ስምንት መምህራን በአዲስ አበባ በድጋሚ ታሠሩ። ዬጉጂ ተጋድሎ ጠንክሮ ቀጥሏል።

ስምንት መምህራን በአዲስ አበባ በድጋሚ ታሠሩ። ዬጉጂ ተጋድሎ ጠንክሮ ቀጥሏል።
አጭር መረጃ።
"ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"
 

 
እንዴት አደርን? ስክነትንውጠን ወይንስ ብስጭትን አርግዘን የምንታገለው ከቬርሙዳ ትርያንግል ጋር በመሆኑ ስክነት፤ ዬሚጣደፋትን እዬገራን፤ አዲስ ገቦችን ሰከን በሉ በማለት መስመራችን ጠብቀን መታገል ይኖርብናል። ከእንዲህ ስለ ክፋው ሥርዓት ቁመና ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልግም ቂምን፤ በቀልን፤ አግላይነትን የተጠዬፈ ትግል በስክነት።
#ጉጂ እና ተጋድሎው።
በቅድሚያ በጨካኞች ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቼ ሰማዕትነትን ፈጣሪ ይስጥልኝ። ቤተሰቦቻቸውንም ፈጣሪ ያጽናናልኝ። አሜን። ጉጂ እና ቦረና የሚያውቁት ጉጂ እና ቦረነታቸውን ከፍ ሲል ደግሞ ኢትዮጵያዊነታቸውን ነው። በድርቁ እንዲያልቁ ዬተፈረደባቸውም የማህበረ ሌንጮ አጥፊ ፖለቲካን ስለማይቀበሉ ነው። #ሚስጢሩ ይህ ነው። መሠረታቸውን ለመበወዝ ፕሮጀክት ተሰርቶበታል። ድፍጠጣ።
ይህ በዚህ እንደ አለ ዬብአዴን እና የኦህዴድ ዬወልዮሽ ጉባኤ በአዲስ አበባ እዬተካሄደ እነ አጅሬ አዲስ የከተማ አደረጃጀት እና ዕውቅና የሰጠ ውሳኔ አሳልፈው ነበር። ብዙም የሚዲያ ሽፋን አላገኜም ነበር። በዚህ መሃል ጉጂ በቃን ንቅናቄ ጀመረ። ንቅናቄው በእኔ ዕይታ ሳቢያ አይደለም። ምክንያታዊ ነው። ምክንያታዊ ንቅናቄ ለስኬት ቅርብ ነው። ፖለቲካው ሲመዘን።
አሁን የሚሰማው የገዳ አባቶች ደግሞ መሃል እንደገቡ ተደምጧል። የልጆቻቸውን ጥያቄ ያስማርካሉ ወይንስ ለድል ያበቃሉ? ጥያቄው ይህ ነው። ሌላው ግን የዶር ለማ መገርሳ የከተማ ፖለቲካ ፕሮጀክት አካል ነው ሂደቱ። ጨምተን ለምንከታተለው።
#መምህራን እና ዘመነ ገዳወኦዳ።
ከገዳ ወረራ፤ ከገዳ መስፋፋት፤ ከገዳ አስምሌሽን፤ ከገዳ ዲስክርምኔሽን ጋር ተያይዞ ለአንድ ወር ታሥረው የተፈቱት መምህራን ድጋሚ መታሰራቸው ተደምጧል። ለመሆኑ መምህራን ማህበር አለን? በአንድ ወቅት አደራጃቸው ነበርኩ። እነሱን ለመምራት የተለዬ ስልት እና ጥበብ ይጠይቅም ነበር። ምክንያት ፀጋቸው ወላጅ አቅማቸው ዕውቀት ስለነበር። ጉልበት ያለው ድርጅት አጥሩ እዬተነቀቀ ነው ዝምታው ግን እጅግ ያስፈራል። ዬሆኖ ሆኖ የትናንት እና የዛሬው ዬእስር ዘመቻ እንደሚቀጥል አስባለሁኝ።
ምክንያቱም አዲስ አበባ ከመስከረም 05/2011 ዓም በኦሮምያ ሥር ነውና ዬምትተዳደረው። ዘግይታችሁ ጓደኞቼ የሆናችሁ ይህን ፌቡ ከመጀመሬ በፊት የፃፍኩት፤ የሞገትኩት ነው። ለዚህ ነው በብዙ ነገር እማልደነግጠው። በጥዋቱ የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ ቀድሜ ስለአወቅኩት፤ በዛ ልክ ነው እምራመደው። አቅሜን በሥርዓት ነውም እማስተዳድረው። ላይኬም ሼሬም በመቅኑን ነው። አቅም ለጭካኔ መስጠት ባሩድ ማቀበል ስለሆነ።
1) መምህር አቶ ዘመነ ጌቴ።
2) መምህር አቶ ምስግናው ጫኔ።
3) መምህር አቶ ዘለዓለም ልዑል።
4) መምህር ታያቸው አካለው።
5) መምህር ማትያስ መለሰ።
6) መምህር የቆዬው አሻግሬ።
7) መምህር አቶ ሰይፈ ሚኬኤል።
8) መምህር አቶ ዘመኑ ዋለ።
ዬመምህራኑን ዝርዝር ያገኜሁን ከኢትዮ ኒውስ ነው።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
10/03/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
መሸቢያ ቀን።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።