#መመረቅ። ከሃመር ተዋህዶ ዬተገኜ ነው እማሆይ ዜና ማርያም

ከሃመር ተዋህዶ ዬተገኜ ነው
እማሆይ ዜና ማርያም 

 
=============
በመንፈሳዊ ትምህርት የቅኔ መምህርነት አስመስክረዋል፣ አቋቋም ተምረዋል፣ በረካታ የቤተክርስቲያን ትምህርቶችን ተምረዋል። ከልጅነት እስከምንኩስና በርካታ የችግር ጊዜዎችን አልፈዋል። እማሆይ ዜና ማርያም በዲማ ጊዮርጊስ ቅኔ ተምረዋል፣ በባህርዳር የአብነት ትምህርት ቤት አቋቋም ተምረዋል። በዘመናዊ ትምህርት የመጀመርያ ድግሪ ተምረው ተመርቀዋል፣ በዚህ አመት በ2014 ደግሞ በከፍተኛ ማዕርግ የማስተር ድግሪያቸውን ይዘዋል። በአሁኑ ሰዓት በቅድስት ሰላሴ መንፈሳዊ ዩኒበርስቲ በማስተማር ላይ ይገኛሉ።
እማሆይ ዜናማርያም በልጅነታቸው ከሰንበት ትምህርት ቤት የጀመራቸው የእግዚአብሔር ቃልና ለእግዚአብሔር ራስን የመስጠት ፍቅር እንዲሁም በእግዚአብሔር ቃል የመጠራት ጥበብ በሴትነታቸው የደረሰባቸውን ባህላዊና ቤተሰባዊ ጫና በትዕግስትና በእግዚአብሔር ጥበብ በማለፍ ለዚህ ክብር የበቁ እናት ናቸው። በታላቁ ገዳም በደብረ ሊባኖስ የምንኩስናን ተቀብለው የመንፈሳዊ ህይወት ሰባኪ ሆነው ቀጥለዋል።
እማሆይ ዜናማርያም ለሴቶች የሚከብድ የሚመስለውን ህይወት ኖረው አሳይተዋል እየኖሩትም ነው። የዕማሆይ ፅናታቸውና እምነታቸው ገራሚ ነው። በወጣትነታቸው የገቡበትን መንፈሳዊ ህይወትና ውጣ ውረድ አልፈው ዛሬ ደግሞ ለዚህ ክብር በቅተዋል። በሁለት የተሳለ ሰይፍ የመሆን ምስጢርን አሳይተዋል።
እግዚአብሔር አምላክ እናታችን በዕድሜ በፀጋ ይጠብቅልን

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።