ዬመዳፍ አጤ ዬጉራጌ ማህበረሰብ የህልውና መከራ እንደ አለበት ሊያውቅ ይገባል።

ዬመዳፍ አጤ ዬጉራጌ ማህበረሰብ የህልውና መከራ እንደ አለበት ሊያውቅ ይገባል።
"ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"
ቀደምቱ፤ ጭምቱ፤ ሥራ፤ የማህበራዊ ኑሮ አንበሉ፤ ኢኮኖሚስቱ የጉራጌ ማህበረሰብ የህልውና ተጋድሎ ማድረግ ይገባዋል ዬሚል ጽኑ እምነት ላይ ደርሻለሁ።
የህልውና ተጋድሎ ያለባቸው ማህበረሰባት፤ አመክንዮወች ተዳብለው ሳይሆን እራሳቸውን ችለው ትግል ፈጥረው፤ ተቋም ሆነው መታገል ይኖርባቸዋል። የዘመኑ ዬፖለቲካ ባህሬ ቁመና ዬገዳ ወረራ፤ ዬገዳ አስምሌሽን፤ የገዳ መስፋፋት እና ዬገዳ ዲስክርምኔሽን መሆኑን ጨዋው፤ ጭምቱ ወገናችን ተርድቶ ሰላማዊ ተቋም የሲቢክሳ ሳይሆን ዬፖለቲካ ፈጥሮ መታገልን አህዱ ሊለው ይገባል።
እራሱ ጉጂ እና ቦረናኦሮሞ መነሻ ዋርካ ሆነው ችግራቸው የህልውና ስለመሆኑ አልተረዱትም። ዬእነሱን መነሻነት የሚበውዝ ሂደት ነው ያለው። እንኳንስ ሌሎች ዬማህበረሰብ ክፍሎች። አፋር፤ ሃድያም፤ ጋንቤላ፤ ወላይታ፤ ጋሞ፤ አማሮ፤ ጌዲዮ ወዘተ ቀጣዮቹ ተጠቂወችናቸው። ለምን? ቀደምት ናቸው። ከሁሉ በላይኢትዮጵያ ጽላታቸው ሁለመናቸው ናት። አሁን ግብግቡ ከግዙፋ ጋር ነው። ግዙፍ ስል በአሰፋፈርም በህዝብ ብዛትም ማለቴ ነው።
አንድ ሚዲያ ላይ በአዲሱ ክልል የማትካለሉ ከሆነ የኦሮሞልዩ ዞን ሁኑ የሚል ከጠቅላዩ ዬቀረበው ፍንጭም መጪው ጊዜ ለጉራጌ ማህበረሰብ ቀራንዮ ሊሆን እንደሚችል ያመላክታል። ይህም ብቻ ሳይሆን በ100 ቀናት የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ትጋት ጉራጌ ላይ በጣም አቃለው ለቀረበው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ሰምቻለሁኝ። ጉራጌ የገዘፈ ማንነት ያለው ብልህ ህዝብ ነው። የቤተሰብ አስተዳደሩ እና ውስጥነቱ አዘውትሬ እምቀናበት ማህበረሰብ ነው። የኢትዮጵያ መዳፍም፤ ዬኢኮኖሚ ፈላስፋ ጭምቱ ጉራጌ ነው።
በደረሰው በሚደርሰው ዬ30 ዓመት በደልእጅግአዝናለሁኝ። ሰላም እዬተደበደበ ሰላም ሚር አፈራለሁኝ። እራሱ የጉራጌ፤ የአገው፤ የጋሞ፤ ዬወላይታ፤ የአፋር ወዘተ ህዝባችን እኮ ሰላሞች ናቸው። ፍፁም ሰላሞች ለሰላምም ሐዋርያ ለዛም የተፈጠሩ። ምንግዜም ከጎናቸውም ነኝ። በዕንባቸው፤ በመከራቸው ሁሉ። የቀደመው ዓለም የሚያውቀው ተጋድሎኝ ለድምጽ አልባወቹ ዬኢትዮጵያ እናቶች ድምጽ መሆን ነው። አሁንም እምሠራበት ይኽው ነው። የችግሩ ጫና የቅደምተከተል መስመር ቢኖረውም።
ሌላው ጉራጌ የሚሰቃይበት በማቱቡ አዳሪ ስለሆነ ነው። ለመስቀል ቀናኢ ነው። ዬእስልምና ዕምነት ተካታዮችም ቢሆኑ የጨመቱ ናቸው መኖርን ዬተጠበቡ።
እግዚአቤሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
10/03/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ፍቅር ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።