና ስለመሆኑ አልተረዱትም። ዬእነሱን መነሻነት የሚበውዝ ሂደት ነው ያለው። እንኳንስ ሌሎች ዬማህበረሰብ ክፍሎች። አፋር፤ ሃድያም፤ ጋንቤላ፤ ወላይታ፤ ጋሞ፤ አማሮ፤ ጌዲዮ ወዘተ ቀጣዮቹ ተጠቂወችናቸው። ለምን? ቀደምት ናቸው። ከሁሉ በላይኢትዮጵያ ጽላታቸው ሁለመናቸው ናት። አሁን ግብግቡ ከግዙፋ ጋር ነው። ግዙፍ ስል በአሰፋፈርም በህዝብ ብዛትም ማለቴ ነው። አንድ ሚዲያ ላይ በአዲሱ ክልል የማትካለሉ ከሆነ የኦሮሞልዩ ዞን ሁኑ የሚል ከጠቅላዩ ዬቀረበው ፍንጭም መጪው ጊዜ ለጉራጌ ማህበረሰብ ቀራንዮ ሊሆን እንደሚችል ያመላክታል። ይህም ብቻ ሳይሆን በ100 ቀናት የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ትጋት ጉራጌ ላይ በጣም አቃለው ለቀረበው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ሰምቻለሁኝ። ጉራጌ የገዘፈ ማንነት ያለው ብልህ ህዝብ ነው። የቤተሰብ አስተዳደሩ እና ውስጥነቱ አዘውትሬ እምቀናበት ማህበረሰብ ነው። የኢትዮጵያ መዳፍም፤ ዬኢኮኖሚ ፈላስፋ ጭምቱ ጉራጌ ነው። በደረሰው በሚደርሰው ዬ30 ዓመት በደልእጅግአዝናለ...

«ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ግልጽ ደብዳቤ ለዶ/ር ዓቢይ አህመድ አሊ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስቴር

ምስል
«ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ግልጽ ደብዳቤ ለዶ / ር ዓቢይ አህመድ   አሊ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስቴር   ሲያደክሙን ከባጁት ደጋፊወቻቸው ዬተጣፈ ነው። ፍቅር ሲያልቅ ትዕግስት ይሰደዳል። ሙሉ አምስት ዓመት ለወደመው እኛነት ተጠያቂው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ብቻ??? ወይንስ በሙሉ አቅም አፈርጥሞ ጭካኔ እንዲጨፈጭፈን ያስደረገ ቤተ - ደጋፊ? ይቅርታው? ፀፀቱ? ንስኃስ?   «ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ግልጽ ደብዳቤ ለዶ / ር ዓቢይ አህመድ   አሊ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስቴር አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ የካቲት 29 ቀን 2015 ዓም (March 8, 2023) ለተከብሩ ዶ / ር ዓቢይ አህመድ ለኢትዮጵያ ሀገራችን ትውልድና ታሪክ ተሻጋሪ የሆነ ለውጥ ያመጣሉ በሚል ተስፋ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ እርስዎንና መንግሥትዎን እስከዛሬ ድረስ በሙሉ ልብ ድጋፉን በመስጠት፤ ወደእናት ሀገሩ የእርዳታ ገንዘብ በመላክ፤ መዋዕለ ንዋዩን በማፍሰስ፤ በድርቅና በግጭት በመፈናቀል ብዙ ጉዳት የደረሰባቸዉን ዜጎቻችንን በመርዳትና መልሶ በማቋቋም፤ በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት በሞያ የተደገፈ ምክር በመስጠትና በቁሳቁስ በማገዝ ዳያስፖራው ለሀገሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ከእነዚህ በተረፈ፣ ለዐባይ የህዳሴ ግድብ ስኬት ገንዘብ በማዋጣትና በዲፕሎማሲው መስክ ድጋፍ በመስጠት ሰፊ የሆነ ያልተቋረጠ እገዛ አድርጓል። ሀገራችን ኢትዮጵያ በሰሜኑ የትግራይ ጦርነት ሳቢያ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ በገባችበት ወቅትም ዳያስፖራው ከእርስዎ፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ከመከላከያና የ...