የተርገበገበ ዬተግለበለበ አይደለም ለህልውና ተጋድሎ ለሽሮ ወጥም አይሆንም። በልካችን እንደ ልካችን አንጓዝ።

የተርገበገበ ዬተግለበለበ አይደለም ለህልውና ተጋድሎ ለሽሮ ወጥም አይሆንም። በልካችን እንደ ልካችን አንጓዝ።
እንዴት አደርን? ደህና ናችሁን እነ ማህበረ ክብር?
ለቅኖች ላም እረኛ ምን አለን ለሚያዳምጡ ብቻ የተኮለመ።
"ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"
 

 
1) አዲስ ገቦች እያክለፈለፋት ነው ሁለመናውን። አልጠግብ አሉ መቃወሙን። ከላይ ከላይ ሁለመናውን ያጫጭኑታል። በአግራሞት እዬተከታተልኩት ነው። ምልሰታቸው መልካም ቢሆንም ጥድፊያው ግን አሻሮ ያደርጋል። መሪ ነንም ባዮች ናቸው። ነባሩም ከእነሱ ጋር ግልቢያ ይዟል። አዝናለሁኝ። ስክነት አልቦሽ ትግል ዬክስረት ካንፓኒ ነው። ርጋት ያስፈልጋል። ጠቅላይ ሚር አብይን አታውቋቸውም በዬሰከንዱ ምን ያህል የምንሳሳለትን እንደሚያጋዩ። ዓለምም እራሱ ገና አላወቃቸውም።
እንዲህ ዓይነት መሪወች በጥንቃቄ ሊያዙ ይገባል። እንኳንስ መጣንብህ፤ ደረስንብህ ቀርቶ #በዝምተ #ለመገደል እንኳን አይፈቅዱም። ሳትደርሱባቸው ደረሱብኝ፤ መጡብኝ ተደራጁብኝ ብለው ሲያጭዱም ሲያምሱም ድፍን አምስት ዓመት ሞላ። ቢያንስ #ዘመነ #ፍዳን ተረድቶ ከችግሩ ጋር የቆዬው አደብ ገዝቶ በስክነት መራመድ ሲገባው ከአዲስ ገቦች ጋር ግልቢያው አልገባኝ አለ።
ዛሬ ረቂቁ መከራ እሬሳ ይሸሸጋል። አሁን የድላቸው መከብከቢያ እስከመሆን ደርሷል። በማይዘልቅ ማህበርተኝነት በአልሰከነ ፍላጎት ስንት ነገር፤ ስንት የላቀ መንፈስ #አነጠፍን #አንጠፈጠፍን። ቢያንስ 12993 ዬቅኔው ጎጃም ዬአማራ ተማሪወች የተስፋ እንቅፋትን እንደምን ለናሙና ወስደን ተግ ማለት፤ አደብ መግዛት ዬሚያሳጣንን መስመር መቅጣት ይሳነናል። ስህተት እንደምን መምህር መሆን ያቅተዋል? አቅምን ማኔጅ ማድረግ እንደምን ያቅታል? ቲም ዘኔ ቀጥሎ አሰልጥኖ ቢሆን በኮፒ ራይት ባያተራምሱት ራዕዩን፤ እሱም ቅንነቱን ቢገራ ኖሮ ዛሬ ምን ላይ ይገኝ ነበር ትግሉ??? ዬቲም አንባቸውን ትቼ ማለት ነው።
አሁን ደግሞ ጉዳዩ ወደ ህጋዊው ባለሥልጣና የአማራ ሊሂቃኑ ሽግግር ያደረገ ይመስላል። ይህን አደብ ገዝቶ ማድመጥ ሲገባ ስንኛትን አልደግማቸውም እምሰማው ሂዱ እና ፍጇቸው ነው። ያልሆነውን፤ ያልተሰማውን እንደአለ አድርጎ ማቅረብ ተስፋን ያደርቃል። እኔ እማዬው የአማራ ህዝብ #ሆስቴጅ ተደርጎ ነው። ዬታሠረውን ትቼ በመኖር ውስጥ ዬሚገኜው አማራን ማለቴ ነው። አሁን ጉራጌም ተጨምሯል። ዬሰው ልጅ ቢታመም እንኳን ምን ሊገጥመው እንደሚችል ፈጣሪ ነው ዬሚያውቀው።
2) ዬኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ንዑድ ሆና ነው መከራን እዬተቀበለች ያለችው። ሲሶ፤ እርቦ፤ እኩሌታ መንግሥት ይሰጠኝ ብላ አላመለከተችም፤ አልተጋፋችም፤ እናንተ በምትገዙት ልጆቼ ስንት እጅ ተሰጥቷቸዋል ብላ አልጠዬቀችም። የጠዬቀችው ሥርዓቴ ቀኖናዬ፤ ድንጋጌን አከብር ዘንድ መንግሥት የዜግነት ዋስትናዬን ያረጋግጥልኝ ነው።
የሚገርመው ፖለቲከኛው ሁሉ የራሱን ሥራ ሳይሰራ ማመካኛ፤ መጠጊያ ፍለጋ መንፈሷን ያባትለዋል። ገዢውም ኦነጋዊው ኦህዴድ ሥርዕወ፤ ተደማሪው ተስፈኛውም፤ ተቀናቃኙም ይፈልጋል የእሷን ጥያቄ ታኮ ሌላ ምንትሶ። ያለካልኳታል። ይህ ዬተገባ አይደለም። #ደንበር #ወሰን ሊኖር ይገባል። ማትረፍ በጥንቃቄ ነው። ሱባኤ ላይ ናት። ዓራት አይናማ ዬተጠሞኑ እረኛ አላት። እኛ በገኃዱ ዓለም ውቂ ደብልቂ እሷ በእዮራዊ መንፈስ ቅዱስ ፀጋ ነው የምትመራው። እና ካለ ፀጋችን፤ ካለመሰጠታችን #ባናነኩረው ዬተገባ ነው።
በሁለቱም ስክነት ዬለሽ ጉዞ መከራውን ያገዝፈዋል፤ መስዋዕትነቱንም ያበራክተዋል። ለዛውም ከጭካኔ ጋር ለባጀ ማህበረሰብ፤ በራህብ፤ በቸነፈር፤ በስጋት፤ በማቅ፤ በጦርነት እዬተጠቃ #ያለውም አብሮ #እንዲደህይ ፕሮጀክት ተቀርፆለት እዬተሰራ እያዬን ነው። ከሁሉ የሚጨንቀው መራራው ስንብት በስጋ መለዬት ነው። ሁሉን ያጣን እንዳንሆን በስልት እና በዘዴ // በጥበብ እና በጥሞና፤ በፀሎት እና በእርጋታ// በድዋ እና በመደማመጥ ይህን የምፃት ዘመን ለመሻገር አደብ መግዛት ያስፈልጋል። #እንደ #ገና #መወለድ
3) ደጋግሜ እንደምለው ደስታን በልክ መያዝ ይገባል። በሦስት ምክንያት። አንዱ ተጨማሪ ደስታ ሲገኝ መደርደሪያ እንዳታጡ፤ ሁለተኛው ደስታው ሳይዘልቅ ተስፋ እንዳትቆርጡ፤ ሦስተኛው ደስታ እና ፈንጠዝያ ምርቃት ስለሚያስነሳ።
4) በድንገቴ ደራሽ ነገር ከመዋጥ በዘላቂ እና ሥር ነቀል አመክንዮ ላይ አትኩሮት ማድረግ ይበጃል። ሙሉ የሥርዓት ለውጥ፤ ቅኖች በህብረት የሚመሯት ተፈጥሯዊ አገር ትኖረን ዘንድ ፈቅ አድርጎ አስቦ ዘለግ አድርጎ መሥራት ይጠይቃል።
ውዶቼ ደህና ዋሉልኝ፤ ደህና አምሹልኝ፤ ደህና እደሩልኝም። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/03/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።