ዬቸርነት ዜና ስለ ግዕዝ እና አማርኛ ቋንቋ ከአቶ መኮነን ያሬድ ሰይፋ። አገር ቤት ውጊያ ውጭ አገር ንግሥና።

ዬቸርነት ዜና ስለ ግዕዝ እና አማርኛ ቋንቋ ከአቶ መኮነን ያሬድ ሰይፋ። አገር ቤት ውጊያ ውጭ አገር ንግሥና።
"ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"
ጥንታዊው የግዕዝ ቋንቋ በታላቁ ሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ።
"እ.ኤ.አ. 2016 ጀምሮ ጥንታዊውን የግዕዝ ቋንቋን እንዲሁም የአማርኛ ቋንቋንም ጭምር በታላቁ ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ በታላቅ ክብር እና ሞገስ እንደ አንድ የውጭ ሃገር ቋንቋ ለዩኒቨርስቲው ተማሪዎች እያስተማርን ነው። ክብርና ምስጋና ለልዑል እግዚአብሔር ይሁን።
እናት ዓለም ኢትዮጵያ ዕፁብ ድንቅ ሀገር ከአንቺ በመፈጠሬ እና የአባቶቼ ልጅ በመሆኔ ደስታዬ እጥፍ ድርብ ነው። አንቺ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ጡትሽን ጠብቼ በማደጌ ምንኛ ዕድለኛ ነኝ እንዲሁም ይኽን ጥንታዊ የግዕዝ ቋንቋን እስከአሁን ድረስ ተንከባክበሽ እና ጠብቀሽ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ስለ አደረግሽልን የላቀ አስተዋጽዖ ሁሉ ምሥጋና ይግባሻል። በዚህ ምድር ሲኖሩ ዘመኑን የዋጁ ወደር ለማይገኝላቸው ቀደምት ጀግኖች አበው አባቶቻችን ከፍ ያለ የከበረ ምሥጋና ይድረሳቸውና ብራና ፍቀው ቀለም ቀምመው የራሳችን የሆነ ፊደላት ቀርጸው በጽሁፍና በዜማ ለእኛ አስተላልፏልን። ምን ያደርጋል ታዲያ ተረቱ "ከሞኝ ደጅ ሞፈር ይቆራጣል" ይሉ ዘንድ ሆነብንና ነገሮች ሁሉ የተገላቢጦሽ ነጮቹ የእኛ የሆነውን ታሪክ ሁሉ ለማወቅ የማይቆፍሩት ነገር የለም እኛ ደግሞ የነሱን።"
መጪው ዘመን የግዕዝ ቋንቋ ትንሣኤ ይሆናል!!!
እግዚአብሔር ሀገረ ኢትዮጵያን ይባርክ!!!

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።