ዕለተ ሰኞ ዕለተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት ብራ ለራህብ የሚራራ። „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።“ (ትንቢተ ዕንባቁም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17) ዕለተ ሰኞ ማዕዶት ጠባቂ ሁሉም አጀንዳ የሚሰናገድበት ዕለት ነው። መንፈሴ በይ ያለኝን ሁሉ ያለገደብ የሚኮለምበት። ዛሬ የቀናው አጀንዳ እንዴት ሰነበታችሁ? ሰንበት እንዴት አለፈ? ኢትዮጵያስ እንደምን እያሆነች ነው ይላል። • 365 x 3 = 1095 x 24= 26,280 የቁጥር ተማሪ አይደለሁኝም። በቁጥር ትምህርት እጅግ ደካማ ነበርኩኝ። ስለዚህ ስህትት ሊኖርበት ቢችልም እርዕሴ አይፈረድበትም። እኔ የባይወሎጂ እና የኬሚስትሪ ጎበዝ ተማሪ ነበር የነበርኩት፤ እንዲያውም 11/12ኛ በደረጃ ነበር ተሸልሜ ያለፈኩት። የሆነ ሆኖ ወደ ዕርዕሰ ጉዳዬ ምልሰት ሳደርግ ሰውኛ ኢትዮጵያ ውስጥ በዬደቂቃው አደጋ ውስጥ ነው። ህዝብ እያለቀ ነው። ሞቱ ብቻ አይደለም በስጋት እና በሽብር ኢትዮጵያዊው ሰው ከጽንሰት ጀምሮ እዬተረሸነ ነው። ሰው አለን ለማለት አንችልም። እንዲያውም እኔ ቤት ሆኜ ሳስበው ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ያህል የሥነ - ልቦና ባለሙያ ይኖር ይሆን እላለሁኝ። መጪው ጊዜ መርግ ነው። ችግሩ አልተጀመረም ብዬ ነው እማስበው። • ምክንያቱም … ከአጤ ዝናቡ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጀምሮ የሥነ - ልቦና ህመም የለብኝም የሚል ሊኖር ስለመቻሉ እርግጠኛ አይደለሁም። እያንዳንዱ ደቂቃ በደም ውስጥ ያለፈ // ያለም ነው። እያንዳንዱ ደቂቃ በጭንቅ ውስጥ ነው የሚያልፈው// ያለም። „ከእኛ የሚሞተው ከሌላ አገር ጋር ሲነጻጸር ትንሽ ነው“ ባይ ሄሮድሳዊ መሪ ያላት አገር ናት - ኢትዮጵያ። „ግብጽ ጦርነት ትጀምር ብዙ ስራ የሌላቸው ደሃ ልጆች አሉን...